ELA TECH💡


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


👋 ሰላም ሰላም እንኳን ወደ ELA TECH በሰላም መጡ
➡ ለማንኛዉም ጥያቄ , አስተያየት እንዲሁም ሀሳብ
በዚ ያገኙናል
👇
@ELA_TECHBOT
➡ በ Youtube ጠቃሚ ቪዲዮችን ለማግኘት የ YOUTUBE ቻናላችንን ይጎብኙ
👇
https://youtube.com/@ELA_TECH

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


የቀጠለ


📍 ከዚህ በፊት በሶስት part ስለ fund አካውንት አይተናል ይሄ በ master account የመጨረሻ part ነው

📍የመጨረሻ part ላይ እንዳየነው phase 2 profit target 5% ካሳካን ቀጣዩ part master account ነው master account ስንቀበል ብዙ የሚያስፈልጉን ነገሮች አሉ ከነዛ መካከል KYC verification አንደኛው  ነው

- passport
- national id


📍 ተጠቅመን verify ማድረግ እንችላለን ከዛ በኋላ በተወሰነ ቀናት ውስጥ master account ይሰጡናል የሚቆይበት አጋጣሚ አለ ግን ያው ይሰጣሉ በብዛት እና በፍጥነት

ዋና ዋና ህጎቹ


📍phase 1 እና phase 2 ላይ ስትጠቀሙት የነበረው ህግ አሁንም እዚሁ ላይ አለ የተለየ ነገር የለውም ልዩነቱ እዚህ ላይ profit የምታደርጉት በሁለት ቀን በሳምንት ወይም በወር በተለያየ % ልዩነት ማውጣት ትችላላችሁ ልዩነቱ ያ ነው

daily loss 5%
maximum loss 10%
Profit split 80%

📍Profit share ስንት % ነው ?

በሁለት ቀን payout 60%
በሳምንት payout 80%
በወር payout 100%

ይሄ የ funding pips ነው

📍ይሄ ሁሉም prop firms ላይ የለም የተወሰኑ ናቸው የሚጠቀሙት ብዙሀኑ ግን 80/20 ነው የሚጠቀሙት እና በየሳምንቱ ነው የ payout day

📍ቀጣይ ደሞ ስለ real account እና በስንት ብንጀምር የተሻለ ነው የሚለውን እናያለን መልካም ቀን
©433_Crypto
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


ባር ኮድ እና QR ኮድ ምንድን ነው ልዩነታቸው።

- ባር ኮድ እና QR ኮድ ሁለቱም መረጃን በምስላዊ መልክ የሚያከማቹ እና የሚያስተላልፉ ቴክኖሎጂዎች ናቸው። ነገር ግን በመጠን፣ በሚይዙት የመረጃ መጠን እና በአጠቃቀም ላይ በርካታ ልዩነቶች አሏቸው።

📍 ባር ኮድ
- አንድ ልኬት ኮድ: ባር ኮዶች በአንድ አቅጣጫ ብቻ መረጃን የሚይዙ አንድ ልኬት ኮዶች ናቸው።

-  ቀላል መረጃ: በአብዛኛው የምርት መታወቂያ ቁጥሮችን፣ ዋጋዎችን እና ሌሎች አጭር የጽሑፍ መረጃዎችን ያከማቻሉ።

-  አነስተኛ የመረጃ አቅም: በአንጻራዊነት በጣም ትንሽ መጠን ያለው መረጃ ብቻ ይይዛሉ።

- ቀላል ንድፍ: ጥቁር እና ነጭ ቀጥ ያሉ መስመሮችን በተለያየ ውፍረትና ርቀት በማዋሃድ የተሰራ ነው።

- አጠቃቀም: በዋናነት በሱፐርማርኬቶች፣ በመጋዘኖች እና በሌሎች የሎጂስቲክስ አካባቢዎች ለምርት መለያ እና ለመከታተል ያገለግላል።

