ሰላም ጋይስ እንዴት ናችሁ? እስቲ ሳምንታዊ የትሬዲንግ ጥሪዎቻችን እንዴት እንደነበሩ ለመመልከት እንሞክር። እንደሚታወቀው በመጪው የቡል ማርኬት በጋራ የምንጠቀምበትን መንገድ ለመፍጠር በማሰብ የተለያዩ የገበያ እይታዎቼን ማጋራት እንደምጀምር ካሳወኩ እና ያንንም ማድረግ ከጀመርኩ እነሆ 8ኛ ቀናችን ላይ እንገኛለን። እንዳጋጣሚ ሆኖ በተለይ ብዙዎቻችሁ እየጠበቃችሁ የነበረው የተለያዩ የአልት ኮይን ጥሪዎች በገበያው መውረድ ምክንያትነት ያን ያህል አመርቂ ጥሪዎችን ማቅረብ አልተቻለኝም ነበር። እንደምታውቁት በትሬዲንጉ አለም በትክክለኛ አመንክዮ ላይ ያለተመሰረተ ግብይት ከማድረግ በተሻለ ከናካቴው ትሬድ አለማድረግ አንዱ የስኬታማ ትሬደሮች ስትራቴጂ ነውና የቢትኮይን እንቅስቃሴ እስከሚለይለት እና አልት ኮይኖችም ከዚህ መሰሉ ተፅእኖ ሙሉ ለሙሉ ነፃ እሰክሚሆኑ ድረስ መጠበቅን መርጫለው። ይህንንም በዋናነት ያደረኩት በተለይ አብዛኛዎቻችሁ ለክሪፕቶ አለም አዲስ እንደመሆናችሁ ከሪስክ ማኔጅመንት ተጋላጭነታችሁ አንፃር ያለባችሁን ችግር ላለማባባስ እና ኪሳችሁንም ከኪሳራ ለመጠበቅ እንደነበር ልብ ይሏል።
ታዲያ በዚህ አካሄዳችን በአንድ ሳምንት ውስጥ አራት በተሳካ ሁኔታ ያለቁ የትሬድ ሴትአፖችን እና አንድ በአሁኑ ሰዓት እየተከወነ ያለ የግብይት ሁነትን በመጠራት ጥሩ የሆነ ሳምንትን እንደጅማሬያችን ሆኖልን ልናሳልፍ ችለን ነበር። እንደአጠቃላይ የነበረውን ሁነት ለማስታወስ ያህል፡
1/ የመጀመሪያ የገበያ ሁነት አካሄዱን ለመገምገም የሞከርኩት
ዴሴምበር 15 ላይ በነበረው የትሬዲንግ ቪው ቻርት እይታ ፖስቴ ላይ ቢትኮይን ከ102700 ዶላር በላይ ወዳለው እና ጠንካራ ወደሆኑት የ105 እና የ107ሺ የሬዚስታንስ እርከኖች እንደሚጓዝ ነበር። ይህ ሁነት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ ዲሴምበር 17 ላይ ቢትኮይን የምንጊዜም ከፍተኛ ዋጋ የሆነውን የ108353 ዶላር እርከን ሊነካ ችሎ ነበር። ✔️
2/ ይሁንና ይህ እርከን እጅግ የጠነከረ የሬዚስታንስ ዞን እንደመሆኑ እና ገበያው እያሳየ ከነበረው ደካማ አካሄድ በተጨማሪነት እና በዋነኝነት ደግሞ ሀውኪሽ የሆነ ውሳኔ የተሰማበት ዜና በአጠቃላይ ቢትኮይን አሳይቶ
የነበረው ጥንካሬ ሊከዳው እንደሚችል ማሳያ ሆኖን ቢትኮይን ቢሪሽ ሊሆን እንደሚችል 105 ሺህ የዋጋ እርከን አካባቢ ወደሽያጭ መግባት አዋጪ እንደሆነ ገምተን ነበር። ይህም ሁነት በተለይ በአንድ ቀኑ ቻርት ላይ አሳይቶን ከነበረው የዶጂ ካንድል ጋር በዋነኝነት የተወሰደ እንደነበር ይታወሳል። ✔️
