ብስራት ስፖርት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ትኩስ መረጃዎችን ፣ የዝውውር ዘገባዎች እንዲሁም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እኛ ጋር በላቀ ጥራት እና ብቃት ያገኛሉ!
✍️ @jonwilly

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


🗣 ሳሊባ

"እኔ እዚህ አርሰናል ጋር በመሆኔ እጅግ ደስተኛ ነኝ። በኮንትራቴ ሁለት አመት ከግማሽ ይቀረኛል እናም እዚሁ መቀጠል እፈልጋለሁ"

"ከአርሰናል ጋር ትልልቅ ነገሮችን ማሸነፍ እፈልጋለሁ! አርሰናል ቆይተህ ምንም ዋንጫ ሳታነሳ ከክለቡ ከወጣህ ደጋፊዎች ይረሱሀል! እዚህ ማሸነፍ እፈልጋለሁ"

@BisratSportTm


የማንቸስተር ዩናይትድ ባለድርሻ ሰር ጂም ራትክሊፍ!

"300 ሚልዮን ፓውንድ ካወጣሁ በኋላ አሁን በክለቡ የቀረ ምንም አይነት ገንዘብ የለም"

"ነገርግን ከሶስት ወይም ከአምስት አመት በኋላ ማንቸስተር ዩናይትድ የአለማችን አትራፊው ክለብ ይሆናል"

@BisratSportTm


ኒውካስል ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

ሰኞ ምሽት በተደረገ የ28ተኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኒውካስል ዌስትሃምን በብሩኖ ጉማሬስ ብቸኛ ጎል ታግዞ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ኒውካስል ማሸነፉን ተከትሎ ከቼልሲ በ2 ነጥብ ተበልጦ ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ደግሞ በእኩል 47 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 6ተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

@BisratSportTm


🗣️ ክቫራትሼሊያ

"በፓሪስም ሆነ በአንፊልድ ተጫወትን ምንም ማለት አይደለም! ግባችን ነገ ማሸነፍ ነው! ያለንን ሁሉ እንሰጣለን።"

@BisratSportTm


ጠያቂ: ልጅ በነበርክበት ጊዜ ከባርሴሎና የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል የሚባለው ወሬ እውነት ነው?

የኤስፓኞል አስልጣኝ ማኖሎ ጎንዛሌዝ እንዲህ ሲል መልሷል...

"እውነት ነው! ባርሴሎና አይመቸኝም መቼም ቢሆን ወድጃቸው አላውቅም! በፍፁም ወደ እነሱ አልሄድም ይሄንን እነሱም ስለሚያውቁ አይጠሩኝም"

@BisratSportTm


ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች !

እዚህ ቻናል ላይ እንዲስተካከል የምትፈልጉት እና ያልተመቻችሁ ነገር ካለ ይስተካከላል

ሀሳብ አስተያየታችሁን ከስር ኮሜንት ላይ አስቀምጡ 👇


የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች እና አሰልጣኝ ዩምበርግ አስገራሚ አስተያየት ሰጥቷል !

"እንደ ኦዴጋርድ ወይም ሳካ ጥሩ ተጫዋች ከሆንክ በዚህ ክለብ ውስጥ ሻምፒዮናውን የማሸነፍ እውነተኛ እድል እንዳለህ ታስባለህ? ወይንስ ከንቱ እስክትሆን ድረስ ትጠብቃለህ?"

"ተጫዋች እያለሁ ወኪሌን ሻምፒዮናውን ወደማሳካበት ቦታ ልሄድ ስለምፈልግ ስለ ገንዘብ ደንታ እንደሌለኝ እነግረው ነበር።" በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል

@BisratSportTm


✅ ኮዲ ጋክፖ ወደ ልምምድ ተመልሷል

@BisratSportTm


📸 || የፔዤ ስብስብ ሊቨርፑል ከተማ ደርሰዋል !

@BisratSportTm


ሞሀመድ ሳላህ የካቲት ወር የፕሪምየር ሊግ የደጋፊዎች የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል ተመርጧል።

@BisratSportTm


ሊቨርፑል በሚቀጥለው የውድድር አመት በሜዳው ፣ ከሜዳው ውጪ እና አማራጭ ሶስተኛ ማልያው እነዚህ እንደሚሆኑ በስፋት እየተዘገበ ይገኛል።

@BisratSportTm


በነገው ዕለት አንፊልድ ተጉዞ ሊቨርፑልን የሚገጥመው የፔዤ ስብስብ ይፋ ሆኗል!

@BisratSportTm


አስገራሚ እውነታ !

ቫንዳይክ ለሊቨርፑል በአንፊልድ በፕሪሚየር ሊጉ 115 ጨዋታዎችን ተጫውቶ የተሸነፈው 3 ጨዋታዎችን ብቻ ነው።

@BisratSportTm


ሊቨርፑል ከፈረንጆቹ ኦገስት 1 2025 ጀምሮ ከአዲዳስ ጋር ለመስራት ከስምምነት መድረሳቸውን በኦፊሻል ገፃቸው አስታውቀዋል።

NIKE ከሊቨርፑል ጋር ይሄ አመት የመጨረሻው ነው!

@BisratSportTm


በያዝነው የፕሪሚየር ሊግ የውድድር አመት በአንድ ጨዋታ ብዙ ታክሎችን በመውረድ ካስሜሮ በጉዬ እና በለሚና ብቻ ነው የሚበለጠው።

በትናንትናው የአርሰናል ጨዋታ ካስሜሮ 9 ታክሎችን መውረድ ችሎ ነበር!

Warrior In Midfield ⚔

@BisratSportTm


ዴክለን ራይስ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ !

"እስከ ውድድር አመት መጨረሻ ድረስ ያለንን ሁሉንም ነገር እንሰጣለን! ሊቨርፑል አስደናቂ ነበሩ ነገርግን ገና አላበቃም መግፋታችንን መቀጠል አለብን እኛ አርሰናል ነን።"

"አሁንም ብዙ ጨዋታዎች ይቀራሉ"

@BisratSportTm


ተጠባቂው ጨዋታ በአቻ ተጠናቋል !

በ28ተኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል አንድ አቻ በሆነ ውጤት ጨዋታውን አጠናቀዋል።

የማንቸስተር ዩናይትድን ጎል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከቅጣት ምት ሲያስቆጥር የአርሰናልን የአቻነት ጎል ራይስ ከመረብ አሳርፏል።

@BisratSportTm


ራይስ ከጎሉ በኋላ የማን ዩናይትድ ደጋፊዎችን ዝም በሉ ብሏል

@BisratSportTM


የተጠናቀቁ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች

➣ ቶተንሃም 2 - 2 በርንማውዝ

➣ ቼልሲ 1 - 0 ሌስተር ሲቲ

@BisratSportTm


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በአሁኑ ሰዓት ኦልድትራፎርድ አቅራቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የማንቸስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ለግሌዘሮች ተቃውሞ እያሰሙ ይገኛሉ

@BisratSportTm

20 last posts shown.