📍 QR ኮድ
- ሁለት ልኬት ኮድ: QR ኮዶች በሁለት አቅጣጫ መረጃን የሚይዙ ሁለት ልኬት ኮዶች ናቸው።

- ውስብስብ መረጃ: ዩአርኤሎችን፣ ስልክ ቁጥሮችን፣ ኢሜይሎችን፣ ጽሑፎችን፣ ምስሎችን እና ሌሎች ብዙ አይነት መረጃዎችን ማከማቸት ይችላሉ።

- ከፍተኛ የመረጃ አቅም: ከባር ኮዶች በጣም በልጠው ትልቅ መጠን ያለው መረጃ ይይዛሉ።

- ውስብስብ ንድፍ: በካሬ ቅርጽ ያለው ሞዱል በተደረደሩ ጥቁር እና ነጭ ሞጁሎች የተሰራ ነው።

- አጠቃቀም: በሰፊው በማስታወቂያ፣ በክፍያ፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በመረጃ ማከማቻ እና በሌሎችም በርካታ አካባቢዎች ጥቅም ላይ ይውላል።

- በአጭሩ ለማጠቃለል፣ ባር ኮድ በዋናነት ለምርት መለያ እና ለመከታተል የሚያገለግል ሲሆን QR ኮድ ደግሞ በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃን ለማከማቸት እና ለማስተላለፍ የሚያገለግል ነው።

📍 ለምሳሌ:
- ሱፐርማርኬት ውስጥ ባሉ ምርቶች ላይ የምናየው ጥቁር እና ነጭ መስመሮች ያሉት ምልክት ባር ኮድ ነው።

- በመጽሔቶች፣ በፖስተሮች እና በሌሎች ማስታወቂያዎች ላይ የምናየው ካሬ ቅርጽ ያለው ምልክት ደግሞ QR ኮድ ነው።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


የቀጠለ


ከዚህ በላይ ባለው ስለ phase 1 አውርተናል አሁን ደሞ ስለ phase 2 እናያለን

📍 ከ phase 1 ጋር ሁሉም ነገር ተመሳሳይ ነው ልዩነቱ ማትረፍ ያለባችሁ መጠን ብቻ ነው ይሄ ማለት በመጀመሪያ ማለትም በ phase 1 8%(400$) ነው ማትረፍ ያለብን በሁለተኛው phase 2 ደሞ 5%(250$) ነው ማትረፍ ያለባችሁ

መርሳት የሌለባችሁ ነገር


📍 phase 1 ማለፋችሁ ጥቅም የሚኖረው እና ፍሬ የሚያፈራው phase 2 ስታልፉ ብቻ ነው ከዛ ውጪ ጥቅም የለውም

📍 አንድ ሰው phase 1 ምንም አይነት ስህተት ሳይሰራ ቢያልፍ እና phase 2 ላይ ከህጉ ውጪ ማለትም በቀን ከ 5% በላይ ቢከስር ወይም በአጠቃላይ ከ 10% በላይ ቢከስር አካውንቱን ያጣል phase 1 ያለፈበትም ይከስራል ማለት ነው ምንም ጥቅም የለውም

📍ለ phase 1 እራሱን የቻለ 5000$ አካውንት
ለ phase 2 እራሱን የቻለ 5000$ አካውንት ነው የሚሰጣችሁ



ስለዚህ በአጠቃላይ የተሳካ ነገር ለማድረግ

phase 1 5400$ balance
Phase 2 5250$ balance

📍 መሆን አለበት ማለት ነው phase 1 5400 አድርጋችሁ phase 2 ላይ ስህተት ብትሰሩ እንደ አዲስ ከ phase 1 የምትጀምሩ ይሆናል ስለዚህ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው

📍ሁለቱንም ካሳካችሁ በኋላ ቀጣይ ምንድነው ሚደረገው ? master account ይሰጣችሁ ይሄ ማለት የምታገኙትን profit payout ማድረግ የምትጀምሩበት አካውንት ነው

በውስጡ ያሉትን ወሳኝ ህጎች እና አንዳንድ ነገሮች በቀጣይ እናያለን

©433_Crypto
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


በሮቦቶችና በሰው ልጆች የሚደረገው የሩጫ ውድድር !

