Bule Hora University


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


Bule Hora University Official telegram

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት YOLK ከተባለው ግብረሰነይ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን ሀምበላ ዋመና ወረዳ በጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት በፀሐይ ሃይል የሚሠራ የሶላር ኃይል ማመንጫ አገልግሎት አስጀመረ።
****************
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህብረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት YOLK ከተባለ ከደቡብ ኮሪያ ድርጅት ጋር በመተባበር በምዕራብ ጉጂ ዞን በሀምበላ ዋመና ወረዳ የኤሌክትርክ ኃይል ካልተዳረሰባቸው ት/ቤቶች አንዱ በሆነዉ ጮርሶ ሶዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በፀሐይ ኃይል የሚሠራ ሶላር ዲሽ በመግጠም ትምህርት ቤቱንና ማህብረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት የግብረሰናይ ሥራን ለመሥራት ‹‹SOLAR COW››የሚል መጠሪያ ካለው ሌላ ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ተፈራርሞ ወደ ስራ እንደገባ ታውቋል።
የሶላር ኃይል ማመንጫው ሊገሳ ዋናው ዓላማ የተማሪዎችን መጠነ ብክነት ለመቀነስ፣የአከባቢው ማህበረሰቡና ቤተሰቦቻቸው በማታ የመብራት ሃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ሆኖ በሌላ በኩል የትምህርት ጥራትንም ለመደገፍና ማሻሻል ላይ ያተኮረ ነዉ።

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.bhu.edu.et/
ቴሌግራም -https://t.me/BuleHoraUniversity
ፌስቡክ - https://facebook.com/BuleHoraUniversity
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ


ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም (BHU)
በዩኒቨርሲቲዉ የአካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት እና  በኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ዲን የተመራውና እንድሁም በኮልጁ ስር ከሚገኙ ከተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ጋር በመሆን ጉብኝት  ተካሄደ።
**************
በጉብኝቱም ወቅት የዩኒቨርሲቲዉ አካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገበየሁ አሻግሬ  እና የኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ዲን መ/ር ቦሩ በዴያ እንዲሁም የኮሌጁ የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች መምህራን በተገኙበት የተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ተጎብኝተዋል።

የጉብኝቱም አላማ በኮሌጁ የሚገኙ የትምህርት ክፍሎች አሁናዊ ሁኔታዎችን መፈተሽን ዓላማ ያደረገ  ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው ጠንካራውን በምን መልኩ ማሰቀጠል እንዳለባቸውና እንድሁም እንደ ክፍተት የታዩትን ደካማ ጎኖች ደግሞ  እንዴት  ማሻሻል አንደሚቻል አቅጣጫ ያስቀመጡበት ሁኔታ የተፈጠረ ሲሆን፣በተጨማሪም በዘለቄታነት የኮሌጁን ችግሮች መፍታትና የትምህርት ጥራት ላይ በማተኮር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ በማፍራት ዓላማው እንዲቀጥል አቅጣጫ ተቀምጦ ጉብኝቱን አጠናቋል ።

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ






ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም (BHU)
በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የፀረ-ጾታ ጥቃት፤የፀረ-ኤድስ እና የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከበረ፡፡
**********************************
በዚህ አመት የፀረ-ፆታ ጥቃት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ ‹‹የሴቷ ጥቅት የእኔም ነዉ ዝም አልልም! ›› በሚል መሪ ቃል፤ በሌላ በኩል የፀረ-ኤድስ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ36ኛ ጊዜ ‹‹ሰብዓዊ መብት ያከበረ ኤች አይ ቭ አገልግሎት ለሁሉም!›› እንዱሁም የአካል ጉዳተኞች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ32ኛ ጊዜ ‹‹የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታችና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ!››በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲዉ የሥራ ኃላፊዎች ፤ሰራተኞችና ተማሪዎች በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች ታጅቦ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡
በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ምርምር፤ስርፀትና ሥነ ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር አብነት በቀለ ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች በተሻለ መልኩ የተለያዩ ሰብዓዊ መብቶች እንዳይጣሱ የሚጠበቁበት አካባቢ ቢሆንም አሁንም መሻሻል ያለባቸዉ እንደ ፆታዊ ጥቃት ዓይነቱ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየታዩ መሆናቸዉን በመጥቀስ ይህን መቅረፍ የሚቻለዉ በትምህርትና በእንደዚህ ዓይነት የሥርዓተ ጾታ በኩል በሚዘጋጁ መድረኮች ላይ በመገኘት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨባጫ ሥራዎችን በመሥራት መሆኑን አስረድቷል፡፡

ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ



6 last posts shown.