በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍል ሰማይ ላይ የታየው ክስተት በሰው ሰራሽ የስፔስ ቁስ ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ይችላል፦ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦፓሻል ኢኒስቲትዩት
*************
በትናንትናው ምሽት በደቡብ ኢትዮጵያ ክፍል ሰማይ ላይ እየተቃጠለ ተቆራርጦ ወደ ምድር ሲጓዝ የታየው ቁስ በሰው ሰራሽ የስፔስ ቁስ ምክንያት የተከሰተ ሊሆን እንደሚችል የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦፓሻል ኢኒስቲትዩት ገለፀ፡፡
በስፔስ ሳይንስ እና ጂኦፓሻል ኢኒስቲትዩት የከባቢ አየር ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት ገመቹ ፋንታ (ዶ/ር) ከኢቢሲ ዶት ስትሪም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጊዜ ያበቃላቸው ሳተላይት እንዲሁም ሳተላይቶችን የመጠቁባቸው የሮኬት ቁርጥራጮች ሊሆኑ ይችላሉ ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
በማንኛውም ሰው ሰራሽ መንገድ ህዋ ላይ የሚንቀሳቀሱ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ወደ ከባቢ አየር ውስጥ ሲገቡ የመቃጠል እና ተሰባብሮ የመውረድ ምልክቶችን እንደሚያሳዩ ገልጸዋል፡፡
ክስተቱ የተፈጠረው በተፈጥሮአዊ የህዋ አካላት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡
ከመሬት እና ከሶላር ሲስተም አፈጣጠር አንጻር አለቶች በመኖራቸው በማንኛውም ጊዜ እየተቆራረጡ ሊወርዱ እንደሚችሉ ነው ያነሱት፡፡https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0mqCDgmGv1QMKcKbNsdLBcvPzseSxzWviAKQwy8L5LFb6FutqEByCPLFq7rpFjrYl