3/ በሶስተኛው የግብይት አካሄዳችን ቢትኮይን በእለታዊ ቻርቱ ከሰራው የዶጂ ካንድል ባለፈ የመሰረተው
የራይዚንግ ዌጅ ቢሪሽ ፓተርን መሰበር በተጠናከረ ሁኔታ የገበያ ዋጋው የበለጠ ወደታች ሊጓዝ እንደሚችል ማሳያ ሆኖ እስከ 95700 ዶላር ድረስ የወረደበትን ሁነት ልንመለከት ችለን ነበር። ✔️
4/ከዚህ እርከን ሰበራ ሙከራ በኋላ ቢትኮይን ባደረገው መልሶ የማደግ እንቅስቃሴ ወደነበረበት የ6 ፊገሮች ዋጋ ይመለስ ይመስል የነበረ ቢሆንም እንደአለበት የዋጋ ጣሪያነት እና ቢሮች እንደነበራቸው ጥንካሬ
አሁንም መልሶ ሊወርድ እንደሚችል ያሳየንበት እና ያንንም ሁነት ያረጋገጠበትን ሁነት ልንመለከት ችለን ነበር። ✔️
5/ በስተመጨረሻ አሁንም በስራ ላይ ያለው
የመጨረሻው የትሬድ ሴትአፓችንን በአንድ ቀኑ ቻርት ላይ ባገኘነው የቡሊሽ ሜጋፎን ፓተርን እና በኢቺሞኩ ክላውድ ባህሪያቱ ምክንያት ሲሆን በተለይ አሁን ባለበት አካሄድ እስከ 90ሺህ የአሜሪካን ዶላር ሊወርርድበት የሚችል እድል ያሳየንበት ነበር። ይህ ትሬድ በአጭር ጊዜ የግብይት ታይም ፍሬም ላይ ለሚገበያዩ ቤተሰቦች ጥሩ የሆነ እድል የሰጠ ቢሆንም እንደገበያው ኢተገማችነት እስካሁን የደረሰበት የ92500 ሺህ እርከን ድረስ ባለው ሁነት የትሬዳችንን 50 በመቶ ይዘን መውጣት የምንችልበትንም እድል የሰጠን ሆኖ እናገኘዋለን። 🟢
በዚህም በአጠቃላይ ከአልት ኮይኖች ውጪ በዋነኝነት በቢትኮይን ላይ አተኩሮ ባለፈው የትሬዲንግ ሳምንታችን ቢትኮይን ከ102700 ወደ 107000 እንደሚያድግ፤ ከ105000 ወደ 95000 እንደሚወርድ እና በድጋሚም ከ95000 ወደ 90ሺህ የገበያ ዋጋ እርከን እንደሚወርድ የወሰድናቸው ቅድመግሞቶች ሁሉ በተሳካ ሁነት የተፈፀሙ መሆኑ ለማስሳወቅ እወዳለው።
እንዳጠቃላይ ያለንበትን አሁናዊ ሁነት በተብራራ መልኩ ገበያው ሁነኛ እንቅስቅሴዎችን በሚያሳይበት ቅፅበት update የማደርጋችሁ ሲሆን በተቻለ የሪስክ ማኔጅመንት ህጋችሁን አጠንክሩ እንጂ እኔ የሰራሁትን ሁሉ አብሬ ላሰራችሁ ቃሌም እንደሆነም ለማሳወቅ እወዳለው።
በተረፈ በተለይ የሜም ኮይን ጥሪዎች እጅግ በጣም በጣም በጣም ከሚታሰበው በላይ ቁምራዊ ባህሪይ ያላቸው በመሆናቸው ከእኔ በተለይ በሺት ኮይን ደረጃ ያሉ እንደጋምብል የሚታዩ የክሪፕቶውን ስፔስ የሚያጠለሹና የማይወክሉ ጥሪዎችን ከወዲሁ እንዳጠብቁ አበክሬ ለማሳወቅ እወዳለው። ይልቅስ የአልት ኮይኖችን እንቅስቅሴ በደንብ ተከታትዬ ከጨረስኩና ገበያውም ጥሩ መነቃቃትን ካሳየ በኋላ ከሞላ ጎደል ከሪስክ ነፃ የሆኑ ኮይኖችን እየጠራሁ ፍርቱናችንን የፈቀደልልን ልኬት ሁሉ በአንድ ላይ የምንበላ ይሆናል።
መልካም ምሽት በያላችሁበት።
💚💛❤️