የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክርስቲናያን መንፈሳዊ ትምህርቶች እና ጽሁፎች ቻናል⛪️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የዚህ ቻናል ዋና አላማ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መምህራን ትምህርቶችና ጽሑፎችን የሚናስተላልፍ የተዋህዶ ልጆች ቻናልነዉ
1ኛቆሮንቶስ1÷23፤እኛ፡ግን፡የተሰቀለውን፡ክርስቶስን፡እንሰብካለን፤ይህም፡ለአይሁድ፡ማሰናከያ፡ለአሕዛብም፡ሞኝነት፡ነው
24፤ለተጠሩት፡ግን፥አይሁድ፡ቢኾኑ፡የግሪክ፡ሰዎችም፡ቢኾኑ፥የእግዚአብሔር፡ኀይልና፡የእግዚአብሔር፡
ጥበብ፡የኾነው፡ክርስቶስ፡ነው።
ማነኛው አስተያየት
@geremch. @Aboyite.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter












ተአምር ሚካኤል


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
#ድምፅ_መስጠት_ተጀመረ!

#አንቴክስ_ፉድ_ኤይድ_ፕላስ ባዘጋጀው BIWs prize ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን የሰላም ዘርፍ እጩ ተሸላሚ አድርጓቸዋል።

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በሰላም ዘርፍ ከአምስት እጩዎች ውስጥ ተክትተዋል የዘርፉ አሸናፊ ከሆኑ #10ሚሊየን ብር ይሸለማሉ!!!

ብፁዕነታቸውን BIWን በማስቀደም ኮድ08 (BIW08) በማስገባት በSMS 9355 ላይ አሁኑኑ ይምረጡ!!! 

ድምጽ መስጠቱ እስከ ሐሙስ ታህሳስ 17/2017 ዓም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

በSMS 9355 ላይ BIW08 በማለት ብፁዕነታቸውን አሁኑኑ  ይምረጡ!!!

#10ሚልዮን #አንቴክስ #ፉድኤይድፕላስ #biwsprize #BTM #ብፁዕአቡነኤርምያስ  #ይምረጡ

Vote Abune Ermias now for the BIWs prize!

#AbuneErmias
#10million #BIWS2024 #Prize  #ANTEXETHIOPIA  #ANTEXTEXTILE  #FOODAIDPLUS #BESHATUTOLEMARIAMMULTIMEDIA


በልቡ የላይኛውን የሚያስብ ሰው✝
                         
Size 60.5MB
Length 1:05:21

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ


ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ /2/
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ
የፍቅርን ሕይወት እንድትለብሱ
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ
አዝ

ሁሉን በሚችል በአምላክ ጥላ
በእረፍት ውኃ ስር አርፈናልና
ሰላምና ፍቅር ሕይወት በሚሰጥ
ወደ ጌታችን እንሂድ እንሩጥ
አዝ

ምሕረትና ፍርድ በእጁ የያዘው
የሰላም አባት መድኅኔዓለም ነው
ሕይወት የሆነን በመስቀል ውሎ
ብርሃንን ሰጠን ጨለማን ሽሮ
አዝ

የሚያስደነግጥ የሚያስጨንቀን
ይጠፋልና እርሱን ተማጽነን
በቀን ከሚበር ፍላጻ ሁሉ
ይታደገናል በቅዱስ ቃሉ
አዝ

እግርህ በድንጋይ እንዳይመታ
በፈተና ውስጥ እንድትበረታ
መቅሠፍት ከቤትህ እንዲከለከል
ይጠብቅሃል ሌሊትና ቀን
አዝ

ስሙን ያወቀ ሕይወት መሆኑን
ይመላለሳል ከኀይል ወደ ኀይል
ረጅም ዕድሜ ይጠግባል እርሱ
ብርሃን ይሆናል የጸጋ ልብሱ
አዝ

አቤቱ አንተ ተስፋ ነህና
የምትመግብ የፍቅር መና
ማዳንህ እኛን አስደስቶናል
እንዲህ ያለ ክብር ከየት ይገኛል

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለተዋሕዶ ልጆች👇
               


አንቺን የያዘ ሰው

አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ/2/
አዝ

በረከትሽ ብዙ የደናግል ገንዘብ
የምስኪናን እናት የርሁባን ቀለብ
ለሁሉ መጋቢ ጸጋሽ የማይጎድል
ስምሽ ጥዑም ምግብ ከረሀብ የሚያስጥል/2/
አዝ

