#ህወሓት ጠቅላል ጉባዔ እንዲያካሂድ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ቀነ ገደብ እንደማይቀበልና መንግስት"የ #ፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ እንዳይተገበር እንቅፋት መሆኑን” ገለጸ‼️
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ የ #ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው ጠቅላል ጉባዔ እንዲያካሂድ ቀነ ገደብ መሰጠቱን እንደማይቀበል አስታወቀ።
ማዕከላዊ ኮሚቴው ከጥር 5 እስከ ጥር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ያደረገው ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ “ ህወሓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የተናጠል ውሳኔ ዛሬ ይሁን ነገ አይቀበልም" ሲል ገልጿል።
ህወሓት ነሀሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም “በልዩ ሁኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ” መመዝገቡ ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲው እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም እንዲያደርግ አሳስቧል።
ይሁን እንጂ ቦርዱ ፓርቲው ለጠቅላላ ጉባዔው ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ምንም ምልክት እንደሌለው ገልጾ፣ በቦርዱ የተላለፉትን ውሳኔዎች በወቅቱ ሳይፈፀም ቢቀር ሕጉን መሠረት ያደረገ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በመግለጫው ምርጫ ቦርድ “ለኮንግረሱ ቀነ ገደብ ከመስጠት የተፈጠሩ ልዩነቶች በፓለቲካዊ ውይይት ለመፍታት የተጀመረው ጥረት ማስቀጠል ላይ ትኩረት ያድርግ” ሲል ገልጿል።
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) የሚመራው ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴው፤ ፌዴራል መንግስቱ "የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በአግባቡ እንዳይተገበር እንቅፋት እየሆነ ነው” ብሏል። ፓርቲው በትግራይ ውስጥም "ከሃዲ ኃይሎች" ሲል የጠራቸው አካላት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይደረግ እንቅፋት እየሆኑ ነው ሲልም ስጋቱን ገልጿል።
በተጨማሪም መግለጫው፤ ተፈናቃይ እና ስደተኞች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው “ሃዘን እና ቁጣ ተስምተኞናል” ሲል ገልጾ “ይበቃል” በሚል በመቀለ የተካሄደው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚደግፍ አስታውቋል።
=======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት 👉
@Akiyas21bot @ET_SEBER_ZENA@ET_SEBER_ZENA