አርአያ ተስፋማርያም/Araya Tesfemariam


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች🇪🇹

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ለመላው የክርስቲና እምነት ተከታዮች በመሉ እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

መልካም በዓል!


ጎረቤታችን ሶማሊላንድ የመልካም በዓል መልዕክት አስተላልፈዋል እናከብራችኋለን እናመሰግናለን🙏 https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0yiotKYiNaV9r3g5SgHa6Fr4p5RXqLsd3Ldbh4azwx1Jq59ECouNE8s2nVtR5F66bl&id=61555703253147&mibextid=Nif5oz


ወቅታዊ መረጃዎችን በአማረኛ የሚያቀርበው የሶማሊላንድ የፌስቡክ ገፅ በመሆኑ ገፁን Follo Share ያድርጉ
https://www.facebook.com/61555703253147/posts/pfbid03R5crQQMUD6AFHePVms9H6VCaYdCTeiNBts3xNfe6xZPZAMyJhYiowszMiGXeBrrl/?app=fbl


#ነውርእናወንጀል መጀመሪያ ተመልካች ለመሳብ ያደረጉት ርዕስ መስሎኝ ነበር (በእርግጥ እሱም ቢሆን ሩብ እንኳ ልክነት አይኖረውም ፕሮግራሙ ውስጥ ያለው ድድብና የባሰ ሆኖ ከቨር ስለሚያደርገው እንጂ)

ፍልፍሉ "ይቅርታ ሴት ደፍሬ አውቃለሁ..." ሲል ጃሉድ ቀለል አድርጎ "የምን ይቅርታ ነው? ፈጣሪውንስ ሚዳፈር አለ አይደል እንዴ? ኖርማል ነው" ይለዋል።

ጥላሁን ይቀበልና "አዎ ስንት ነገር አለ አይደል ይሄማ ኖርማል ነው። የእኔን አባት ጨምሮ አብዛኛው ወንድ ጠልፎ'ና ደፍሮ ነው ያገባው" ብሎ ስለ አስገድዶ መድፈር የሰራውን ዘፈን ይዘፍናል።

ደፈራት ደፈራት ደፈራት
መሬት አስተኝቶ እያንፈራፈራት
እኛ እስከምናውቀው ከጥንት ጀምሮ
ሁሉም ሰው ያገባው አስገድዶ ደፍሮ

ከጀርባቸው ብዙ ሳቅ አለ የሚያወሩት እና የምሰማው የተለያየ እስኪመስለኝ ድረስ ።

ምንድነው ልትነግሩን የፈለጋችሁት? ምንድነው የምታደርጉት? ሚዲያውስ ልክነቱን አምኖበት፥ ሀሳቡን ተቀብሎት ነው ፕሮሰሱን ሁሉ አሳልፎ እንዲተላለፍ ያደረገው? አልገባኝም

Via Beza Wit

@EliasMeseret




"እነሆ÷ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው።" ሉቃ ፪÷፲፩


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ!


ከናቅናት ቀጣይ የኢትዮጵያ ፈተና ትሆን ይሆናል!!

ይሄ ትርክት በዚህ ከቀጠለ በኢትዮጵያ ውስጥ ከተከሰቱ ችግሮችና አሁንም እየተከሰተ ካለው ችግር ሊብስ ይችላል በብልፅግና ዘመን ነገሮች ሲጀምሩ ይናቃሉ (under mine) ይደረጋሉ ያቺ የመናቅ አባዜን ስለማቃት ነው ዛሬ ለመፃፍ የተገደድኩት,ይቺ ሀገር ጫና በዝቶባታል ብየ ነው በዛሬው ዕለት ታላቅ የኢሳ ህዝብ እንመሰርታለን ሲባል ማንን ለመግጠም እንደሆነ ለማውቅ አይቸግርም ለማንኛውም በሽንሌ ዞን የጀቡቲ እናና የኢትዮጵያ ኢሳ ጎሳ የጀቡቲ ገንዘብ ሚ/ር እና የሶማሌ ክልል ም/ፕሬዚዳንት አቶ እብራሂም ኡስማን ትልቅ ህዝባዊ ስብሰባ እያካሄዱ ነው።በዚህ ስብሰባ ከተሳተፉት መሃከል አቶ አልያስ ደዋሌ ይገኙበታል፥ አቶ ኤልያስ ደዋሌ ማለት ደግሞ የጀቡቲ ገንዘብ ሚ/ር የዛሬ ሁለት አመት አዋሽ ውንዝ የጀቡቲ ነው ብሎ ትዊተር ገፅ የለጠፈ ደፋር ሰው ናቸው። ስለዚህ ይቺ መሰባሰብ ለበኋላ እንዳንነታርክባትና ወደ ማያበራ ችግር እንዳትወስደን በአግባቡ እንያት ግድ የለም ለማለት ነው።


ነፍስ ይማር😭

ትናንት ከነዛ ወራሪ ጥይት ተርፋችሁ ዛሬ ትናንት ጋሻ መከታ በሆንክለት ወንድም ጥይት መሞታችሁ ከልብ አሳዝኖኛል 😭😭😭


ነፍስ ይማር😭

ትናንት ከነዛ ወራሪ ጥይት ተርፋችሁ ዛሬ ትናንት ጋሻ መከታ በሆንክለት ወንድም ጥይት መሞታችሁ ከልብ አሳዝኖኛል 😭😭😭


እውነት ያሸንፋል!


