Neway Debebe — Alwashim
ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለሁ
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ እተክዛለሁ
ውብ ጨዋታና ሳቅሽን አስታውሼ
እህ እላለሁ እተክዛለሁ አስባለሁ አስባለሁ
እንግዲያው አንቺም ከተለየሽ ከራቅሺኝ አስታውሺኝ
በፍቅር ከደበቅነው አንጀት ከሆድሽ ውስጥ አታውጪኝ
እንዳልረሳውሽ አደራ አንቺም አትርሺኝ አስታውሺኝ
ፍቅሬ አስቢኝ አስቢኝ አስታውሺኝ
እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
እንደምነሽ እንደምነሽ
ከተሰናበትሽኝ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ
እጠብቅሻለሁ መች ትመለሻለሽ
ለብቸኝነቴ ለብቸኝነቴ ላዲሱ እንግዳዬ
ትካዜ ብቻ ነው መስተናገጃዬ
እንደምነሽ ብዬ ሁሌ አስብሻለሁ
በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለሁ
በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለሁ
የኔ ፍቅር
በቃልኪዳን ፅናት እጠብቅሻለሁ
አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ
አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ
አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ
ሲነጋ አሰብኩሽ
አልዋሽም እኔ አልዋሽም
የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም
ከቆምንበት ቦታ ቆሜ አንቺን አስባለሁ
ቁጭ ብለን ካወጋንበት ቁጭ ብዬ እተክዛለሁ
ውብ ጨዋታና ሳቅሽን አስታውሼ እህ እላለሁ
እተክዛለሁ አስባለሁ አስባለሁ
እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
እንደምነሽ ኧረ እንዴት ነሽ
ከተሰናበትሽኝ ከሄድሽ እኮ ቆየሽ
እጠብቅሻለሁ መች ትመለሻለሽ
ናፍቆትሽ በዓይኔ ላይ
ናፍቆትሽ በዓይኔ ላይ ከተመላለሰ
የፍቅር እመቤቴን አንቺን ካስታወሰ
እንደምነሽ ብዬ አስታውስሻለሁ
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለሁ
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለሁ የኔ ፍቅር
ጤና ሰላምሽን እመኝልሻለሁ
አልዋሽም ስበላ አሰብኩሽ
አልዋሽም ስጠጣ አሰብኩሽ
አልዋሽም ሲመሽ አሰብኩሽ
ሲነጋ አሰብኩሽ
አልዋሽም እኔ አልዋሽም
የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም
አልዋሽም እኔ አልዋሽም
የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም
አልዋሽም አልዋሽም
የእምነት የእውነት ቃሌን ክጄ አላበላሽም
@DJKIAbot