♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Books


☞ የስብህና ልቀት ለማምጣት ከመፃህፍት ጋር እናዉጋ
☞ በዚህ ቻናል ተወዳጅ የሆኑ ግጥሞችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይቀርቡበታል
ለሃሳብ አስተያዬታች
@Almnu6
@Almnu6
መነጋገር ይቻላል
ገጣሚ ማለት በአጭረር አነጋገር እረጅም ሃሳብን መግለፅ ነዉ፡፡

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Books
Statistics
Posts filter


ድካም ሲበረታ ሰው ተስፋን ሲናፍቅ፤
እኔን ነው ሚመስለኝ
ለደስታ ላይበቃ
ሀዘን ነገን አምኖ ዛሬው’ን የሚፍቅ፡፡
ደሰ


በስልክ ችግር ነው የጠፋሁት ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች አሁን ባለሁበት ሁኔታ ስልክ የሚያውሰኝ ካላግኘው ትግስታችሁ አይለይብኝ እስከዛ መፅሃፍ የሚያውሰኝ ካለ ቢያንስ በሱ ልፅናና ስል በጓደኛዬ ስልክ ፃፍኩላችሁ ለሃሳብ አስተያዬታችሁ
👇👇👇👇👇
@Almnu6
@Almnu6
ፃፍልኝ ደሱ ነኝ🙏🙏🙏🙏🙏


እርዳታችሁን እሻለሁ (10) ሰው አለን ካለኝ በውስጥ መልክት እልካለሁ


የምር የስልክ እጦት ሊያሳብደኝ ነው!


ድንገት በአይኔ ገብተህ
ወንዳወንድነትህ
ገራገር ልቦናህ
ልቤን ቢያሸፍተው፣ወዳንተ እንዲመንን፣
ሊደበቅ በጉያህ፣ሊፍቅ ላጤነትን፣
አንተ ግን ሸሸኸው
ያመነህን ልቤን በእሾ ድር አነቅከው፣
መራመድ እንዳይችል፣በዳዴ ነዳኸው፣
ሽሽ ግዴለም እራቅ
ታውቃለህ የልቤን
እያዘንኩ ማንባቴን
ግን ይሄን ካላዎክ፣
ያለቀሰው ልቤ
ልክ ለመሆን ሲሻ፣አገግሞ ከእምባ፣
መመለስን ሽተህ፣በደካማው ጎኔ ድጋሜ እንዳትገባ፣
ምናልባት ከገባህ
አፍቃሪህ ነኝና
ውስጤ ቂምን ቋጥሮ፣ላዬ ቢቀበልህ፣
ሙት በድኔን ነው ያቀፍክ፣ነፍሴ ተጠይፋህ፣
ወረት ያገኜች'ትለ
ብድሯን ልትከፍል፣ማቅ ልታስለቅስህ።
ተፃፈ✍ደሱ


ምናለበት እንደው አንድ ወዳጅ ስልክ አውሶኝ በተገላገልኩ ከዚህ ከይሲ ጀለሴ ሆሆ ደግሞ እስክሪኑን በንፁህ ሶፍት እየጠረክ ይበለኝ፣ጭራሽ እጄ ንፁህ መሆን እንዳለበትም ሊነግረኝ ይከጅላል ሆሆ አይ ጊዜ ደጉ እንዲህ ይቀልድሜብኝ ያቺን ፍቅረኛውን በግጥ አማሎ እንዳላበሰላት፣ይሁና እንደው ግን ትርፍ ስልክ ሁላችሁም የላችሁም ፀጥ ብትሉብኝ አይደል😂😂😂😂😂
ለማንኛውም ሞቅ ሞቅ ባለ ነገር ስለሆነ የምንከሰተው በትግስት ጠብቁኝ ወይ ግን ለምን አዋጥታችሁልኝ አንድያዬን ስልኬን አላስጠግንም፣ለናንተምኮ ጥሩ አይደለም የውስጣችሁን የምታዳምጡበት ግጥም ሲጠፋ🙈🙈🙈እንዴ ደግሞ በውስጥ ፃፍልን ብላችሁን ዝም ያልኳችሁ በዚሁ በስልክ ችግር መሆኑ ይታወቅልኝ
@Almnu6
ለማንኛውም እንደው ዝም ከምላችሁ ብዬ እንጅ እናንተ .......❤️❤️❤️ነገር ናችሁ።


ግጥም ለመለጠፍኮ ጓደኛዬን መለመን አስጠላኝና ጠፋሁ በትግስታችሁ እረካለሁ፣ቤተሰቦቸ በቅርቡ ምርጥ ምርጡን ለናንተ is loading..


