በዚህ ምድር ላይ የምትኖርበት ጊዜ የተወሰነ ነው፡፡ ቁጥሩም የታወቀ ነው፡፡ ወሰኑና ድንበሩም የተመጠነ ነው፡፡ የቁጥሩ ወሰን ላይ እስከምትደርስ ድረስ ግን፣ መንገዱ ክፍት ነው፡፡ ሜዳውም ሰፊ ነው፡፡ በዚህ ሜዳ ላይ ዕቅድህን ለማሳካት ትሮጣለህ፡፡ ግብህን ከዳር ለማድረስ ትኳትናለህ፡፡ ውጥንህ እንዲሞላ ላይ ታች ትላለህ፡፡ አንዳንዴ ይሳካል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይጠምማል፡፡ አንዳንዴ ይሞላል፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይጎድላል፡፡
አንዳንዴ ከልብህ ትስቃለህ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ ምርር ብለህ ታለቅሳለህ፡፡ አንዴ ታመሰግናለህ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ታማርራለህ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሠው ታምናለህ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ አይ ሠው! ብለህ ተስፋ ትቆርጣለህ፡፡ ትነሳለህ ደግሞ ትወድቃለህ፡፡ ትሾማለህ ደግሞ ትሻራለህ፡፡ ትሰጣለህ ደግሞ ትወስዳለህ፡፡ ሕይወት ማለት ይህ ነው፡፡ የመፈራረቅ ኑሮ!
📓ርዕስ፦ከማዕዘኑ ወዲህ
✍️ደራሲ፦ዳግማዊ አሰፋ
📚
@Bemnet_Library