📍በመጪው ሚያዝያ ወር ቁርጡ ይታወቃል በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዓለም ታዋቂ የሮቦቲክስ ኩባንያዎች ባዘጋጁት በደርዘን ከሚቆጠሩ ሰው መሰል ሮቦቶች ጋር የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ሊያደርጉ ቀን ተቆርጦለታል።

📍አሸናፊዎቹ ሰውም ይሁኑ ሮቦት እንደ አፈፃፀማቸው የገንዘብ ሽልማት ያገኛሉ ተብሏል።

📍እንደ ኦዲት ሴንትራል ዘግባ ከሆነ የሮቦቶቹ ፍጥነት በሰዓት ከ8 እስከ 12 ኪሎ ሜትር እንደሚደርስ ይገመታል።

📍21 ነጥብ 1 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የግማሽ ማራቶን ውድድር በአንድ ሰዓት ተኩል ውስጥ ለማጠናቀቅ ደግሞ በአማካይ በሰዓት 14 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ያስፈልጋል።

📍ይህ ለሮቦቶቹ ምናልባትም ፈተና ሊሆንባቸው ይችላል.....በተጨማሪም ሮቦቶችን የሚገጥማቸው የባትሪ ችግር ሲሆን የውድድሩ አዘጋጆች ግን በውድድሩ አጋማሽ ላይ ባትሪ መቀየር እንደሚፈቀድ አስታውቀዋል።
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


የቀጠለ


አንድ ሰው በ fund account trade ሲያደርግ phase 1 እና phase 2 የሚባሉ ነገሮች አሉ ምንድናቸው ?

📍አንድ ሰው ለምሳሌ የ 5000$ አካውንት እንደገዛ የመጀመሪያው step phase 1 ይባላል ይሄ ማለት ከዚህ በታች ያለውን ህግ የሚጠቀም ይሆናል :-

account size 5000$

trading period = unlimited

Minimum trading days = 3 days

Maximum daily loss 5%(250$)

maximum loss = 10%(500$)

Profit target = 8%(400$)
📍ይሄ phase 1 ወይንም እንደ መጀመሪያ ፈተና ቁጠሩት በዋነኝነት ማየት ያለባችሁ ነገር የገዛችሁት account size 5000$ ስለሆነ ብቻ በሙሉ trade ማድረግ አትችሉም ከላይ እንዳስቀመጥኩት የራሱ የሆነ rule አለው

ይሄ ማለት ምን ማለት ነው

?

📍አንድ ሰው ለምሳሌ ዛሬ trade ለመግባት ቢያስብ እና የ አካውንቱን 5%(250$) risk ቢያደርግ እና በ SL(በኪሳራ) ቢወጣ ሙሉ ለሙሉ የገዛውን አካውንት ያጣዋል ምክንያቱም daily loss አጠቃላይ እንኳን ህጋቸው ላይ 5% ነው የሚፈቅዱት ያንን ከከሰራችሁ አካውንቱን ታጡታላችሁ ።


ስለዚህ ምን ማድረግ አለብን

?

📍trade ስንገባ 5000$ እንዳለው ሰው ሳይሆን 250$ እንዳለው ሰው ነው risk manage የምናደርገው ስለዚህ በ % ስናሰላው የቀን ትሬዳችንን balance እንደ 250$ እያሰብን መሆን አለበት ማለት አጠቃላይ በአካውንቱ risk mange ስናደርግ ደሞ 500$ እንዳለው ሰው መሆን አለበት

⚠️ ምክንያቱም አጠቃላይ 10% ከከሰርን አካውንቱን እናጣለን
⚠️ በቀን 5% ከከሰርን አካውንቱን እና
ጣለን
📍ስለዚህ የዚህ አካውንት 4500$ ምንም ጥቅም የለውም ማለት ነው