ሰላም ውድና የማከብራችሁ ተደራሲያን ከዛሬዋ እለት ጀምሮ
✅ለእናት
✅ ለአባት
✅ ለወንድም
✅ ለእህት
✅ ለአያት
✅ ለባል /ለሚስት
✅ ለጓደኛ
✅ ለፍቅረኛ
ስሜትዎን የሚገልፅ  የግጥም ስጦታ ማበርከት ከፈለጉ ባሻዎት  ቀንና ሰአት እንዲደርስ ተደርጎ  በተመጣጣኝ ዋጋ ይፃፍልዎታል 🌹🌹🌹🌹
በ 👉  0974793630 ይደውሉልኝ
ወይም ደግም
👇👇👇👇👇👇
@Almnu6
@Almnu6
ሌግራም ላይ ያናግሩኝ 🙏
ማሳሰቢያ ክፍያ የምትጠየቁ ግጥሙን ወስዳችሁ ከተመቻችሁና ካረካችሁ ብቻ ነው❤❤


ግጥም የናፈቀው


ክፋት......
ተንጣሎ መንገዱ
ውሾቹ እየወጡ እንዲወርዱ፣
መጥኔ ለኒያ ከቁር ውርጡ ተሞሽረው፣
መንገዱ ዳር ጋደም ላሉት ከሰው ይልቅ ውሻን አቅፈው፣
ይሰበካል ከአ'ውደምረት
ስለ ሽ ድድቅ ስለ ብዙ የዋህነት፣
ይስተጋባል ከመስጊዱ
ዕልፍ ዱዓ
መቶ አዛን
ስለ ፍቅር እንድንኖር፣ሰው ሳይጨክን በወገኑ፣
ጨለማውን እንዲሻገር፣ፍፁም ታምኖ ለወገኑ፣
ግና
አዛን ሁሉ ከንቱ
ስብከት ሁሉ መና፣
በየ መስጊድ በሩ
በየ አውደ ምረቱ
የሚሰበክ ጩኸት መች ፍቅር ነውና፣
መምህሩ ከሳተ
ምዕመን የሚማረው ጥላቻን ነውና።
ተፃፈ✍ደሱ


ፍራ'ቻ.........
አውቃለሁ
ቡትቶ ማንነቴ በፍቅርሽ ተለውጦ፣
ፀዳል ሸማን ይደርባል ድር ማጉን ሰርክ ድጦ፣
ያቺ ያረጀች የሞተች ነፍሴም በትረ ገነት ትወርሳለች፣
በእውን ኩነት አንቺን አቅፍ ከኔ አካቴው ታሸልባለች፣
አውቃለሁ፦
ንዋይ ያላጣመረው ልባችን ንዋይ ፍለጋ ቢኳትን፣
ቅንጣር እንደማይጎድል ድል አድራጊ ነው ፍቅራችን፣
ዳንኪራ በበዛበት ሀሳዊ መዋደድ አገምድሎ፣
ከኔና አንቺ በስተቀር ማን ይኖር ለፍቅር ጎድሎ፣
አይግረምሽ ታምራታዊው ሴትነትሽ ወንድነቴን ሲፈትን፣
ጎድዬ ነው የምሞላው ድል አድርጌ ድልብ ውሸትን፣
አውቃለው
ትላንት ያስተሳሰረን ፅኑ ቃል፣
ዛሬም እንደነበር ነው ላይሰበር ተመስርቷል፣
አንቺም ለኔ ኑረሽ
እኔም ላንቺ ልኖር
የአንድነታችን ስርዬት፣ አምናን በዘንድሮ ቀይሯል፣
አውቃለሁ፦
ውጥን እኔነቴ ሲታነፅ፣አንቺም በዛ ተወጠንሽ፣
ብቻውን ይሆን ዘንድ፣ክልክል ነው የሚል ቃል ፈፀምሽ፣
አየሽ ለደረትሽ ጎህ ሊቀድ ሲዳዳ፣
የኔ ግራ ደም፣ ለአንቺ ጡብ ሲቀዳ፣
አየሽ አጥንቴ ለመሰረትሽ፣አምድ ሁኖ ሲተከል፣
ማን ሴት አለና
ከአንቺ ውጭ፣ በኔ ግራ ጎን የሚበቅል፣
አውቃለሁ
የእቅፍሽ ሰማዬ ሰማያት፣የአካላትሽ መላ መንበር፣
ርስቴ ነው የወረስኩት፣በመንግስቴ የሚበሰር፣
ይሄን ስልሽ አይግረምሽ
ኤዶሜም ነሽ የገነት በር የማይብሽ፣
እርዛቴን ፋቀልኝ፣ከፍ አደረገኝ ሴትነትሽ፣
ይሄንን ግን አላውቅም፦
ትላንት ያስተሳሰረኝ የእውነት ፍቅር፣
ዛሬም አለ እንደ ፀና፣ ቋሚ ህጉን ሳይሸረሽል፣
እያወቅሽው
እያወኩት ስለ መውደድ ስንዘምር፣
ስለ ፍቅር ስንኳትን አዲስ ቀመርም ስንቀምር፣
በጊዜ ውል፣በዘመን ጎርፍ ተጠልለን፣
ነግ ምን እንደምንሆን፣ማን ይንገረን፣
እንጃ ይሄን ግን አላውቅም🙈
ተፃፈ✍ደሱ


