ደሴ ታይምስ®️ - ወሎ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Other


ቻናላችን በዋናነት
🏜በወሎ ከተሞች እና ወረዳዎች
🏜በኦሮምያ ልዪ ዞኖችን የሚከናወኑ ሁነቶች ላይ የምናተኩር ሲሆን
........ በተጨማሪም........
🌍 ለየት ያሉ አለምአቀፋዊ እና የጦር ግንባር መረጃወችን በአፋጣኝ ከታማኝ ምንጮች በዚ ቻናል ያገኙበታል።
''የወሎየዎች ድምፅ ያለወገንተኝነት''
ባለቤት @Dessieowner

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Other
Statistics
Posts filter


ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ…‼

ከከሚሴ እስከ ሸዋሮቢት ያለው ዋና መስመር የፀጥታው ሁኔታ ከባለፉት ቀናት ትናንትና ዛሬ የነበረው ሂደት ሠላማዊ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ከሰሞኑ በሰሜን ሸዋ ኤፍራታና ግድም አርሷምባ፣ ማኛ፣እና በረሀ በተባሉ ቀበሌዎች እንድሁም በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በጤ እና መሰል አካባቢዎች ተከስቶ የነበረው ግጭት ቆሞ የህዝብ ውይይት መካሄድ ጀምሮ ነበር።

ነገር ግን ዛሬ በግምት ከምሽቱ 12:20 ሲሆን በቀጠናው የተኩስ ልውውጥ ድምፅ መሰማቱን ነዋሪዎች ለወሎ ቲቪ ተናግረዋል።በአካባቢው በቂ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የሚገኙ ሲሆን የምሽቱ የተኩስ ልውውጥ መነሻው ምን እንደሆነ በግልፅ የታወቀ ነገር የለም።

Via wello tv
🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


Forward from: ደሴ ታይምስ Promo
የማስታወቂያ ሰአት 🔈

ለሽያጭ የቀረቡ ኢቦላ ባጃጆች

1, ታርጋ:31ሺ

ዋጋ..180ሺ

2, ታረጋ:28ሺ

ዋጋ..170ሺ

3, ታርጋ:32ሺ

ዋጋ..195ሺ

4, ታርጋ:32ሺ

ዋጋ..265ሺ

ይደውሉ☎️ +251915776714

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob


መብራትን በተመለከተ ከከንቲባችን❕

ደሴ :ሐምሌ 7-11-2014

በከተማችን እየተስተዋለ ያለው ልክ የሌለው የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግር የሀይል አቅርቦት እጥረት መሆኑን ለማስረዳት እና አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው ዘንድ ከኢትዬጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ስራ አስፈፃሚዎች ጋር አዲስ አበባ ዋናው መስሪያቤት ፍሬማ ውይይት አካሂደናል።