የመከላከያ ሰራዊት ለሀገራዊ ደኅንነት የመጨረሻው ምሽግ በመሆኑ ለሕዝባችን እና ሀገራችን ደኅንነት ሁልጊዜም እንሠራለን ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የአየር ጥበቃ ፖሊስ አባላቱን እና ቴክኒሻኖች አስመርቋል፡፡
በዚሁ ወቅት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባደረጉት ንግግር÷ በርካታ ልፋትን አከናውናችሁ የማዕረግ ሽልማትን ያገኛችሁ የአየር ሃይል አባላትና ቤተሰቦች ለዚህ ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
አየር ሃይል የሀገሪቱ መከላከያ ክንድ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይሄንን ኃይል ማጠንከር ብቻ ሳይሆን የባህር ሃይል አቅምንም በመጨመር ከፍ ማለት እንደሆነ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ትልቅ የምድር ሃይል አቅምን ገንብታለች ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ÷ አየር ሃይላችንንም በከፍተኛ አቅምና ችሎታ የጠነከረ ለማድረግ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዘመነ ህውሓት የአየር ሃይሉን አቅም በአቅሙ ወደታች የሆነ እና የብሄር ብሄረሰብ ተዋጽኦም ያልነበረው ተቋም አድርጎት እንደነበረ አስታውሰው÷ ኢትዮጵያ ለስሙ ብቻ አየር ሃይል አላት ተብሎ ለውድቀት እንድትዳረግ ያደረገ የህውሓት የሴራ ውጤት እንደነበረም ገልጸዋል፡፡
የሀገሪቱን የፓይለት ባለሙያዎች ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን÷ ከውጭም ሌሎቹን ማሰልጠን የሚችል አቅም ተፈጥሯል ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአፍሪካ የልምድ መውሰጃ ማዕከል እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን÷ ባለፉት ሁለት አመታት በተሰራው ስራም ለውጥ ማምጣት ተችሏል ተብሏል።
አየር ሃይሉ የደረሰበትን ከፍታ በሽብር ቡድኑ ላይ ያከናወነው የጀግንነት ተግባር እና ጀብዱ ማሳያ እንደሆነ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ


እንኳን ለከተራና ለብርሐነ ጥምቀቱ በዓል በሠላም አደረሣችሁ!


የተመድ ውሳኔ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
_የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ህወሓትን ለምን በክፉ ዓይን አየሽብኝ በሚል በኢትዮጵያ የሚሰሩትን ኬንያዊቷን የሥራ ኃላፊ ከሀላፊነት ማንሳቱን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል።

አሸባሪውን ድርጅት “ቆሻሻ“ እና “ጨካኝ” በሚል የገለጹትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አለቆችን ለአማጺው ቡድን ይወግናሉ በሚል ያጋለጡት በኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ ዋና ኃላፊ ሞሪን አቺንግ ከኒውዮርክ በተላለፈ ትዕዛዝ በትላንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ተደርጓል።

ይሄንን ተከትሎም ኬንያዊያንን ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ውሳኔውን በመቃወም ላይ ይገኛሉ። ሞሪን አቺንግ ስለትግራይ ሁኔታ ሀሳባቸውን ባጋሩበት የድምፅ ቅጂ ላይ “ህወሓቶች ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመለሱ የትግራይ ተወላጅ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ እያሴሩ ነው፤ እና ከዚያ ከሩዋንዳ ምን አይነት የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር አታውቁም። ብቻ ግን ያለው ነገር ቆሻሻ ነው” በማለት ገልፀዋል።

ተመድ 7 የድርጅቱ ሰራተኞች ከዚህ ቀደም ከአሸባሪው ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ቅሬታ ችላ ብሎ ቡድኑ እያደረሰ የሚገኘውን ጥፋት ብሎም የተመድን ያልተገባ አቋም የተቹትን ኃላፊ ከሥራ ማሰናበቱ የድርጅቱን ገለልተኛነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ሆኗል።

የተመድን እርምጃ በመቃወም ድምጻቸውን ካሰሙት መካከል የሆኑ ኬንያዊያን ”በጥቁር አድሏዊነት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኬንያዊቷን ሞሪን አቺንግ ለእውነት በመቆማቸው እና ህወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ የፈጸማቸውን ጭካኔ በማውገዛቸው ከሥራ አግዷቸዋል። ማስፈራራት ቢኖርም እንኳን ኬንያውያን ሁል ጊዜ ለኢትዮጵያ ይቆማሉ።“ በሚል ገልጸዋል።


ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት በመላው ኢትዮጵያ የሚታየውን የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ አስመልክቶ ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። በስብሰባው ላይ የሀገሪቱን ጸጥታ እና ደኅንነት ሊያስጠብቁ የሚችሉ ቀጣይ ተግባራት እንዲከናወኑ አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።