ህልም....
በዚህ ሩጫ አለም
አሸልቦ እንደ'ማለም
አዲስ እድል፣ታምር የለም፣
በነተበ ፍራሼ ላይ፣ጥውልግ አንሶላ ዘርግቸ፣
ጋደም አልኩኝ፣አደራየን ለአምላክ ትቸ፣
መላ አካሌ ረጠበ፣
በላቤ ዶፍ ታጠበ፣
ሀጢያቴ ሲጎለብት፣ቅድስና ከኔ ሲርቅ፣
እግዚኦ
እግዚኦ
የሚል ጩኸት ይለፈፋል፣ከደጃፌ ቅንጣት ሳይርቅ፣
ተነሳሁኝ
እግዚኦ አልኩኝ
እልፍ ትውልድ ተሰብስቦ፣ዘማውያን ሊረገሙ፣
አዋጅ ነበር የሚጠበቅ፣ተፈንክተው እንዲደሙ፣
ከቀሳውስት
ከሹማምንት
መንጋ ርቀው፣ በፍቅር መጋረጃ ተጠልለው፣
የመዳን ጣር ይጮሃሉ ሁለት ነፍሶች ተቸንክረው፣
አቤት ውርደት
አቤት ቅሌት
የሚል ጩኸት በረታ፣ሊሰቀሉ ደወል ጮኸ፣
እውነታቸው ተቀበረ፣የውሸት ውል ጎልቶ ደኸ፣
ያቺ አለቀሰች
ውብ ጉንጮቿ በእንባ ራሱ
ፀዳል መልኳ ጨፈገገ፣ኩል አይኖቿ አለቀሱ፣
ገራገሩ የኔ ገላ በጥፋቱ ሳይፀፀት፣
አይዞሽ ብሎ አባበለ አቅፎ ያዛት፣
ተረጋግታ አይኗን አበሰች
ስለ እውነታው ተናገረች
አስተውል አንተ ጠማማ ህዝብ ሆይ፣
እኔ ደሊላን አይደለሁም፣ሀይልን በዝሙት ላፈርስ፣
ሴትነቴን የመነፈኩ፣መቅደሴንም የማረክስ፣
ኤልዛቤልንም አይደለሁ፣ርስት ለመውረስ የምባክን፣
ምስጊንን ገፍቸ ጥዬ፣የማባብል እውር አዳሜን፣
ቤርሳቤህንም እንዲሁ፣ ውብ ፍጥረትን ለማቀፍ፣
ዝሙትን የምመኝ፣ቅዱስ ምግባሬን የማጎድፍ፣
እና ማነው ፈራጁ
ሰይፍን ያነሳ በጁ
እኔ እውነትን እንዳዘልኩኝ፣ስለ ፍቅሬ ለመሰዋት፣
እድል ፅዋን የሚያድለኝ፣እርኩ'ሷን,ምድር እንድሸሻት፣
ስትል ያቀፍኳት ፍቅሬ
ልቤ ስለሷ ሸፈተ
ወኔን የተላበሰው ወንድነቴ በድፍረቷ ተፈወሰ፣
ለመፃኢው ፍርደ ገምድል መቀበሪያ ፊደል ማሰ፣
አቅፎ መሳም አማረኝ
ከደረቷ መለጠፍ
አደረኩት በወኔ ልቤ እስኪዝል ብሎ ፍስስ፣
ይሄን ሁሉ ቅዱስ ኪዳን
ስመሰክር ይዤ ክንዷን
በላብ የራሰው ገላዬ፣ከአንሶላው ድንገት ሲላቀቅ፣
ህልም መሆኑ ገባኝ፣በእውን ፍፁም የማይዘልቅ፣
እውነትማ ወዳጄ
ወዲያ ነው ያለ፣ ከአድማሱ ጀርባ ተጋርዶ፣
የውሸት ፍቅርን አንግሶ፣በቅዠት የተካ ግርዶ።
ተፃፈ✍ደሱ