📍 ማትረፍ የሚጠበቅብን በ phase 1 8%(400$) ነው ይሄንን ካሳካን ወደ phase 2 የምንሄድ ይሆናል ማለት ነው

ይቀጥላል phase 2......
©433_Crypto
══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


አደገኛ መተግበሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ መሆኑን ንግድ ባንክ አስታወቀ፡፡

📍ደምበኞች በዋትስ አፕ እና በቴልግራም የሚሠራጭ Pharma+
/CBE Vacancy መተግበሪያን እንዳይጭኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳስቧል።

📍ባንኩ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት፤ ባደረገው ምርመራ መሠረት አደገኛ መተግበሪያ ማግኘቱን ገልጿል።

📍ይህ Pharma+
/CBE Vacancy የተሰኘ አሳሳች መተግበሪያ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በሰፊው እየተሰራጨ እንደሆነ በመጥቀስ፤ ይህ መተግበሪያ በቴሌግራም እና ዋትስአፕ ወደ ደንበኞቹ እየደረሰ መሆኑን ጠቁሟል።

📍መተግበሪያው በስልክ ላይ ከተጫነ ያለ ፈቃድ ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችልም አሳውቋል።

📍ባንኩ ከዚህ አይነት አደጋ ለመጠበቅ ከቴሌግራም ወይም ዋትስአፕ መተግበሪያዎችን አታውርዱ ብሏል።

📍ደንበኞች መሰል ተግባራት ሲገጥሟቸው በ951 ነጻ የስልክ መስመር ደውለው እንዲያሳውቁ አሳስቧል።


══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


Assisterr Ai Airdrop

📍በቅድሚያ በዚህ ሊንክ ገብታችሁ ከSolana Wallet ጋር Connect አድርጉ
https://build.assisterr.ai/?ref=6799ba28416e202d4f6d224e

- ከX እና Discord አካውንታችሁ ጋር Connect አድርጉ
- Home የሚለው ላይ ያሉትን Task ስሩ
- SLM የሚለው ላይ እየገባችሁ የምትፈልጉትን ጥያቄ ጠይቁት (Like chatgpt)
- Daily እየገባችሁ Claim አድርጉ


የናሳ WIFI ፍጥነት ወደ 91GB/s ነው። ይህ ማለት አንድ ረጅም ተከታታይ ፊልም ሙሉ ሲስንና ኤፒዞድ ማውረድ ብትፈልጉ ለማውረድ ቢበዛ 1 ሰከንድ ነው የሚፈጅበት

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ለመግዛት ንግግር መጀመሩን ትራምፕ ገለጹ

📍ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ለመግዛት ውይይት ላይ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያው ሽያጭ ላይ "የጦፈ የጨረታ ግብግብ" ማየት እንደሚፈልጉ ትራምፕ ተናግረዋል። የአሜሪካው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ማይክሮሶፍት ለጨረታ እያዘጋጀ ነው ወይ የሚል ጥያቄ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ትራምፕ “አዎ” ሲሉ የመለሱ ሲሆን አክለውም በርካታ ኩባንያዎች “በቲክ ቶክ ላይ ትልቅ ፍላጎት አላቸው" ሲሉ ተደመጠዋል።

📍ትራምፕ ሆኑ ጆ ባይደን የቲክቶክ እናት ኩባንያ የሆነውን ባይትዳንስ የአሜሪካን በብሔራዊ ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላል በሚል ምክንያት እንዲሸጥ ለማስገደድ ሲሞክሩ ቆይተዋል። በዚህ መሰረትም መተግበርያው ለ17 ያህል ሰዓታት ተዘግቶ ለመቆየት ተገዶ የነበረ ቢሆንም ኃላ ላይ ትራምፕ በሰጡት የ75 ቀናት ቀነ ገደብ ምክንያት ቲክቶክ በአሜሪካ ዳግም መስራት የጀመረ ቢሆንም በ75 ቀናት ውስጥ ግን ቢያንስ የቲክቶክ 50 በመቶ ድርሻ ለአሜሪካዊ ባለሀብት ወይንም ኩባንያ እንዲሸጥ ታዟል። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ቲክቶክ ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ እንደሚዘጋ ተገልፆል።