ሽፍታው የ30 አመት የመስረቅ የመዝረፍ የመዋሸት የመግደል ልምድ ነው ያላቸው ኢትዮጵያ በቃችሁ ብትላቸው እናፈርስሻለን አሏት ግን አትችሉም ብለዋቸዋል ልጆቿ ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ሽፍታውና ጠላቶቿ ግን ይቀበራሉ።


ተስፋ የቆረጠው የሽፍታው መሪ ደብረፅዮን ለአንቶዮ ጎቴሬዝ አደራድሩኝ እያለ መለመን ይዟል። ለድርድር የተላኩት የሀገር ሽማግሌዎች ክብር አዋርደው እንደመለሱ እንዴት እንደረሱት ይገርማል።የተሰጣችሁን እድል አበላሽታችኋል። ከዚህ በኋላ ያላችሁ እድል መተሰር አልያም መሞት ነው።


የትግራይ ተወላጆች አሸባሪው ህወሓትን ለመታገል ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

"ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ" ብሎ የተነሳውን አሸባሪውን ህወሓት ለመታገል ቁርጠኛ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተናገሩ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በክፍለ ከተማው ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት እንደተገለጸው፤ አሸባሪው ህወሓት ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የክፋት፣ የጥላቻና የዘረኝነት እንቅስቃሴዎችን ሲያራግብ ቆይቷል።

አሸባሪው ህወሃት የዘራውን አሉታዊ አስተሳሰብ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከውስጡ አውጥቶ የአሸባሪውን የክፋት አመለካከት በጽኑ ሊታገለው እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በመድረኩ አስተያየታቸውን የሰጡት ወይዘሮ ንግስቲ አበበ፤ አሸባሪው ህወሓት በሴራ ፖለቲካ ዘረኝነት እንዲስፋፋና ዜጎች እርስ በርስ እንዲጋጩ አድርጓል፤ እያደረገም ነው።

ይህ የሽብር ቡድን ለእኩይ ዓላማው ሲል የትግራይ ወጣቶችና ህፃናትን በማስገደድ ለጦርነት በመማገድ እያስጨረሰ መሆኑንም አንስተዋል።

አሸባሪው ሕወሃት ለህዝብ የማይጠቅም መሆኑን ጠቁመው፤ ቡድኑን ለማስወገድ እስከ መጨረሻው ለመታገል ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

የቡድኑን ዓላማ ለማስፈፀም በአዲስ አበባ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸው፤ "እኔ እያለሁ ኢትዮጵያ አትፈርስም" ብለዋል።

በማንኛውም መንገድ የአገር ሰላምን ለማደፍረስ ከሚያሰሩ አካላት መራቅ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው የክልሉ ተወላጅ አቶ ማቲዎስ ገብረሥላሴ፤ “ዜጎች ሁሉ የኢትዮጵያን አንድነት ለማስቀጠል መስራት ይኖርባቸዋል” ብለዋል።

ትግራይ የኢትዮጵያ ጠንካራ መሰረት መሆኗን የተናገሩት አቶ ተካ አበበ፤ የአሸባሪውን ሴራ ለመቀልበስ የትግራይ ህዝብ እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በአንድነት መቆም እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም በአንድነት ሊቆም እንደሚገባም ጠቁመዋል።

ሌላኛዋ የክልሉ ተወላጅ ወይዘሮ መሰሉ ረዳ እንደገለጹት፤ አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህዝብ እርዳታ እንዳያገኝ በማድረግ ለክልሉ ሕዝብ ጠላትነቱን በማስረጃ አረጋግጧል።

ይህ የሽብር ቡድን ዳቦ ሊሰጣቸው የሚገባ የትግራይ ህፃናትን ከእናቶቻቸው ጉያ ነጥቆ ሀሺሽ በመስጠት ወደ ጦርነት መማገዱ የሚያሳዝንና ሊወገዝ የሚገባው ድርጊት እንደሆነም አመልክተዋል።

በተለይም "ለክልሉ ሕዝብ ደህንነት የአካባቢው ተወላጆች ይህንን የሽብር ቡድን በጋራ መታገል አለብን" ብለዋል።

"እኔ ያልመራኋት ሀገር ትፍረስ" በማለት የሽብር ተግባር የሚፈጽመው አሸባሪው ህወሃት ለትግራይም ሆነ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይጠቅም አብራርተዋል።

የክፍለ ከተማው የህዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ዘመን ተስፋዬ በበኩላቸው እንደተናገሩት፤ አሸባሪው ህወሓት ከውጪ ሀይሎች ጋር በመሆን ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴውን በጋራ መመከት ይገባል።

አሸባሪው ቡድን የከፈተውን የውክልና ጦርነት በመመከት ረገድ የክልሉ ተወላጆች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጠይቀዋል።

በተለይም በአዲስ አበባ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች የከተማውን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅና የኢኮኖሚ አሻጥርን በመዋጋት የበኩላቸውን መወጣት እንደሚገባቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


''ኢትዮጵያ ትስዕር''



20 last posts shown.

8 864

subscribers
Channel statistics