ናፍቆት.....
በፍቅር አምናን ማስታወስ
ዘንድሮ አምጦ አይንን ማስለቀስ
ስለ ፍቅር ማቀርቀር
ስለ መውደድ መሽቀርቀር
በዛ'ን እለት አንቺም ለኔ እኔም ላንቺ፣
በውብ ሳቅሽ የፍቅርን ጥል ስትረቺ፣
በጉንጭሽ መሀል ባለች ዲንብል፣
መማረኬን ስገልፅልሽ በሰው መሀል፣
ሳንረታ ለቆፈኑ
ሳንሸነፍ ለምዕመኑ፣ስንጋፋ ስንተሻሽ
ሙሉ ነበርኩ አንቺ እያለሽ፣
ግን መቸም ሰው ነኝና
ከስናፍጭ ቅንጣት የምታንስ ጥፋት፣
አንችን ሙሽራዬን በመቅዘፍቱ ቀጣት፣
ሳቅሽ ላይመለሽ አሸልቦ ቀረ
ህልምሽም በወና ሰንብቷል ካደረ
እኔ ግን አፍቃሪሽ
ድግምግም ጥፋትሽ ሳያሳጣኝ ተስፋ፣
እናፍቅሻለው
እጠብቅሻለ፣
ቀኔን የምቆጥረው፣በኖርኩት ልክ ሳይሆን፣
ከዛ ጀምሬ ነው አንቺን ከአፈቀርኩት።
ቁጠሪ
በደንብ ቁጠሪ
ድህረ አለሜን ሳስብ ያላንቺ ባዶ ነው፣
አሁናዊው አለሜም ያላንቺ ድህረት ነው ፣
ጥለሽኝ ስትሄጅ ፍቅሬን ሳላጎድፍ፣
እናፍቅሻለው
በአዲስ ግላጭ ጀንበር እያፈቀርኩ'ሽ እጥፍ፣
ተፃፈ✍ደሱ


🎚.መስቀል.......🎚
ሊጨስ ደመራው
ኢሌኒ ልትወደስ
ቆስጠንጢኖስ ሊዘከር፣ አይሁዳን ሊረገሙ፣
ተጠራራ ምዕመኑ
አቡን አሉ ጳጳሳት
ተለኮሰ ጭራሮ
ተደመረ ደመራው ሹማምንቱም ታደሙ፣
በስሌት ዘውግ
ሽ ዘመናት ተወንጭፈው
ለዚህ በቁ፣በአዲስ ትውልድ ግፍ ተቆጥረው፣
በዚህ ዘመን
በደመራ የመሰልናት፣ሀገሬ ናት የምትነድ፣
ጭራሮ ህዝቧ፣ለመቃጠል የሚማገድ፣
ምሰሶዋ ማቅ ለበሰች
የባሩድ ጭስ እየማገች
ሰንደቋ ተረገጠ፣ውብ ሸማዋ ምድር ማሰ፣
ለሙታን ክብር ተነጠፈ፣ሰማዕታትን አለበሰ፣
እዩልኝ ሀገሬን
እዩልኝ እምዬን
ለምለም ፊቷ ጎስቁሎ፣ምድሯን እምባ ሲያረጥባት፣
ለመከራ ስትዳር፣ትንሳኤዋን ሲቀሟት፣
እናም የተለኮሰው ደመራ፣
ሀገሬ ናት
ልክ እንደኔ መጥኔ አፍኖ፣ጉም ያደረጋት፣
በጭጋግ ሀይል፣ውብ ቀለሟን የጋረዷት፣
ሀገሬ ማለት ዛሬ
እኔ ማለት ሁሌ
የተስፋ ፍኖስ የጠፍን፣በመከራ የምንበስል፣
እራፊ ነን የማንቆም፣በሹማምንት የምቆስል፣
ለመቆም እየዳዳን፣አግድሞሹን የምንወድቅ፣
ስጋችንን ለመመፅወት፣ነፍሳችንን የምንነጥቅ።
እኔም ኢትዮጲያዬም ደመራ ነን ችቦ ሙሉ፣
ቀን የደላው የሚያነደን በሞታችን እየማሉ።
ተፃፈ✍ደሱ