📍ከዚህ ቀደም ማለትም እኤአ በ2020 ላይ ማይክሮሶፍት ቲክቶክን ለመግዛት ተንቀሳቅሶ የነበረ ቢሆንም በሰዓቱ ግን የቲክቶክ የአሜሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከማይክሮሶፎት ይልቅ ድርሻቸውን ለኦራክል ለመሸጥና ከነሱ ጋር አብረው ለመስራት መወሰናቸውን ቢገልፁን ስምምነቱ ግን ተፈፃሚ የሆነ አልነበረም። አሁን ታድያ የመሸጥ ወይም የመዘጋት አጣብቂኝ ውስጥ የገባው ቲክቶክ በቀጣይ ለማን ይሸጣል ምንስ ይሆናል የሚለው ነገር ተጠባቂ ሲሆን ትራምፕ በበኩላቸው ግን የቲክቶክን ሽያጭ በተመለከተ ከበርካታ አካላት ጋር እየተወያዩ እንደሆነ እና በሚቀጥሉት 30 ቀናት ውስጥ በመተግበሪያው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተናግሯል።

📍ስለ ግዢው የተጠየቁት የማይክሮሶፍት ቃል አቀባይ በበኩላቸው ኩባንያው "በአሁኑ ጊዜ ምንም የሚያጋራው መረጃ የለም" ብለዋል። በቲክቶክ ግዢ ላይ ከማይክሮሶፍቶ በተጨማሪ እንደነ ሜታ ያሉ ኩባንያዎችና እንደነ ሚስተር ቢስት ያሉ ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎችን በተደጋጋሚ ስማቸው እየተነሳ ይገኛል።

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


ለአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የቻይናዉ ዲፕሲክ ስኬት የማንቂያ ደዉል ነዉ ሲሉ ትራምፕ ተናገሩ

📍የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰው ሰራሽ አስተዉሎት ኢንተለጀንስ (AI) ሞዴል በዎል ስትሪት ግብይት ላይ አስደንጋጭ ስኬት ማግኘቱን ተከትሎየቻይናውን ዲፕሲክ ኩባንያ መነሳት ለአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ “የማንቂያ ጥሪ” ነዉ ብለውታል።እንደ ኒቪዲ ያሉ ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች አክሲዮኖች በከፍተኛ ሁኔታ የተቀዛቀዘ ሲሆን ፣ ግዙፉ ቺፑ 600 ቢሊዮን ዶላር የአክሲዮን ገበያ ዋጋ አጥቷል።

📍ኢንደስትሪውን ያናወጠው የ DeepSeek የ R1 ሞዴሉ ከተቀናቃኞቹ ዋጋ በትንሹ የተሰራ ነው፡፡ ስለወደፊቱ የአሜሪካ ሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት የበላይነት እና የአሜሪካ ኩባንያዎች እያቀዱ ስላሉት ኢንቨስትመንቶች መጠን ጥያቄዎችን አስነስቷል።ዲፕ ሲክ ከጀመረ ከአንድ ሳምንት በኋላ በአሜሪካ ውስጥ በጣም ዳዉንሎድ የተደረገ ነጻ መተግበሪያ ሆኗል።ለዜናው ምላሽ ሲሰጡ ትራምፕ በቻይና ሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት ኢንዱስትሪ ውስጥ የተከሰቱት የቅርብ ጊዜ ለውጦች ለአሜሪካ “አዎንታዊ” ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል ።

📍በርካሽ ማድረግ ከቻሉ፣ ባነሰ እና ተመሳሳይ ውጤት ላይ መድረስ ከቻሉ፣ ይህ ለኛ ጥሩ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።ዩናይትድ ስቴትስ በዘርፉ የበላይ ሆና እንደምትቀጥልም ተናግረው ስለ ግኝቱ ስጋት እንዳልገባቸዉ አክለዋል፡፡ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መተግበሪያዎችን ቢሊዮን ዶላር ወጪ አድርገው የሰሩ ቢሆንም ይህ  ጀማሪ የቻይና ኩባንያ ግን በትንሽ ወጪ ተሰርቷል።