በሀገራችን ጥንታዊና ከፍተኛ ቁጥር ያለባቸው ሰፊ ከሚባሉት ከተሞች አንዷ የሆነችው የደሴ ከተማ ያላት የዱሮ 66 KV ኃይል በመሆኑ እጅግ አስቸጋሪ የሆነ የኤሌክትሪክ ኃይል ችግር ገጥሟታል ለዚህ ደግሞ የከተማዋን ዕድገት ያገናዘበ አዲስ ከፍተኛ አቅም ያለው ፓወር ስቴሺን ለመገንባት ስትራቴጅካዊ መፍትሄ ሳይቀመጥላት እስካሁን መቆየቱ ተገቢ አለመሆኑን ለማስረዳት ተሞክሯል። በመሆኑም በከተማችን የኃይል እጥረት ከመኖሩ ጋር በተያያዘ ማህበረሰቡ በእጅጉ መቸገሩን ፣ ሸድ ተሰርቶላቸው የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ማምረት አለመቻላቸውን፣ ሆቴሎች መስራት ባለመቻላቸው ዘርፍ እስከመቀየር እየደረሱ መሆኑን፣ የኃይል አቅርቦት ችግር በመኖሩ ከተማው ኢንቨስተሮችን ለመሳብ አለመቻሉን በአጠቃላይ የከተማዋን ሁለንተናዊ የልማት ዕድገት እየገታ መሆኑን በማንሳት ጠንካራ ውይይት አካሂደናል። በመጨረሻም ችግሩ ልክ መሆኑን መግባባት ላይ ተደርሷል። የከተማ አስተዳደራችን ለፓወር ስቴሺን መገንቢያ ቦታ (Site) ያዘጋጀን ሲሆን እንደተጠየቀ ለማመቻቸት ቁርጠኛ መሆናችን የካሳ ግምት ሂደቶችን አፋጥኖ ሰርቶ ለማሳውቅና ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናችን አስቀምጠናል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩልም የችግሩን አሳሳቢነት ተረድተው አሉ የተባሉ አማራጮቾን ሁሉ ተጠቅመው አዲስ 230 KV ፓወር ስቴሺን መገንባት እንዳለበት አስቀምጠዋል ትልቅ ቁርጠኝነትም አሳይተውናል። የገቡልን ቃል ለመፈፀም እየሰሩ መሆኑን በተግባር ማስተዋል ጀምረናል። ቀድሞ ተጀምረው የነበሩ የጥናት ስራዎችን ማጠናቀቃቸውን ከውይይት መልስ በኋላ በስልክ ሊያሳውቁን በመቻላቸው ስራ ውስጥ መሆናቸውን ተረድተናል ። ይህን ችግር በማስረዳት በኩል ጧት ማታ ከዋና መስሪያቤቱ ባለመነጠል የወከሉትን ህዝብ ጥያቄ በአካል በማስረዳት እያገዙን ለሚገኙት የህዝብ ተወካዮቻችን እናመሰግናለን።

Via: የከተማችን ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


የዛሬ ሐሙስ - ሐምሌ 7-11-2014 መረጃዎች


እንኳን ደስ አለህ!

ደሴ :ሐምሌ 7-11-2014

ሮፍናን - ከዩኒቨርሳል ሚዩዚክ ግሩፕ ጋር በመፈራረሙ ዓለም አቀፍ ስኬቱን በማድነቅ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲየ"እንኳን ደስ አለህ" መልእክት አስተላልፎለታል።

U.S. Embassy Addis Ababa
We congratulate Ethiopian artist Rophnan on his international success, including the drop of his latest album and his recent contract with Universal Music Group!

Rophnan - That's awesome! Congratulations!

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


የደሴ ታይምስ ቤተሰቦች ተጋበዙልን

🔊 ደሴ

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​👤 ሮፍናን

⌚️ 0:00 - 4:30

📍8.2MB

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


የደሴ ታይምስ ቤተሰቦች እስከነ ግጥሙ ተጋበዙልን

🔊 ደሴ

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​👤 ሮፍናን

👉ግጥም:

ደሴ መጀን

ብለን መተናል
ውድ ለብሰናል

አመት ደርሰናል
ወርቅ ለብሰናል

እስኪ በይ እስኪ
ከፍቅርሽም አስነኪኝ

ነይ አይናለሜ

አንቺ ካለሽ ሁል ግዜ ቀኑ
በዓል ነው
ጠቡም ሰርጋም ክፉም ውጪ
ዳር ነው
ያልጣፈጠኝ ኮሶ እሬቱም
ማር ነው
ካንቺ የሚለየኝ ኧረ ማነው
ተይ ማነው?

ተራራው አምባሰል
ሀገሩም ደም ደሴ
ሀገሩም ቆቦ
ውሃም ከሚሴ
ውሃውም ሐይቅ ነው
ውሃውም ገራገር
እኔ የከተማ ሰው
መሃል ሀገር ሸገር
በሸገር ሸገር
ምን አለ በሸገር
ሀገር ስጠኝ ካልሺኝ
ዋ ብዬሽ እንዳልቀር
ዋ ብሎኝ የቀረው ልጅ
ብለሽ ብታሚኝ
ሀገር ያውቃል አንቺም
ደሴን አትሰጭኝ

