“ሁለቱም የመስመር ተከላካዮች ቋሚ ተሰላፊዎቹ ተከላካዮቻችን ካጋጠማቸው ጉዳት በኋላ ድንቅ ስራ ሰርተዋል፤ ቫዝኬዝ እና ፍራን ጋርሺያ ከብዙ ጨዋታዎች በኋላ ጥሩ ስራ ሰርተዋል እናም ቡድኑን በእውነት ረድተዋል።”
“ስለ ቫልቬርዴ በአስቸኳይ ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር በቀኝ ተከላካይ ውስጥ ላጫውተው አላስብም።
አሴንሲዮን በቀኝ ተከላካይ ስለማጫወት? “እሱን እየሞከርን ነው እሱ የዛ ቦታ ባህሪያቱ አለው፤ ምንም እንኳን ከአጥቂነት የበለጠ ተከላካይነት ላይ ያዘነበለ ቢሆንም።”
ጁድ፣ ምባፔ፣ ቪኒ እና ሮድሪጎ አብረው ያሳዩት ብቃት? “በጉዳት ምክንያት አብረው ብዙ ጨዋታዎችን አላደረጉም፤ ነገርግን በአጠቃላይ ጥሩ መላመድ ሲያሳዩ አይቻለሁ። አንዳንድ ጊዜ ምባፔ ወደ ግራ እና ቪኒሲየስ ወደ ውስጥ ሲገባ ይታያል ወይም ደግሞ በተቃራኒው... 4ቱን ቋሚ ቦታ መስጠት አልፈልግም ይልቁንም ተንቀሳቃሽነት እና ነፃነት አላቸው።”
"ይህን እንቅስቃሴ ለማግኘት መሞከር አለብህ ምክንያቱም የአጥቂ አጨዋወታችን ወሳኝ ገጽታ ነው:: ምባፔ በቢዩልዳፕ ላይ በጣም እንዲሳተፍ አልጠይቀውም ምክንያቱም ችሎታው ከተከላካዮች ጀርባ በመሮጥ ላይ ነው። እሱን የምጠይቀው የበለጠ ወጥነት ያለው ነገር በየጨዋታው እንዲያደርግ ነው።”
ባለፉት 17 ዓመታት ውስጥ 2 ብራዚላውያን ካካ እና ቪኒ ብቻ በአለም ምርጥ ሆነው ተመርጠዋል፤ እና እርስዎ ያሰለጥኗቸው ነበር፤ ስለዚህ ቢነግሩን... “በራስ የመተማመን ስሜታቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ተሰጥኦ ያላቸው ተጫዋቾች የአለማችን ምርጥ የመሆን ዕድል አላቸው። በተመሳሳይ መንገድ በእያንዳንዱ ተጫዋች ላይ እምነትን መፍጠር አትችልም አንዳንድ ተጫዋቾች በዓለም ላይ ምርጥ የመሆን ጥራት ካላቸው በጊዜ ሂደት ይመጣል።”
@ETHIO_REAL_MADRID_15@ETHIO_REAL_MADRID_15