አንቺ ብትመጪ ከምስኪኗ ቤቴ
እንደ መጥምቁ እናት በዛልኝ ሐሴቴ
የአዲስ ኪዳን ቁርባን መንበር ጠረጴዛ
ጽድቅን አሸተትን የሕይወትሽን መዓዛ /2/
አዝ

ልቤ ተጠራጥሮ ኪዳንሽን ካልከዳ
ልመናም አልወርድም አልይዝም አቁፋዳ
ሁሉን እየሞላሽ መመገብ ታውቂያለሽ
ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋና ሀብት አለሽ/2/
አዝ

የእግዚአብሔር ማረፊያ ኮሬባዊት ዋሻ
የሕይወት ውሃ ምንጭ የህግ መፍሰሻ
ነበልባል ተዋህዶሽ ሙሴ አንቺን አይቷል
ጫማውን አውልቆ በፊትሽ ተደፍቷል /2/

ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
ለተዋሕዶ ልጆች👇
               


Forward from: መደኃኔዓለም ወቅዱስ ዮሐንስ ማህበር










እንደ ኤልሳቤጥ ላመስግንሽ

እንደ ኤልሳቤጥ ላመስግንሽ
ፊትሽ ወድቄ ልሳለምሽ
የጌታዬ እናት የእኛ እመቤት
አዛኝ ነሽ ከልብ ፍጹም የዋህት
አዝ

ርኀራኄሽ ያስደንቀኛል
ስለ ኃጢአቴ ምልጃሽ ይቀድማል
የሰላምታሽ ድምፅ ደስ ያሰኘኛል
ከትካዜዬም ያሳርፈኛል
አዝ

ድምፅሽ ሲሰማኝ ልቤ ይረካል
ሃዘኔ ቀርቶ ፊቴ ይፈካል
በእናትነት አንቺን ለሰጠን
ቸሩ አምላካችን ይክበር ይመስገን
አዝ

የሁሉ እመቤት የሁሉ አጽናኝ
የአበዉ መድኀኒት ከአምላክ አገናኝ
ዛሬም በልቤ ደስታን ጨምረሽ
እንደ ኤልሳቤጥ ሰላም ልበልሽ
አዝ

ከሴቶች መካከል መርጦ ቀድሶሻል
ትዉልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉሻል
በልዩ ወዳሴ ያመሰግኑሻል
ድንግል ንግሥታችን በቀኙ ቆመሻል
አዝ

የሰላሞታሽ ድምፅ ልቤ ሲሰማ
ነፍሴ ደስ አላት ቀለለ ሸክሟ
ድንግል ለክብርሽ ስንበረከክ
እጅሽ ይዘርጋ ለመባረክ

የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አድርሱ
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
    




Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
🗓 ነገ ማለትም
#ዕለት:- ረቡዕ
#ቀን:- ታኅሣሥ ፪  ፳፻፲፯ ዓ.ም

በቅድስት ቤተክርስቲያናችን
ሐዋርያዉ ታዴዎስ ፣ ሠለስቱ መዕት ፣ ቅድስት አትናስያ ፣ አቡነ እንድርያኖስ ፣ ቅድስተ ዜና ማርቆስ ፣ አባ ጉባ

አክብረን እና አስበን እንውላለን።

📣📣📣
✔️ የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው። ምሳ ፲፤፯

✔️  መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል መዝ.፻፳፮፥፮


✔️ "ቅዱሳን በዓለም ላይ እንዲፈርዱ አታውቁምን? ፩ኛ ቆሮ ፮:፪

የመላዕክት ፣ የቅዱሳን ፣ የሰማዕታት ተራዳይነት እና በረከት ከሁላችንም ጋር ይሁን።

#ድምፀ_ተዋህዶ


Forward from: 🎤✨ድምፀ ተዋህዶ✨🎤
✨አንድ ትእቢተኛና ልብ አውልቅ ተማሪ
መምህሩን ሊሳለቅባቸው አሰበና "የኔታ ገሀነም በየት በኩል ነው ?"

አላቸው።የኔታም የውስጡን አውቀው "ልጄ እመንገዱህ ላይ ነህ ......"አሉት ይባላል

✨#ድምፀ_ተዋህዶ✨


Forward from: ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
"የዝናም አባቱ ማን ነው?" (ኢዮ. ፴፰:፳፰)
(መኑ አቡሁ ለዝናም?)

☞ገድለ አቡነ ዮሐንስ (ዘደብረ ቢዘን)

☞ወአበው ቅዱሳን መርትያኖስ ወዳንኤል
☞ቅድስት ደብረ ቀልሞን

https://t.me/zikirekdusn

20 last posts shown.