Jaallee koo
Qabii laphee koo
Garaa koo
Beektaa qalloo koo
Jaalalti kee damma
Dammee ko
Taate yaada koo
Taate maarree
Takkittii kan koo
Qubee koo
Afaan koo

እስካገኝሽ ሳልምሽ
ካንቺ በር ደርሼ እንዳልስምሽ
ወግ አይደለም በሀገር ሳልክስሽ ጥሎሹን ሳልችልሽ
ወርቅ እንደ ጃኖ ሳልደርብሽ
እኔን ልሸልም አይደለም ወይ
ለምነው ምትይኝ ቆይ
ምትግደረደሪው
መውደድሽ እንድ እርቦኝ
ሰሚ እንኮይ
የፍቅር ሀገር ደሴ አይደለም ወይ

ብለን ሞተናል
ውድ ለብሰናል

አመት ደርሰናል
ወርቅ ለብሰናል

እስኪ በይ እስኪ
ከፍቅርሽም አስነኪኝ

ነይ አይናለሜ
አንቺ ካለሽ ሁል ግዜ ቀኑ
በዓል ነው
ጠቡም ሰርጋም ክፉም ውጪ
ዳር ነው
ያልጣፈጠኝ ኮሶ እሬቱም
ማር ነው
ካንቺ የሚለየኝ ኧረ ማነው
ተይ ማነው?

Low low low low
ዝቅ ዝቅ ዝቅ
ደግሞ ከፍ
ከፍ ከፍ ከፍ ከፍ
መልሽ መልሽ
ደሞ
Low low low low
ዝቅ ዝቅ ዝቅ
ደሞ ወደላይ
ከፍ ከፍ ከፍ
መልሰኝ

የሀገሬ ሰው ሸላይ ነው

ይታያል ገና

ደሴ ላይ ደስ አለኝ አገኘሁ መላ
ውብአለም ይላታል ለቤቷም ጥላ

በይልኝ ዘና ደና
ጥርሷም ይረቃል
ጉራማይሌ ንቅስ ያንፀባርቃል
እስክስ ይደቃል

ካንገቷ ንቅል አይኗም ይሰርቃል
ከተራራው ጠፍ
ከቤተመንግስት ቆሜ አይጠየፍ
ባየው ከሚሴን
በንጉሥ ፈረስ ደሴ ላይ ከተፍ
ሚካኤል ንጉሥ አለች
ሰርቃ ብታየኝ ደንግጣ በስሙ ማለች
በእሪኩም የተሳመች
የመልኳ ሳያንሳት ማርዳዋን በአንገቷ አዋለች
ምን ታየኛለህ አቦ
በል እሪኩም
ግጠመኝ ያዝ አትቁም
ደሴ ገራገር አለም ባቲ አምባሰል
ስጠኝ የውበት ጥጉን
ላሊበላ ልሳለም እመጣለሁ ገና አዬ
ወሎ መጀን
ሰላምሽ ይብዛ ይልሻል ሮፍናን
እዬዬዬ
ወሎ መጀን
ደሴ መጀን
ወሎ መጀን
ደሴ መጀን

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ፤ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ!

ደሴ :ሐምሌ 6 -11-2014

የብልፅግና ተመራጭ እና የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ ዕጩ ዶክተር ዮናስ ዘውዴ ከኃላፊነታቸው በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸውን ከታማኝ ምንጭ አረጋግጫለሁ።

የመረጃ ምንጬ የለቀቁበትን ምክንያት ሲያብራሩ አገዛዙ በሙስና የተዘፈቀ እና ለአገሪቱ መጻኢ ተስፋ የማያስብ በመሆኑ ከዚህ ሥርዓት ጋር ለመቀጠል ስለከበዳቸው መልቀቃቸውን ገልጸውልኛል።

Via:Mulugeta Anberber

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


በሸገር የተያዙት የኮንዶሚኒየም ሌቦች

ደሴ :ሐምሌ 6 -11-2014

ከ14ኛ ዙር የ20/80 እንዲሁም ከ40/60 3ኛ ዙር እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮና የቤቶች ቢሮ የተለያየ እርምጃ የተወሰደባቸው

