🔝
የአንገት ጌጡ አንድ ውብ ወጣት ሴት ነበረች። ነገር ግን ከድሀ ወገን ስለነበረች አንድ ተራ ፀሀፊ አገባች።በህይወቷ ደስተኛ አልነበረችም።*ታዲያ ባሏ የትምህርት ሚኒስትሩ ከሚገኙበት ታላቅ ግብዣ ተጠራ።ዜናው ያስደስታታል ብሎ ሮጦ መጥቶ ቢነግራት እንደጠበቀው አልተደሰተችም።**
"ምነው?" ቢላት
"ምን ለብሼ እሄዳለሁ?" አለችው።
ትንሽ አሰበና ለአስፈላጊ ጊዜ ይሆናል ብሎ አስቀምጦት ከነበረ ብር ላይ 300 ፍራንክ ቀንሶ ሰጣት
ደስ እያላት ሄዳ አዲስ ቀሚስ አሰፋች።
ቀሚሱ ካለቀ በኋላ ደግሞ ለካ ስታስበው ምንም የሚረባ ጌጣ ጌጥ የለት።ባሏ ግን አንድ ሀሳብ አቀረበላት።አንድ ሀብታም ጓደኛ ነበረቻት።
"እና ለምን ከሷ አትዋሺም?" አላት።
በማግስቱ ጓደኛዋ ጋር ሄደች።
መረጠችና በጣም የተዋበ የአንገት ሉል ተዋሰች
አሁን ሁሉም ሙሉ ሆነ።ወደ ግብዣው ሄደች።ሰዎች ምን ያህል ውብ እንደሆነች አዩ።ሁሉም ሰው ከሷ ጋር መደነስ ፈለገ።ሚኒስትሩ ሳይቀሩ አነጋገሯት።በህይወቷ በጣም የተደሰተችበት ቀን ሆነ።
ግብዣው አልቆ ከባሏ ጋር በሰረገላ ተሳፍራ ወደ ቤቷ ሄደች።ቤት ስትደርስ ሉሉን ከአንገቷ ላይ ብትፈልገው አጣችው።በጣም ደነገጠች።ከባሏ ጋር ሆነው በመጡበት መንገድ ተመልሰው ሌሊቱን ሁሉ ሲፈልጉት አደሩ።ሊያገኙት አልቻሉም።በማግስቱም በብርሀን ፈለጉት። ምንም ፍንጭ ጠፋ። ተስፋ ቆረጡ።
በመጨረሻ ጌጣ ጌጥ ሰሪ ቤት ሄደው ተመሳሳዩን ለመግዛት ጠየቁ።17000 ፍራንክ ተባሉ።ድሀ ቤተሰብ ናቸው!እድሜ ልካቸውን ከፍለው የማይጨርሱት የአራጣ ብድር ተበድረው ሉሉን ገዝተው ለባለቤቷ መለሱ።ከዚያ ያንን ብድር ለመክፈል ሁለቱም ከአቅማቸው በላይ ሶስት አራት ስራ እየሰሩ በ10 አመት ብድሩን ከፍለው ጨረሱ። በድካሟ መሀልም፣ ያን ሌሊት ያ ጌጥ ባይጠፋ ፣ ህይወቷ ምን ሊመስል ይችል እንደነበር ታልማለች።
ታዲያ ያች ውብ ወጣት ሴት በስራ ብዛት ምክንያት ያለእድሜዋ ገርጅፋ ወዟ መልኳ ጠፍቶ አስቀያሚ አሮጊት መስላለች።አንድ ቀን መንገድ ላይ ያች ሀብሉን ያዋሰቻትን ሴት ታገኛታለች።
አሁን ያለፈ ስለሆነ ስለ ሉሉ ወይም ስለ ጌጡ መጥፋት ልንገራት ትልና ሰላምታ ትሰጣታለች።ሀብታሟ ሴት ግን ልታውቃት አልቻለችም፦"እኔ ማቲልዳ ነኝ"
"ውይ ምነው አረጀሽ?"
"ባንቺ ምክንያት ነው!"
"በኔ? እንዴት?"
"ታስታውሻለሽ ውድ ጌጥ አውሰሽኝ ነበር"
"አዎ"
"እና ጠፋብኝ"
"እንዴ መልሰሽልኛል እኮ"
"አዎ!ግን በምትኩ ሌላ በ17000 ፍራንክ ገዝቼ ነው የመለስኩልሽ"
ጓደኛዋ በጣም አዘነች።
"እኔ ያዋስኩሽ እኮ አርቴ ነበር,,,ዋጋውም 500 ፍራንክ አይሞላም!!!"
በህይወቴ ካነበብኳቸው አጭር ታሪኮች ሁሉ ምርጡ " የአንገት ጌጡ " ነው!
👉በየቀኑ ጠቃሚ መልእክቶችን፣ መጽሐፍት ፒዲኤፍ፣ በነፃ የምታገኟቸው አሪፍ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች፣ የቢዝነስ ሃሳቦች እና የገንዘብና የተለያዩ ሽልማቶችን ለማግኘት ገጾቻችንን ይቀላቀሉ።
📱ቴሌግራም👉
@Beleqe_boostup📱ፌስቡክ ገጽ👉
https://www.facebook.com/SuperBoostUp🌐ዌብሳይት 👉
https://superboostup.com/📱ቲክቶክ👉
tiktok.com/@superboostup