የታክሲ ሰልፎች ላይ ጥናት አልተደረገም እንጂ : የሠው ልጅ ባህሪ ተለዋዋጭነትን ፤ የህይወት ከባድነትን እና የድህነት አስከፊነትን ከብልሹ አሰራር ጋር : አያይዞ ቁልጭ ያለ ተጨባጭ ውጤት የሚገኝበት: የምርምር መስክ ነው።
ረ-ጅ-ም ሰልፍ ጠብቀህ: ታክሲ ውስጥ: ዘው ልትል ስትል ፤ ሰልፍ ላይ ያላየሃቸው :- እርጉዞች ፣ በእድሜ ጠና ያሉ እናቶች ፣ አያት የሚሆኑ አዛውቶች ፣ አካልጉዳተኞች ከታክሲ በሩ ጥግ ላይ ድቅን ብለው እያየህ : እንዴት ትገባለህ ? ማንንስ ታስገባለህ?

ሰልፉ ይገፋሃል : በኩራት ቆሞ የነበረው ሱፍ ለባሹ ገፍቶህ ይገባል፣ ስርዓት ያለው የመሰለ ሰውዬ: በስርዓት አልበኝነት ጥሶህ ያልፋል፣ እርጉዝ እንዳታሳልፍ ፤ አንተም የሆድህ ነገር ያሳስብሃል፣ አዛውንት አታሳልፍ ነገር፤ የአለቃህ ጭቅጭቅ ትዝ ይልሃል ፤ በቃ! ላለማርፈድ ፤ አይንህን ጨፍነህ ታክሲው በር ጥጉ ላይ የቆሙትን : የኢትዮጵያዊ እናት ፊት ባላዬ አልፈህ: የገፉህን ገፍተህ : በርትተህ ታግለህ ትገባና ወንበርህን በትግልህ ስትቀዳጅ :-
"የከተማ ውስጥ የታክሲ ትግል ተፋፍሟል !" የሚል ዜና መስራት ያምርሃል።

ታክሲው ውስጥ :-
"ሱፉን ግጥም አርጎ ተከምክሞ ፀጉሩ
መልዓክ መስሎ ታዬኝ ፤ አይ ያለው ማማሩ ! --- " እያለች አስቴር :ግፊውንም ሰልፉንም አስረስታ: ደህንነት እንዲሰማህ ታደርጋለች። ሾፌሩ የሚያጫውተው የቅጂ ቅጂ ሚሞሪ እና ጥራት አልባው ድምፅ ማጉያ :- የ አስቴርን ተስረቅራቂ ድምፅ ተንኮራኳሪ ለማድረግ ተግቶ እየሰራ፤ 'እፍን' እና "እንቅ" ቢያረጋትም: አስቴር ግን አሸንፋ ፤ በዚያ ፤ ጆሮ እና ልብ ሰራቂ በሆነ ዜማዋ : በሃሳብ ወሰድ፤ መለስ ታረገናለች።

"ሱፉን ግጥም አርጎ --- - ተከምክሞ ፀጉሩ
መልዓክ መስሎ ታዬኝ፤ አይ ያለው ማማሩ :- ይሄ የአስቴር ዘፈን ዘፈን ከመውጣቱ በፊት # "ሱፍ" በጣም ውድ ንብረት :የነበረ ሲሆን : ተለብሶ ከተወለቀ በሁዋላ :በሳጥን ውስጥ ተቀምጦ : በጓጉንቸር ቁልፍ ተቆልፎ : በዘበኛ ይጠበቅ ነበር።አሉ። ቻይና ራሷ : ያኔ : ሱፍ መውቀጥ እንጂ ሱፍ መላክ አልጀመረችም ነበር ፤ የባንክ ሰራተኞችም: ሱፍ ውድ ከመሆኑ የተነሳ ምናልባት እጀጠባብና ጎጃም አዘነ ለብሰው፤ ባንክ ውስጥ ከአቅማዳ ውስጥ ጠገራ ብር እያወጡ፤ በብራና በተፃፈ የባንክ ደብተር የያዙ: ደንበኞቻቸውን ያስተናግዱ ነበር። 'ሱፍ ልብስ" ከፍተኛው የሃብት መለኪያ ስለነበርም : የሃገሮች ዕድገት የሚለካው ህዝቦችዋ ባላቸው የሱፍ ልብስ መጠን ነበር አሉ። ! (አሉ ነው እንግዲህ)