አመራሮችና ባለሙያዎች ስም ዝርዝር

1ኛ. ዶ/ር ሙሉቀን ሃብቱ ቢሮ ሃላፊ ከሃላፊነቱ የተነሳ

በቁጥጥር ስር የዋሉ፡-

1ኛ. አብርሀም ሰርሞሎ የዘርፉ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

2 ኛ . መብራቱ ወልደኪዳን :_ዳይሬክተር

3ኛ. ሀብታሙ ከበደ :_ሶፍትዌር ባለሙያ

4ኛ. ዬሴፍ ሙላት :_ሶፍትዌር ባለሙያ

5ኛ. ጌታቸው በሪሁን :_ሶፍትዌር ባለሙያ

6ኛ. ቃሲም ከድር :_ሶፍትዌር ባለሙያ

7ኛ. ስጦታው ግዛቸው :_ሶፍትዌሩን ያለማ

8.ኛ. ባየልኝ ረታ ፡_ሶፍትዌር ተቆጣጣሪ

9ኛ. ሚኪያስ ቶሌራ ፡_የቤቶች ኢንፎሜሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያ

10ኛ .ኩምሳ ቶላ ፡_ የቤቶች ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዳሬክተር

በቀጣይም ሂደቱን እየተከታተልን ለህዝባችን ማድረሳችንን የምንቀጥል ይሆናል፡፡

Via Mayor Office of Addis Ababa

አስተማሪ ቅጣት እንጠብቃለን

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


ቁራሊዮ ቢዝነስ ቢሆንም ለህዝብ ህይወት ስጋት ግን ሊሆን አይገባም።

ደሴ :ሐምሌ 6 -11-2014

ከከተማ መሀል ሊወጡ ግድ ነው።

ትናንት ማለትም በ 5/11/2014 በከተማችን ሳላይሺ አካባቢ የፈነዳው ቁራሊዮ በመኪና ጭኖ ከምዕራብ አቅጣጫ ወደ ከተማው በማስገባት የገባውን ቁራሊዮ በማዳበሪያ የተጫነውን በሚዛን እያስመዘኑ በማሰባሰብ ላይ ባሉበት ሲያነሱ ሲጥሉ ቁራሊዮ ተብሎ ከተቆጠረው ማዳበሪያ ውስጥ ቦንብ F1 አብሮ ተቆጥሮ በመገኘቱ ፈንድቶ በጎችን ገድሏል ሰዎችን አቁስሏል አንድ ሰው ከባድ ጉዳት ደርሶበታል። እስካሁን የሞተ ሰው አልሰማንም። የፈነዳው ነገር በፀጥታ ሀይል እንድጣራ ተደርጎ ስለተገለፀልን ነው። ከዚህ የምንረዳው በቁራሊዮ ስም የጦር መሣሪያ ማንቀሳቀስ ስራ እየተሰራ መሆኑን ነው። ስለሆነም ቁራሊዮ ከከተማ መሀል እንድወጣ ይደረጋል የምርመራና ፍተሻ ስራም ይሰራል።

በሌላ መልኩ ከወር በፊት አራዳ ሸርፍ ተራ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት ቁራሊዮ አብሮ ተሰብስቦ የነበረው የጦር መሠራያ ቅሪቶች እየፈነዳ ሰው መጉዳቱ ይታወሳል።

በቁራሊዮ ስራ የተሰማራችሁ ወገኖች ለህዝብ ደህንነት ሲባል ከመሀል ከተማ መውጣት ይኖርባችሗል። ካልሆነ ግን ከተማ አስተዳደሩ ለህዝብ ደህንነት ሲባል ህግ ያስከብራል።

Via: የከተማችን ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ በነበረው የሰላም ችግር በተመለከተ የሰሜን ሸዋ ዞኖች የስራ ኃላፊዎች በህግ ሊጠየቁ ይገባል።

ደሴ :ሐምሌ 6 -11-2014

ከዚህ ጥቃት ጀርባ የአካባቢ አመራሮች ጭምር አስተባብረዋል የሚሉ አመላካች መረጃዎች እየወጡ ነው።

ከምክንያቶቹ መካከል:

