በበኩሌ ከምሽቱ 3:00 በኋላ የሚኖር የስልክ ወሬ አልስማማም!
በተለይ "እንፋቀራለን" በሚሉ ተቃራኒዎች መካከል የሚኖረው ንግግር በአብዛኛው የስጋ ሀሳብ ላይ ያተኮረ ስለሚሆን ወዳልተገባ ነገር ለመሄድ መንገድ ጠራጊ ነው።
ሄሀ
በእንቅልፍ በተከበበ የተስለመለመ ድምፅ የሚሰማው አካል የስጋ መሻቱ ሊያይል ይችላል። በዚህም መሀል ነው የምታፈቅሪኝና የምታምኚኝ ከሆነ ፎቶሽን( Private part ተጠቅሶ) ላኪልኝ የሚል ቦንብ ጥያቄ የሚከተለው። በመጀመሪያው ቀን ላይሆን ይችላል በተደጋገመ ቁጥር ግን ነገሮች እውን እየሆኑ ይሄዳሉ።
"አፍቃሪሽ" አፍቃሪህ በምን ታውቅሀለች? ፍቅረኛዬ ከ 3:00 በኋላ ቃል ታነባለች፣ትፀልያለች፣መዝሙር ትሰማለች፣ተኝታለች፡ በአጠቃላይ ከጌታ ጋር ህብረት እያደረገች ስለሆነ አልረብሻትም ብሎ ያከብርልሻል ወይስ በፈለኩ ሰዓት እንደፈለኩ አገኛታለሁ እንደውም ፀሎትም ላይ ከሆነች አቋርጣ ለኔ ጊዜ ትሰጣለች ብሎ ያስባል/ታስባለች?
በነገራችን ላይ በዚህ ጊዜ አብዛኛው "ተፋቃሪ" ለእግዚአብሔር ከሚሰጠው ጊዜ ይልቅ ነገ ታግባው አታግባው እርግጠኛ ላልሆነችበት ሰው ጊዜዋን ትሰጣለች። አገልግሎት ቀርታ ካፌ ልታገኛት ትችላለህ።
ወደዋናው ሀሳቤ ስመለስ ሌሊት ላይ ስልክ የምትደዋወሉ ሰዎች ግዴላችሁም ይቅርባችሁ። የሌሊትን የስልክ ወሬ ሰይጣንም የራስህም ስጋ አይቃወምህም። እስቲ ወሬ ያቁምና ለፀሎት ተንበርከክ! በቅፅበት ነው እንቅልፍ ጓዙን ጭኖ የሚመጣው። #WHY?
እናንተ ምን ትላላችሁ?
❤️ @Biblicalmarriage❤️
@Biblicalmarriage_bot