-- - ከታክሲ ስወርድ : ምትሃተኛው የአስቴር ዘፈን ጆሮ ላይ ቀርቶ: ያለ አንዳችም ጆሮ ማዳመጫ በጆሮዬ እየተንቆረቆረ ነበር። ወደ ቤቴ ለመድረስ: በድካም ስክም፤ ውልክም:እያልኩ ገና ከመሰራትዋ: በተቆፋፈረችው ፒስታ መንገዷ ላይ: እየተጓዝኩ :በቤታችን አቅራቢያ: በስተግራዬ በኩል ካለው: 'የአብዲልባሲጥ መደብር' ደርሼ: ገልመጥ ስል፤ ሠፋ ካለው የመደብሩ የመስኮት ደፍ ላይ ቁጭ ብሎ: በርጫውን :-እየሸጠም፤ እየቃመም፤ ከሚገኘው አብዲ : ጋር: ዓይን ለዓይን ተገጣጠምን።

'ዎኦኦ ቡሼ !' እያለ: ዙርባውን አስቀምጦ :ከያዛት የጫት ቀንበጥ ጋር እጁን እያውለበለበ ሰላም :አለኝና
"ወንድምህ ደህና ነው ?" ሲል ጨመረበት።
"አለን አብዲ!" ብዬው የሰላምታ አፀፌታውን መልሼለት: :- የመጨረሻው ጥያቄ ክንክን እያለኝ: መንገዴን ቀጠልኩ ።

'ቃሚ እኮ የዋህ ነው: አብዲ ከመሬት ተነስቶ : "ወንድምህ ደህና ነው ወይ?" ካለኝ:፤ ወይ ሹክሹታ ነው ፤ ካልያም ሰበር ዜና ነው፤ ወይ ደግሞ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ነው፤ ከዚህ ውጪ አይደለም።

የግቢያችንን በር በያዝኩት ቁልፍ ከፈትኩና: ወደ ግቢ ገብቼ በድምፆች ወደ ተሞላችው ሰርቪስ ክፍል አቀናሁ። እናቴ እና እህቴ 'ሃናን' : በዛ ጥግ፤ የሆነ ድስት ጥደው : በዚህ ጋ ደሞ ቅመም እየፈጩ አገኘሁዋቸው ። የሚሰሩት አያልቅባቸውም መቼስ።

ሰላም ብያቸው በርጩማ ስቤ ተቀመጥኩና
"ሀባስ' ስ?" ብዬ ጠየቅኳቸው ። ያው ያ የአፍቃሪውን ወንድሜን ሁኔታ ለመጠየቅ ነበር። የሹክሹክታውን ምንጭ ለማወቅ ልቆፍርም አይደል?

"ቡ- ሼ -'አለች እናቴ
" ቡ- ሼ - ኧረ ይሄ ልጅ ስራ ተገባ አሰልሷል !: አለች።
እናቴ ደሞ አንዳንድ ቃላቶችን ደርሳ ስንቅር የምታረገው ነገር አላት " አሰልሷል ደሞ ምንድነው በፈጣሪ ? ለስልሷል ነው?"
ግር እንዳለን ፊቴ ላይ ተመልክታ
" ይሃው"ሶስተኛ ቀኑ ስራ ተሄደ !" አለችኝ ።

እ? ይሄማ: ዱሩዬው ፍቅር ነው ! ሥራ የሚያስጠላ፤ እሷን እሷን ብቻ የሚያሰኝ ፤ ዞሮ አዳሪ ፍቅር፤ እንግዲህ ፍቅርም እንደሰው ከሆነ :- ዱሩዬ ፣ጎዳና ተዳዳሪ፣ አስተማሪ ፣ ወታደር እና ፣ሌላም ሌላም የተለያየ ባህሪ እና ስራ ሊኖረው ይችላል ማለት ነው።

