ECWC/ኢኮሥኮ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


Official ECWC Telegram Channal
.የኮርፖሬሽኑ ዜናዎች
.የጨረታና የሥራ ማስታወቂያዎች
. በየወሩ የሚታተመው የዜና መጽሄት
. ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮች
.በየ 6ወሩ የሚታተመው የኮርፖሬሽኑ ዕይታ መጽሄት እና የኮርፖሬሽኑ ፕሮፋይል በዚህ ገጽ ላይ በየጊዜው ይቀርባል፡፡

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የውስጥ ባለድርሻ አካላት ፎረም በተለያዩ የአሰራር ማኑዋሎች ላይ ተወያየ
----------
በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የውስጥ ባለድርሻ አካላት ፎረም በተለያዩ የአሰራር ማንዋሎች ላይ ጥልቅ ውይይት አደረገ፡፡
የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሰፋ ከሲቶ የማኑዋሎች ዋና ዓላማ የኮርፖሬሽኑን መብት እና ፍላጎት ማስጠበቅ እና የተቋሙን መልካም ስምና ዝና በዘላቂነት ጠብቆ ማቆየት ነው ካሉ በኋላ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የኮርፖሬሽኑ የሥራ ክፍሎች ማኑዋሎችን ሙሉ በሙሉ መተግበር ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
እስከ አሁን የስጋት ሥራ አመራር፣ የይገባኛል ሥራ አመራር፣ የተሰብሳቢ ሂሳብ ሥራ አመራር፣ የሥራ ውል ሥራ አመራር እና የክርክር ጉዳዮች ሥራ አመራር ማኑዋሎች በጥንቃቄ ተቀርጸው ለሥራ ዝግጁ ሆነዋል፡፡
ፎረሙ በየወሩ በመሰብሰብ በስጋት፣ በይገባኛል እና ህግ-ነክ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት የሚወያይ አደረጃጀት ነው፡፡


የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ECWCT/NCB/SG-64/2017


የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የተለያዩ ያገለገሉ መሳሪያዎችንና ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1.  በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል ለድርጅቶች የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሲሆን ለግለሰብ ደግሞ መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ በማቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር/በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት የሀገር ውስጥ ጥቅል ግዥ ቡድን ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
2.  የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚመጣ ተዛማጅ የሆነ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ወይም መታወቂያ እና  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡

3.  የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች    መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም ተጫራች ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው ፡፡


4.  ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ብር አስር በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ጋራንቲ (የባንክ ዋስትና) ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡

5.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ግዥ መምሪያ-1 ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው፡፡


6.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው ግዥ መምሪያ-1 የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

7.  ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

8.  ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
         
          የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግዥ መምሪያ አንድ ቢሮ
          አድራሻ፡-ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ
                  አንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ፊት-ለፊት
                  ስልክ ቁጥር 0118 72 29 91/ 0118-72 29 58






Invitation for EOI 62-2017.docx
35.8Kb
EOI For pre qualification of construction companies having GC-5, BC-5, RC-5, WWC-5 And above


የኮርፖሬሽኑ የምገባ ማዕከል ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ድጋፍ አደረገ
----------------------
የገና በአልን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የተስፋ ብርሃን ምገባ ማእከል  ተጠቃሚዎች   የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ፡፡

በኮርፖሬሽኑ የማህበራዊ ጉዳዮችና የሥራ ቦታ ደህንነት መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ቁምላቸው  በድጋፍ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ128 ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ብር፣ በድምሩ 640 ሺህ ብር ለግሷል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የካ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 09 የሚገኘው የምገባ ማዕከሉ ከሰኔ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለበርካታ ወገኖች የምገባ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡




የኮርፖሬሽኑ የሠራኞች ስፖርት ቡድን የበጋ ስፖርት ውድድሩን በድል ጀመረ
--------
ታህሳስ 27 2017 (ኢኮስኮ)
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ባሰናዳው የ2017 ዓ.ም የበጋ ስፖርት ውድድር የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢኮስኮ) የሠራተኞች  የስፖርት ቡድን በመክፈቻው  ዕለት  በ200 ሜትር ሴቶች እና በ400 ሜትር ወንዶች የሩጫ ውድድር በሁለቱም ፆታዎች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት የሜዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም ከ20 ተቋማት በላይ በሚሳተፉበት በዚህ ውድድር  የመክፈቻ ፕሮግራሙን በማድመቅ ለተከታታይ ሁለት ዓመት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ውድድሩ ጠንካራ፣ ጤናማና አምራች ዜጋን የመፍጠር፣ በሰራተኞች መካከል መልካም ግንኙነትን የማጎልበት  ዓላማን ያነገበ ስለመሆኑም ነው የኢኮስኮ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ  አንተነህ ሙሉቀን የገለፁት። 

የኮርፖሬሽኑ የሠራተኞች  የስፖርት ቡድን በስምንት የውድድር ዓይነቶች የሚሳተፍ ይሆናል።


Ambassador Mesfin visits ECC's branch office in Rwanda
--------------------
H.E Mesfin Gebremariam, Ambassador Extraordinary & Plenipotentiary of Ethiopia to the Republic of Rwanda visited ECC's branch office in Rwanda.

During the visit , the branch office head Eng. Yared Wedajo extended his heartfelt thanks to the Ambassador on behalf of the entire ECC team, and expressd his commitment to work together fostering collaboration and development of the region.


Date: 1/2/2025
NOTIFICATION OF BID EXTENSION
To: All Participants of the Bid
Subject: Extension of Bid Closing Date for Tender No. ECWCT-NCB-PG-58/2017 
Dear Sir/Madam,
We have received a request from bidders to extend the bid closing date for the procurement of Asphalt (Bitumen) 60/70, 80/100, MC-30 with tender number captioned above. After careful consideration, we have decided to honor this request and extend the bid closing date from the original date of January 4, 2025, to January 9, 2025, at 10:00 A.M., with the bid opening scheduled for 10:30 A.M. on the same day.
We understand the importance of providing all interested parties with sufficient time to prepare and submit their bids effectively. Therefore, we believe that extending the bid closing date will allow for a more comprehensive and competitive bidding process. Please note that all other terms and conditions outlined in the original bid invitation remain unchanged.
Thank you for your understanding and cooperation in this matter.
For Additional Information:
                                        Ethiopian Construction Works Corporation.
                                       Gurd Shola behind Athletics federation building
                                          and Infront of Andinet international College
                                             Telephone 011 8 96 29 91/01118 67 80 89
                                                      Addis Ababa, Ethiopia





12 last posts shown.