- በአንዳንድ ዞኖች አቅራቢያ በሚገኙ ጫካዎች ውስጥ ለኦነግ ሰሪዊት ስልጠና ሲሰጥ የተመለከቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ጥቆማ የሰጡ ቢሆንም በቸልተኝነት መታለፉ

-ሰላም ለማስከበር የተላኩ የልዩ ሀይል አባላት የፌዴራል ባንዲራ ይዘው በገቡ እና ዩኒፎርም በለበሱ የኦነግ በኣባላት ባልጠበቁት ሁኔታ በወጋቻው

-አንዳንድ ባለስልጣናትም በተንቀሳቃሽ ምስሎች ላይ በመታየታቸው

የግድ መመርመር አለባቸው

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


#UPDATE

ወለጋ❗️

ደሴ :ሐምሌ 6 -11-2014

ታጣቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃንን ከጨፈጨፉበት ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች መንግሥት እስካሁን ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳልሰጣቸው መናገራቸውን ዶይቸቨለ ዘግቧል። መቻራ በተባለች ከተማ ለተጠለሉት ተፈናቃዮች ባሁኑ ወቅት እርዳታ እያቀረበ የሚገኘው የአካባቢው ሕዝብ ብቻ ነው። የክልሉ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን ግን 24 ሺህ ያህል ለሚሆኑት ተፈናቃዮች የእርዳት ቁሳቁሶችን እያጓጓዘ መሆኑን አስታውቋል።

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


የዛሬ ዕረቡ - ሐምሌ 6-11-2014 መረጃዎች


#UPDATE

ወለጋ የቀሩት አማሮች❗️

በቄለም ወለጋ ዞን በሑሉም ወረዳወች ያሉ አማራወች ማለትም በ1977 ዓ.ም በሰፈራ የሔዱ አማራወች ጋር ከትላንት በስተያ በቀን 3/11/2014 የመከላከያ ጄኔራሎች ጋር ውይይት አድርገዋል::

በውይይቱ ላይ ከሕብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄወች:
👉የንብረት ካሳችን መንግስት ይክፈለንና ወደ ትውልድ ሐገራችን ይመልሰን
👉እስከምንመለስ እንዳናልቅ ጥበቃ ይደረግልን : የኦሮሚያ ባለስልጣናት ከዞን እስከወረዳ ጥበቃ እያደረጉልን አደለም ወደፊትም አያደርጉልንም በማለት በአብዝሃኞቹ ቀበሌዎች ተጠይቋል::

ከጀኔራሎቹ የተሰጠ መልስ :

👉መንግስት ወደ አማራ ክልል አይመልስም ግን ባላችሑበት ጥበቃ ያደርግላችሗል
👉የሆነ ያልሆነውን ለሚድያወች አታራገቡ : ፎቶ አታንሱ : ቪድዮ አትቅረጹ : ወደ ወሎም መሔድ አይቻልም : ወደከተማም እዛው አካባቢ ተከራይቶ መኖርም አይቻልም : አርፋችሁ ተቀመጡ የሚል ነው::

Via:Roha news & አካባቢው ካሉ የወሎ ተወላጆች

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


በከተማችን ደሴ የተከሰተውን ፍንዳታ በተመለከተ የሞቱ ሰዎች እንዳሉ አሁን ያገኘኋቸው መረጃዎች ያመላክታሉ

ደሴ :ሐምሌ 5-11-2014

ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ከነበሩ ተጎጅዎች ውስጥ የሞቱም እንዳሉ ለማወቅ ችያለሁ።

ከሟቾቹም መካከል የቀን ሰራተኞች እና በግ ለመግዛት በአካባቢው የነበሩ ግለሰቦች ሊኖሩ እንደሚችሉ በፋንዳታው ወቅት በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ሃሳባቸውን ገልፀውልኛል።

እስካሁን ድረስ በፍንዳታው 3ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ መረጃው አለኝ።

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


ዛሬ በደሴ ከተማ የተከሰተው ፍንዳታ በምስል

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


የአጣዬ ዙሪያው ጥቃት!