📍በቀላሉ ዲፕሲክ ማለት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የጎለበት ቻት ቦት ሲሆን፣ እንደ ቻትጂፒት ያለ ነው።ይህ በ Apple's app store ላይ በብዛት እየወረደ ያለ ነጻ መተግበሪያ ነው፡፡ ዲፕ ሲክ"ጥያቄዎችዎን ለመመለስ" ተብሎ የተዘጋጀ ነው።

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


💧 3 ምርጥ ምርጥ ዌብሳይቶች 💧

#1
ytx.mx

💡እዚ ዌብሳይት ላይ የምትፈልጉትን የውጭ ሀገር ፊልሞች በነፃ ማውረድ ትችላላችሁ

#2
img2go.com

💡እዚህ ዌብሳይት ላይ ከ 30 በላይ በ AI Develop የተደረጉ የፎቶ ኤዲቲንግ
#tools በነፃ መጠቀም ትችላላችሁ

#3
pexels.com

💡በዚህ ዌብሳይት ቪዲዮ ኤዲተር ከሆናችሁ የፈለጋችሁትን Stock video እና Picture በነፃ ማውረድ ትችላላችሁ

😊ሁሉንም ሞክሯቸው እና የተመቻችሁን ኮሜንት አርጉ 👇👇 መልካም ሰኞ ❤️


የጥንቃቄ መልዕክት

ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁት እና ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት እናሳስባለን


🎙ዋይርለስ ማይክ ጥራት ያላቸው ማይኮች  #20_ሜትር_ ርቀት_ድረስ የሚሰሩ በ 1 ካርቶን 2 ማይኮች የያዘ ለቪዲዮዋቹ ቮይስ በጥራት የሚቀዱ  ቪዲዮዋቹን የሚያሳምሩ በተመጣጣኘ ዋጋ አዲስ አበባ ቅርብ አካባቢ ላላቹ በእጃቹ ሞክራቹ ትወስዳላቹ📩

call 📞 0777403952 | 0941546755

👇in box
@Laday_33


YouTube Logo Evolution 📺


በኢትዮጵያ በጎግል ላይ ሰዎች በብዛት የፈለጉት ቃላቶች የትኞቹ ናቸው?

ጎግል በፈረንጆቹ 2024 ሰዎች በድረ ገጹ ላይ በመግባት በብዛት የፈረጉትን (ሰርች) ያደረጉትን ቃላቶች ይፋ አድርጓል።

1 ኢትዮጵያ (Ethiopia)

2 ዩ ትዩብ (youtube)

3 ትራንስሌት (Translate)

4 ጎግል (Google)

5 አፕ (app)

6 ዌዘር (weather)

7 ፕሪምየር ሊግ (premier league)

8 ቴሌግራም (telegram)

9 ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ (amharic to English)

10 ቤስት ቤት (best bet)

12 ፌስቡክ (facebook)

13 ጎግል ትራንስሌት (google translate)

14 ቲክቶክ (tiktok)

15 ሊቨርፑል (Liverpool)

©ዐል ዐይን

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጎዳና የታየችው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነችው ቴስላ ሳይበር ትራክ መኪናን ያስመጣው የፋሪስ ቴክኖሎጂ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆነው ኤልያስ ይርዳው ሲሆን ፋሪስ ቴክኖሎጂ በአይሲቲ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ኤሮስፔስ ላይ ተሰማርቶ እየሰራ የሚገኝ ኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


Wi-Fi ራውተር እና ADSL ምንድን ልዩነታቸው ምንድን ነው?