አንዴ እናቴን : አንዴ እህቴን እያፈራረቅኩ እያየሁ :
'እና ለመሆኑ የት እየዋለ ነው? በምንስ አውቃችሁ ?" ስል
እህቴ ተሽቀዳድማ:-
" ከቢሮ እየደወሉ ነበር ።ቢሮ እንዳልገባ ለማዬ ስነግራት : ደወለችለት ። እላይ ሰፈር ነኝ ብሎ ነገራትና : እብዲ ባለመደብሩ ደሞ ለኔ" እላይ ሰፈር ሱቅ ውስጥ ነው ሚውለው" ብሎ ነገረኝ።" አለች ። (ዓይኗ ውስጥ ትንሽዬ ሳቅ ያየሁ መሰለኝ።

አሃ ! አልኩ አሁን የሹክሹክታ ምንጩን ደረስኩበት።

እናቴ ጭንቅ እንዳላት ትኩ'ር ብላ ታየኛለች።

ሱቅ ስላላት: ሱቅ ውስጥ መዋል ጀመረ ! ንዴቴን የሚያበርድ እናቴን የሚያፅናና ነገር ማሰብ ጀመርኩ። ፖዘቲቭ ቲንከር ለመሆን ተጣጣርኩ ።

አይበለውና ! ይቺ ወንድሜ ያፈቀራት ልጅ መጠጥ ቤት ከፍታ ቢሆን ኖሮስ?
ቀምቃሚ ሆኖ መቅረቱ አልነበር?
አይበለውና ፤ ቁማር ቤት ብር ክፍት ?
ቁማርተኛ መሆኑ አይደል?
አይበለውና እህእ ፊልም ቤት ብትከፍት
አክተር ሆኖ ይቀር አልነበር ?
ሃሃሃ ብቻ: ድግ ደጉን ለማሰብ ስሞክር : ፌዘኝነት አመዘነብኝ።

ዓይን ዓይኔን ለምታዬኝ እናቴ መልስ መስጠት -የሚያፅናና ነገር መፍጠር አለብኝ ። ለማስተዛዘን እና ውጥረቷን ለማርገብ ፈልጌያለሁ ።

"አይዞሽ እናቴ ነገ ቁጭ አድርጌ መክረዋለሁ አስጠነቅቀዋለሁ ።አይበለውና ልጅቷ በሱቅ ፋንታ የቲክቶክ አካውንት ከፍታ አክቲቪስት ሆና ቢሆን ኖሮ እኮ ይሄኔ ባንዱ ክልል ዘምቶልሽ ነበር።"
አልኳት ።

ለማፅናናት ብዬ ለቀልድ ያልኩት ንግግር: ሳላስበው : የእናቴን የእምባ ከረጢት ወግቶ ኖሮ :-እናታችን ከተቀመጠችበት ተነስታ እዬዬ ትል ጀመር ።

ሁለታችንም ደንግጠን :በቅፅበት ውስጥ ክውው እንዳልን አጠገብዋ ተገኘን ። እህቴ አቅፋ ታረጋጋ ጀመር። እኔ በደመነፍስ ክው እንዳልኩ ቀርቻለሁ ።

እናት:- በሃዘን አትቀልድም፣ በጦርነት አታሾፍም፣
በዘመቻ አትስቅም ፣
የእናትነት ውስጥ በስጋት ተጀምሮ በስጋት የሚጠናቀቅ ከጥልቅ ፍቅርና : ሃላፊነት ተገምዶ በሴትነት የተማገረ : ከሰብአዊነት የተዋቀረ: ነፍስ አለ ።

እናቶቻችን ነጠላዎቻቸው የማይዘቀዘቅበት ፣
እጆቻቸውን በአፋቸው ጭነው የሚስቁበት ፣
ከልጆቻቸው ጋር የሚቀልዱበት ፣ እስክስታ ና ድግስ የሚያዘወትሩበት
የማይሰጉበትን የብርሃን ቀን እናምጣ።

አ.ብ.
ቡሽራ ነኝ ከሠንጋተራ(ከzehabesha)


እርባናውን ስቶ ለሚናውዝ ፍጡር፣
ለነግ አዲስ ጮራ፣ሰው እንዲሆን ማለም፣
እዉርን በጭፍን
መምራት ነው ውሳኔው፣ በዚች ታካች አለም፣
በጊዜያዊ ዋሻ
ለፈራሽ ስጋችን፣ነፍስን አቀንጭሮ በስጋ መደለብ፣
ትርፉ ሁሉ መና
ድካም ሁሉ ከንቱ
ፍፃሜው ጩኸት ነው፣ፍሬያችን ሲለቀም።
ተፃፈ✍ደሱ በተውሶ ስልክ አጮልቄ