ደሴ :ሐምሌ 5-11-2014

የኦነግ ሸኔን ጥቃት ተከትሎ በኤፍራታ ግድም ወረዳ ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት ጋብ ማለቱን ነዋሪዎች ገለጹ!

ከቅርብ አመታት ወዲህ ግጭት እየበረታበት ፣ ንጹሃን በግፍ እየተገደሉበት ፣ ለዘመናት ተለፍቶበት የፈራ ሃብት ንብረት እየወደመበት ፣ አለፍ ሲልም ከተማን ያህል ነገር “ነበር” በሚል እስኪቀር የሚጠፋበት የጦርነትና ግጭት ቀጠና እንዲሆን ተደርጓል፤የሰሜን ሸዋ ዞኑ ኤፍራታ ግድም ወረዳ፡፡ወረዳው አንዴ ከሚያጎራብተው የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የሚነሱ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎቹ ሲያወድሙት በሌላ ጊዜ ደግሞ ወራሪው ህወሃት ሲዘርፈው የከረመ ብሶተኛ ወረዳ ነው፡፡

ከሰባት ጊዜ በላይ ጥቃት እንደተፈጸመበት የሚነገረው ይህ ወረዳ ከዚህ ቀደም በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተፈጸመበት ወረራ የወረዳ መቀመጫዋን አጣዬን ጨምሮ በርካታ ቀበሌዎች ለጆሮ በሚከብድ ሁናቴ ወድመዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ ደግሞ በዚህ ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ላይ ይሄው ሽብርተኛ ቡድን ጥቃት መፈጸሙን የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርገን ትናንት መዘገባችን ይታወቃል፡፡

በትናንቱ ዘገባችንም ከባድ መሳሪያ የያዙት የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የጀመሩትን ጥቃት ለማስቆም በገባው የአማራ ልዩ ሃይል ላይ ከትናንት ጠዋት ጀምሮ ተኩስ መክፈታቸውን ዘግበን ነበር፡፡በዚህም ቤፍራታ ግድም ወረዳ በአርሶ አምባ /ዘምቦ/ና አጎራባች ቀበሌዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች አካባቢያቸውን ለቀው እየወጡ እንደነበር ነዋሪዎቹ ገልጸውልን ነበር፡፡የተኩስ ልውውጡም እስከምሽት ድረስ መዝለቁን ሰምተን ነበር፡፡

አዳሩንና ዛሬ በአካባቢው ስላለው ሁኔታ በስልክ የጠየቅናቸው የአካባቢው ነዋሪ እንደነገሩን ደግሞ ሃይል መጨመሩንና አካባቢው አሁን ከተኩስ ድምጽ ነጻ መሆኑን ነግረውናል፡፡ ነዋሪው አክለውም ይህ ማለት ግን ታጣቂ ቡድኑ ጥቃት አያደርስም ማለት እንዳልሆነና በህዝቡም ሆነ በመንግስት በኩል ጥንቃቄ የግድ መሆኑን አስረድተዋል። ምክንያቱም ቡድኑ ከዚህ ቀደምም እንዲሁ እያዘናጋ ውድመቶችን ያደርስ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


በደሴ ከተማ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

ደሴ :ሐምሌ 5-11-2014

በደሴ ከተማ በተለምዶ ሳላይሽ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተከሰተ ፍንዳታ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በደሴ ከተማ የ3ኛ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር አለባቸው መለሰ ለኤፍቢሲ እንደገለጹት ዛሬ 5 ሰዓት ከ30 ላይ ሳላይሽ በግ ተራ አካባቢ የቆራሌ ዕቃ በሚራገፍበት ሰዓት ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ነገር ፈንድቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፡፡

በፍንዳታው በግ ሲገዙ የነበሩ ሰዎችና የቀን ሠራተኞች ላይ ጉዳት መድረሱ የተገለጸ ሲሆን ተጎጂዎችም ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የፖሊስ መረጃ እንደሚያመላክተው እስካሁን ድረስ ከ31 በላይ ሰዎች ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ከ15 በላይ በቦታው ለሽያጭ የቀረቡ በጎች ሞተዋል።