📍 Wi-Fi ራውተር በቀላሉ በዙሪያው ያሉ መሳሪያዎች ከኢንተርኔት ጋር እንዲገናኙ የሚያስችል መሳሪያ ነው። ይህ ማለት ስማርትፎንዎ፣ ላፕቶፕዎ፣ ታብሌትዎ እና ሌሎችም መሳሪያዎች በራውተሩ በኩል ወደ ኢንተርኔት መግባት ይችላሉ። ራውተሩ የሚቀበለውን የኢንተርኔት ሲግናል ወደ ገመድ አልባ (wireless) ሲግናል ቀይሮ በዙሪያው ያሉ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙበት ያደርጋል።

📍ADSL (Asymmetric Digital Subscriber Line) ደግሞ ከኢንተርኔት አቅራቢዎ ወደ ቤትዎ ወይም ቢሮዎ የኢንተርኔት ግንኙነት የሚያመጣ ቴክኖሎጂ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ በመሠረቱ የስልክ መስመርን ተጠቅሞ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል።
በአጭሩ፣ Wi-Fi ራውተር በቤትዎ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎችን ከኢንተርኔት ጋር የሚያገናኝ መሳሪያ ሲሆን፣ ADSL ደግሞ ከኢንተርኔት አቅራቢዎ ወደ ቤትዎ የኢንተርኔት ግንኙነት የሚያመጣ ቴክኖሎጂ ነው።

📍ልዩነታቸው

- ተግባር: Wi-Fi ራውተር የኢንተርኔት ሲግናልን በገመድ አልባ መልኩ በዙሪያው ያሰራጫል። ADSL ደግሞ ከኢንተርኔት አቅራቢዎ ወደ ቤትዎ የኢንተርኔት ግንኙነት የሚያመጣ ቴክኖሎጂ ነው።

- አይነት: Wi-Fi ራውተር አንድ መሳሪያ ነው። ADSL ደግሞ ቴክኖሎጂ ነው።

- አጠቃቀም: እያንዳንዱ ቤት ወይም ቢሮ Wi-Fi ራውተር ሊኖረው ይገባል። ነገር ግን ሁሉም ቤት ወይም ቢሮ ADSL ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ኢንተርኔት ላያገኝ ይችላል።
ምሳሌ:

📍 ቤትዎ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ግንኙነት ADSL ቴክኖሎጂን ይጠቀማል ብንል፣ ይህ ቴክኖሎጂ ከኢንተርኔት አቅራቢዎ ወደ ቤትዎ ያለውን ዋና የኢንተርኔት ገመድ በኩል ይመጣል። ከዚያም ይህ ገመድ በቤትዎ ውስጥ ካለው Wi-Fi ራውተር ጋር ይገናኛል። Wi-Fi ራውተሩ ደግሞ ይህንን ሲግናል ወደ ገመድ አልባ ሲግናል ቀይሮ በዙሪያው ያሉ መሳሪያዎች እንዲጠቀሙበት ያደርጋል።

📍በአጭሩ፣ ADSL ኢንተርኔትን ወደ ቤትዎ ያመጣል፣ Wi-Fi ራውተር ደግሞ በቤትዎ ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች በዚያ ኢንተርኔት እንዲጠቀሙ ያስችላል።

📍 ማስታወሻ: ዛሬ ላይ ADSL ከሌሎች ፈጣን የኢንተርኔት ቴክኖሎጂዎች እየተተካ ነው። እንደ ፋይበር ኦፕቲክ ያሉ ቴክኖሎጂዎች ከፍተኛ ፍጥነት ያለውና የተረጋጋ የኢንተርኔት ግንኙነት ያቀርባሉ።

📍 ሌሎች የሚዛመዱ ቃላት:-

- ራውተር (router): በአውታረ መረብ ውስጥ ውሂብን የሚያስተላልፍ መሳሪያ።
- ሞደም (modem): አናሎግ ሲግናልን ወደ ዲጂታል ሲግናል ወይም ዲጂታል ሲግናልን ወደ አናሎግ ሲግናል የሚቀይር መሳሪያ።
- ገመድ አልባ (wireless): ገመድ ሳይጠቀም ውሂብን የሚያስተላልፍ ቴክኖሎጂ።
- ኢንተርኔት አቅራቢ (Internet Service Provider): ኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥ ኩባንያ።

