ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት
ለባንካችን ከፍተኛ አመራሮች ‘‘ሥነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት’’ በሚል ርዕስ ጥር 30 እና የካቲት 1/ 2017 ዓ.ም በሀይሌ ግራንድ ሆቴል ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናው የተገኙት የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ስልጠናውን አብረን በመውሰድ ወደ ተግባር መለወጥ ይገባል ብለዋል።
ይህ ‹‹ሥነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልዕኮ ስኬት!›› በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት በተሰጠው ስልጠና የሙስና ምንነት ፣የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት፣በባንክ ዘርፍ የሚሥተዋሉ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዲሁም የሙስና መከላከያ ስልቶች የሚሉት ጉዳዮችን ያካተተ ሲሆን ስልጠናውም መቶ የሚጠጉ የባንኩ ከፍተኛ ፣መካከለኛ እንዲሁም ዝቅተኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡ከስልጠናው ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች ከአሰልጣኙ እንዲሁም ከቤቱ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በስልጠናው ማጠቃለያም ሰልጣኞች ለሁለት ቀናት ያገኙትን ዕውቀት የሚፈትሽ ምዘና ተከናውኗል፡፡
ስልጠናው ማጠቃለያም የባንካችን የሰው ሃብት ዋና መኮንን የሆኑት አቶ ሰይፉ ቦጋለ ለሰልጣኞች ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው የሙስና እና ብልሹ አሰራር ክፍተቶችን የጠቆመ በመሆኑ አመራሩ ወደ ተግባር መቀየር አለበት ብለዋል፡፡
ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ድረ_ገጻችንን ይጎብኙ፤
https://www.bankofabyssinia.com/cr/#Bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