BULBULA G/SECONDARY SCHOOL 2


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


SARIS, AKAKI KALITI

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


















መጋቢት 8/2016 ዓ.ም

ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከተማሪ ወላጆች ጋር ውይይት አካሂዷል።


በዛሬው ዕለት ከ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የተማሪዎች ወላጆች ጋር ውይይት አድርገናል። በውይይታችን የመማር የማስተማር ስራችንን በአግባቡ ለማከናወን በሚያስችሉ የቀጣይ ተግባራትና በታዩ ችግሮች ላይ ስለሚወሰዱ መፍትሄዎችና ስለሚከናወኑ ተግባራት  ዝርዝር ውይይት ተደርጓል። የመጀመሪያ መንፈቀ ዓመት የተማሪዎች የውጤት ትንተና ሪፖርትም ቀርቦ ከት/ቤቱ አስተዳደር፣ ከወተመህ እና ከተማሪ ወላጆች ጠቃሚ ሃሳቦች ተሰጥቷል። በማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ኦፊሰር አማካኝነትም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ለማስፈን መደረግ ስላለበት ተግባር ለወላጆች ግንዛቤ ተሰጥቷል።

የተማሪዎችን ውጤትና ሥነ ምግባርን ለማሻሻል ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ት/ቤቱ በጋራ ሊያከናውኗቸው ስለሚገቡ ጉዳዮችም መግባባት ተደርሷል።

ወተመህን በአዲስ ለማደራጀት ከትምህርት ቢሮ በወረደው እቅድ መሠረት እና በክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በተላለፈው የማስፈጸሚያ ሰነድ መሠረት የት/ቤት ወተመህ አባላት እንዲመረጡ ተደርጓል።

በት/ቤታችን በመጀመሪያው መንፈቀ ዓመት የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ለወላጆቻቸው የተበረከተ ሲሆን በመጨረሻም ወላጆች የልጆቻቸውን ውጤት መግለጫ ካርድ ከክፍል ኃላፊ መምህራን እንዲወስዱ ተደርጎ ስብሰባው ተጠናቋል።




Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown


Forward from: Unknown

20 last posts shown.