══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      


ለ 7 ቀን ብቻ ነዉ የሚቆየዉ የተባለዉ
Durov airdrop

የሚያልቅበት ቀን መቁጠር ጀምሯል😉

Invite ማድረግ እና ያሉትን Task ገብታቹ መስራት ብቻ ነዉ አሁን ጀምሩ።


👉 Start / ጀምር


https://t.me/DurovCapsBot/caps?startapp=487784393


SOSOVALUE NEW AIRDROP SEASON 2

በዚ ሊንክ ግቡ 👇 (Use Mises , Kiwi Browser )
https://sosovalue.com/join/449MQ888

Bonus ካልሰጣቹ Use Invite Code :-
449MQ888

እስካሁን ላልጀመራቹ ➡️
HERE


QR ማለት Quick Response ሲሆን በአማርኛ ፈጣን ምላሽ ማለት ነው። ይህ በስማርት ስልኮች ካሜራ በቀላሉ ሊቃኝ የሚችል የባርኮድ አይነት ነው። በውስጡ ብዙ አይነት መረጃዎችን ማከማቸት ይችላል።

QR ኮድ ምን ያህል ጠቃሚ ነው?

📍 ቀላል አጠቃቀም: ስማርት ፎንዎን በማውጣት ኮዱን መቃኘት ብቻ በቂ ነው።
📍ብዙ መረጃ: ዩአርኤሎችን፣ ስልክ ቁጥሮችን፣
ኢሜይሎችን፣ የካላንደር ዝግጅቶችን እና ሌሎችንም መረጃዎች ማከማቸት ይችላል።
📍 በየትኛውም ቦታ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል: መጽሔቶች፣ ፖስተሮች፣ ምርቶች እና ሌሎች ብዙ ቦታዎች ላይ ሊታተም ይችላል።

QR ኮድ እንዴት ይሰራል?

📍ኮዱን መቃኘት: ስማርት ፎንዎ ላይ ያለውን ካሜራ በመጠቀም ኮዱን ይቃኙ።
📍 መረጃን ማግኘት: ስልክዎ ኮዱን አንብቦ ውስጡ የያዘውን መረጃ ያሳየዎታል። ለምሳሌ አንድ ድህረ ገጽ ሊከፍትልዎት፣ አንድ ስልክ ቁጥር ሊደውልልዎት ወይም አንድ ኢሜይል ሊከፍትልዎት ይችላል።

QR ኮድ የት ይጠቀማል?

📍 ማስታወቂያ: ምርቶችን ለማስተዋወቅ እና ተጠቃሚዎችን ወደ ድህረ ገጾች ለመምራት ይጠቅማል።
📍 ክፍያ: ምግብ ቤቶች፣ ሱቆች እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ክፍያ ለመፈጸም ይጠቅማል።
📍 መረጃ ማጋራት: የእውቂያ መረጃ፣ የWi-Fi የይለፍ ቃል እና ሌሎች መረጃዎችን በፍጥነት ለማጋራት ይጠቅማል።
📍 ትራንስፖርት: ትኬቶችን ለመፈተሽ እና መረጃ ለማግኘት ይጠቅማል።

- QR ኮድ ለመፍጠር ብዙ ነፃ መሳሪያዎች አሉ። በኢንተርኔት ላይ በቀላሉ ፍለጋ በማድረግ ማግኘት ይችላሉ።

- ማስታወሻ: ሁሉም QR ኮዶች ደህንነታቸው የተጠበቀ አይደሉም። ከ አጠራጣሪ ምንጮች ከሚመጡ QR ኮዶችን መጠቀምን ያስወግዱ።


══════❁✿❁═══════                                                                           
🎮▩♦️.
@ELA_TECH                         
🎯▩♦️.
@ELA_TECH_GROUP          
🚀▩♦️.
@ELA_TECHBOT      

20 last posts shown.