Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


#STEM_Training

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመደበኛው ፕሮግራሞች በተጨማሪ ውጤታማ እና ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ተማሪዎች ከመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመመልመል በተለያዩ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ (ሳ.ቴ.ም.ሂ) - Science, Technology, Engineering and Mathematics (STEM) ፕሮግራሞች የንድፈ ሃሳብና የተግባር ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፡፡

በዚሁ መሠረት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት የ2017 ዓ.ም የበጋ መርሀ ግብር ቡድን አንድ STEM ሰልጣኞችን በSTEM ስልጠና ማዕከል አስጀምሯል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ


#ማስታወቂያ

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሐ ግብር በPost-basic BSc in Midwifery የመጀመሪያ ዲግሪ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም፦

1. በሚድዋይፈሪ ዲፕሎማ ወይም ደረጃ IV የለው/ያላት እና COC ፈተና ያለፈ/ች፤

2. ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው/ያላት፤

3. የመግቢያ ፈተናውን ተፈትኖ/ተፈትና ማለፊያ ነጥብ መምጣት የሚችል/የምትችል፤

4. ስፖንሰርሺፕ ማቅረብ የሚችል/የምትችል ወይም በግል መክፈል ሚችል/የምትችል፤

5. የድጋፍ ደብዳቤ (Recommendation letter) ማቅረብ ሚችል/የምትችል፤

አመልካቾች ከታኅሳስ 21 እስከ ጥር 2/2017 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን።

#ማሳሰቢያ

 የማመልከቻ ቦታ፡ በዋናው ግቢ የህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ ቅ/ረጅስትራር (ህንጻ 26፣ ቢሮ ቁ. 5/Ground)

 የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን: ጥር 15/2017 ዓ.ም

 አመልካቾች ከላይ የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ዋናውን እና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ በአካል ወይም በተወካይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

በመጨረሻም ምዝገባውን በ http://www.dmu.edu.et/Online-Application-form/ በመጠቀም መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።


#ማስታወቂያ

ለአዲስ የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈታኞች በሙሉ፤

በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ2ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የመግቢያ ፈተና (NGAT) ከጥር 07/2017 ዓ.ም እስከ ጥር 09/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልፆልናል፡፡ በመሆኑም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል በመደበኛ ኤክስቴንሽን እና ክረምት ፕሮግራም ለመፈተንና ለመማር ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ይህንን አውቃችሁ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡

#ማሳሰቢያ

💠ለዝግጅት የሚያግዙ ማቴሪያሎች በቴሌግራም ቻናል DMU college of postgraduate studies ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
💠የአንድ ጊዜ ፈተና ውጤት ለሁለት ዓመት ማገልገል ይችላል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ #ድህረ_ምረቃ_ኮሌጅ






#ማስታወቂያ!

የደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ #አዲስ_የአገልግሎት_የምዝገባ_ጊዜን እንደሚከተለው አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ለነባር የጅምናዝየም የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 08/2017 ዓ.ም ድረስ ሲሆን ለአዲስ የጅም ደንበኞች ደግሞ ከታህሳስ 03/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 13/2017 ዓ.ም ድረስ መሆኑንና ከስልጠናው በተጨማሪ የአካል ብቃትና ጤና የማማከሪያ ማዕከል ስራ ስለጀመረ ማንኛውም የግቢና የአካባቢው ማህበረሰብ መጠቀም የምትችሉ መሆኑን በደስታ እናሳወቃለን።

ለበለጠ መረጃ በ +251913874867 ደውለው ይጠይቁ!

የደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ ስፖርት ሳይንስ አካዳሚ


Call for project proposals


A PhD Public Defense

Join us for two thought-provoking presentations at our upcoming public defense event!

#Endalamaw_Abatihun will delve into the impact of problem-based learning on students' writing, critical thinking, and problem-solving skills. #Yigzaw_Kerebih will share insights on the experiences of EFL teacher educators in self-directed professional learning.

Save the date: 25/3/2017 (Local time) at Nigiste Saba Hall.





10 last posts shown.