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


አርሶ አምባ ቀበሌ❗️

ደሴ :ሐምሌ 5-11-2014

አርሶ አምባ በምትባል ቀበሌ በአርሶ አደሮች ሰብል ላይ ከብቶች መለቀቃቸውን ምክንያት በማድረግ የተጀመረው ይህ ጦርነት በትናንትናው ዕለት ወደ መንተኬ ሸረፋ ወደምትባል ቀበሌ ተስፋፍቷል።

የቀበሌው አስተዳዳሪ አቶ ካሳዬ ክብረት እንዳሉት በትናንትናው ዕለት ምሽት ላይ ከጅሌ ጥሙጋ ቀበሌዎች የመጡ ታጣቂዎች ከ400 በላይ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ተናግረዋል።

በስፍራው እስካሁን የመጣልን የጸጥታ ሀይል የለም የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎችን አስከሬን ማንሳት እንዳልቻሉም ገልጸዋል።

በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ሞተዋል? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄም "እስካሁን አራት ሰዎች ሞተዋል አራት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፣ የት እንዳሉ እና ይሙቱ ይቁሰሉ ያላወቅናቸው ሰዎች አሉ" ብለዋል።

እነዚህ ታጣቂዎች ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ጥቃት አድርሰውብን ነበር የሚሉት አስተዳዳሪው መንግስት ለቤት መስሪያ በሚል የሰጠንን የቤት መስሪያ ቆርቆሮዎችን እና የቤት እንስሳቶቻችን ሁሉ ዳግም ተዘርፈዋል ብለዋል።

የሞቱ ሰዎችን እንድንቀብር እና ሌላ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ መንግሥት የጸጥታ ሀይል እንዲልክላቸውም አስተዳዳሪው ጠይቀዋል።

የአርሶ አምባ ቀበሌ አስተዳዳሪ አቶ ማሞ ማስረሻ በበኩላቸው እስካሁን ሰባት ሰዎች ከጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ቀበሌዎች በመጡ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና 150 መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እንዳረጋገጡ፣ የተወሰኑትን ሟቾች ስርዓተ ቀብር እንደፈጸሙ ገልጸው ቀሪዎቹን አስከሬን ማንሳት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

አዳሩን ጦርነቱ ጋብ ቢልም ዛሬ ጠዋት ጀምሮ ብዙ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ወደ አርሶአምባ ቀበሌ በመኪና እየመጡ መሆኑንም አስተዳዳሪው ገልጸዋል ።

የታጣቂዎቹን ጥቃት አርሶ አደር ሚሊሻዎች ለመመከት እየሞከሩ ቢሆንም የታጣቂዎቹ ቁጥር እና የታጠቁት መሳሪያ የማይመጣጠን ነው፣ ጉዳዩን ለዞን እና ለወረዳ ብናሳውቅም ተጨማሪ የመንግስት ጸጥታ ሀይል አልመጣልንም ሲሉ ነግረውናል።

Via:አዲስ ነጋሪ

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes


በአጣዬ አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማስቆም የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት በሥፍራው መድረሳቸው ተነገረ

ደሴ :ሐምሌ 5-11-2014

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ ቀበሌዎች ከትናንት በስትያ ጀምሮ የተቀሰቀሰውን ግጭት ለማስቆም የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት በሥፍራው መድረሳቸው ተነግሯል።

ከሸዋሮቢት እስከ ኬሚሴ ያለውን አካባቢ ሠላም ለማስጠበቅ የአማራ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያለው የፀጥታ ኃይል ማሰማራቱ ታውቋል።

🧔‍♂➤ @Dessieowner

ደሴ ታይምስ®️➤ @DessieCity

ወሎየ ስራዎች®️➤ @Wollojob
ፌስቡክ ፔጅ :
↪️ www.facebook.com/DesieTimes

20 last posts shown.

10 667

subscribers
Channel statistics