አለሁ አለሁ ውዶችና የማከብራችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች ስልኬ ስለተበላሸች ነው የጠፋሁት ያው ግዙልኝ አልል ነገር የኑሮን ነገር ስለ ማቀው እስከዛ ግን በተጓዡ ማስታወሻ ድንቅ ድንቅ ክታቦችን እያዘጋጀው ነውና ለአቅመ ስልክ ስበቃ መለጠፍ እጀምራለሁ❤️❤️❤️ወይ አንድ ተደራሲያን ስልክ አውሱኝ ልል አሰብኩና🙈🙈🙈🙈መልሸ ተውኩት ወይ ደግሞ አዋጡልኝ ብየም ለማሰብ ይቃጣኛል😂😂😂በመጨረሻ ሀሳቤ የኔ ነውና የተዳፈርኳችሁ በጣም ይቅርታ ብትናፍቁኝ ጊዜ ነው🙏🙏እንደውም በቃ ስልኬን አሰሩልኝና ግጥሞቸን ልለጥፍ ድርሰቷም ወደ ውስብስብ ታሪኳ ትሸጋገር እኔም ጋር ያልጨረስኩላችሁን ታሪክ ልቀጥል👌☝ለነገሩ ምን በወጣችሁ እንደው ቢጨንቀኝ እንጂ😂😂😂ግን ብታዋጡልኝ ምን አለበት አምሳ ሎሚ ለአምሳ ሰው ጌጡ እንዲሉ አበው😭😭በቃ መልካም ሰኞ በተለይ ከውጩ አለም ግጥሞቸን በነፃ የሰጠዋችሁ ወረታየን መልሱልኝ🙊🙊🙊ብዬ መለመንም ይዳዳኛል🫰
ወይ የናንተ ናፍቆት እንደውም በቃ ወሰንኩኝ አዋጡልኝ😂😂😂ድፍረቴ ሆሆ የመፖሰት አመል ያደርገኝን አሳጣኝኮ በሉ ኧረ ወደ ገደለው ግቡና የጣላችሁትንም ቢሆን ትርፍ ስልክ
👇👇👇👇👇👇👇👇
@Almnu6
@Almnu6
አድራሻዬን ጠይቁኝ መጥታችሁ ስጡኝ💋💋🙈
አደራ ይዛችሁ ስትመጡ ካርዷንም እንዳትረሱ በትህትና አመለክታለሁ🙈🙈🙈
ተፃፈ✍ደሱ ነኝ ከጓደኛዬ ስልክ ጀርባ አጮልቄ🌚🌚🌚🌚


ውድ ተደራስያንና ተፈጣሪያን የቻናሉ ቤተሰቦች ስለ ሁሉ ነገር አብሮነታችሁ አይለየን ይቺን አፋልጉኝ ከለጠፍኩላችሁ በሗላ የደሱ ወዳጅ የሆነ የቻናላችን ቤተሰብ ባደረሰን መረጃ ደሱ በጣም እንደናፈቃችሁና አዳስ ሀያሲወቹን ከትቦ በስልኩ መበላሸት እንደጠፋ ነው፡ያረጋገጥኩት


ሰላም ውድ የቻናሉ ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ ደሱ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ እየጠፋብን ስለሆነ እስኪ
👇👇👇👇👇
@Almnu6
ምን ሁነህ ነው በሉት እኔ admin ነኝ


እልህ በቋፍ ችንካር
በትቢት ሞሽሮ ለህዝብ ሲቃ አውጆ፣
በእርቃን ገላ ዙፋን
በደም ሽ ቢተከል ለሚፈርስ ጎጆ፣
አዲስ መንፈስ ገሎ
አዲስ አመት ማንገስ
በነዛ ሚስጊኖች እምባ ስጋ ማብሰል፣
በታይታ ተማርኮ
በልቅሶ የባተ የአዲስ አመት ብስራት፣
ከንቱ ውዳሴ ነው አዋጅ ብሎ መጥራት፣
ህዝቡ ሳይሻገር
በንጉሳን ፌሽታ
በአሽሙረኛ ዘፈን እንኳን አደረሰን አያሉ መማማል፣
ለኛ አይነቱ ሚስጊን
ሞት ለታወጀበት
የምን አዲስ አመት
በአሮጌ ትርክቶች ሆ ተብሎ ዘወትር ተመርጦ ሚገደል።
ተፃፈ👇ደሱ

20 last posts shown.

1 665

subscribers
Channel statistics