ELSHIO ACADEMY ™


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ሰላም👋 እንኳን   ወደ ቻናላችን በሰላም መጣችሁ
በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ጠቃሚ ነገሮች
🟡entrance exam
🟡extreme book & referance book
🟡Textbook ( 9-12 )
🟡Teachers Guide (9-12)
🟡worksheet ( 9-12)
🟡Exit Exam እናም  ሌሎችም
@Elshio_Academy
በእነዚህ ቻናል ያገኛሉ
CONTACT @elshio_ACADEMY_BOT

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


🍿 ትርጉም ፊልም🍿

⚡️ በየቀኑ የሚወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ  ተከታታይ : እንግሊዝኛ ፊልሞች በትርጉም እንዲሁም አማርኛ ፊልሞች በነፃ የሚለቀቁበት ቻናል
Join የምትለዋን ጠቅ አርገው ፊልም መኮምኮም
ብቻ 👇🤗


I am so into you.

#ELSHIO_Academy

👍.ወድጄሻለሁ

😎.ተቀይሜሻለሁ

❤️.ኮርቸብሻለሁ

⚡️.አፍሬብሻለሁ

✅ React to right Answer ✅


በአፋጣኝ [ኢሚድየትሊ] ሲፃፍ ፦
Poll
  •   A, Imidiately
  •   B. Immediately
  •   C Immediay
  •   D Immideatly
195 votes


#MekelleUniversity

በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ፀድቆ የተላከው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወጥ-የሆነ የምግብ ሜኑ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከቅዳሜ ታህሳስ 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ አንድ ዳቦ ለቁርስ እያቀረበ እንደሚገኝ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት ዩኒቨርሲቲው መጠናቸው አነስተኛ የሆነ ሁለት ዳቦ ለቁርስ ያቀርብ እንደነበር ተማሪዎች አስታውሰዋል፡፡

"ዕለታዊ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ተመን ወጪ አንድ መቶ ብር በሆነ ማግስት፥ አንድ ዳቦ ለቁርስ ማቅረብ ማሻሻል አይደለም" ሲሉ ተማሪዎቹ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እንዲሆን መንግሥት መወሰኑ ይታወቃል። በዚህም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ ተመሳሳይ የምግብ ሜኑ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተልኳል፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ የተማሪዎች ህብረት ጋር በመነጋገር የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የምግብ ሜኑን አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መግባቱን ገልጿል። (አዱሱ የዩኒቨርሲቲው ሜኑ ከላይ ተያይዟል)

በማሻሻያውና በቀረበው የዳቦ መጠን ላይ ደስተኛ ያልሆኑ የዋናው ግቢ እና የዓዲ ሓቂ ግቢ ተማሪዎች ድርጊቱን በመቃወማቸው ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

የክልሉ ፓሊስ ኮሚሽን ወደ ካምፓሶቹ የፀጥታ አካላት መላኩ ተነግሯል። በፓሊስ እና በተማሪዎቹ መካከል በተፈጠረ ግጭት ተማሪዎች የድብደባ ጥቃት እንደደረሰባቸው ተነግሯል። በዋናው ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን፤ ይህንንም ተከትሎ የታሰሩ ተማሪዎች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በሁለቱ ካምፓሶች የተፈጠረው ግርግር በአሁኑ ሰዓት ሙሉ በሙሉ መቆሙ ታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ "በምግብ ሜኑው ላይ የሚስተካከሉ ነገሮች ካሉ ብሔራዊ ሜኑ በይዘት እና በጀት ደረጃ እስካልተለየ ድረስ ጥያቄዎች በተማሪዎች ህብረት በኩል ቀርበው ማስተካከል እንደሚቻል" ገልጿል፡፡ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በሰላማዊ መንገድ መግለፅ እንዳለባቸውም ጠቁሟል፡፡

ከሚመለከተው የማኔጅመንት አካላት ጋር ውይይት መጀመሩን የገለፀው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሀብረት፤ "ያለአግባብ የታሰሩ ተማሪዎች እንዲፈቱና ያለ በቂ መረጃ በተማሪዎች ላይ እርምጃ እንዳይወሰድ" ጠይቋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀው አዲሱ የምግብ ሜኑ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እስከሚሆን ድረስ ነባሩ ሜኑ እንዲቀጥልም ህብረቱ ጥሪ አድርጓል፡፡

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረው ጉዳይ ላይ ይፋዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡




#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ የ PhD ፕሮግራም መስጠት ጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው PhD in Coffee Science የመጀመሪያ ቀን ትምህርት የመጀመሪያ Class በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ታሪክ በቡና ሳይንስ የ PhD ፕሮግራም በመጀመር ቀዳሚው ዩኒቨርሲቲ ሆኗል።

በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸው 34 ተማሪዎች ባለፈው ሰኔ ያስመረቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በመስኩ በማስተርስ መርሐግብር ተማሪዎችን በማሰልጠንም ላይ ይገኛል።


ከ ZOO Airdrop እንዴት ጥሩ ነገር ማግኘት እንችላለን ?

ብዙዎቻቹ Airdrop ላይ ጥሩ ተሳትፋቹ ነገር ከ20$ - 30$ ብቻ ሲሰጣቹ ታማርራላቹ ወይም በቶሎ Give up እናረጋለን ስለዚህ በAirdrop ተጠቃሚ ለመሆን ደሞ የሚጠየቁትን criteria ማሟላት ነው

ZOO Airdrop ላይ ጥሩ ለመስራት እነኚን አሟሉ

1. Active ሆኖ መስራት እና እንስሳቶችን feed እያረጋቹ upgrade ማድረግ

2. ሰዎችን invite እያረጋቹ መጋበዝ

3. invest እያደረጋቹ መስራት ነው ምክንያቱም Token allocate በሚደረግ ጊዜ invest ያደረገው ካላደረገው በላይ ቶክን ስለሚሰጥ ባላቹ በትንሽም ቢሆን invest እያደረጋቹ መስራት ጀምሩ

እነኚን criteria ካሟላቹ በርግጠኝነት ከ Airdrop ተጠቃሚ መሆን ትችላላችሁ ።

@Elshio_Academy
@Elshio_Academy
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref1349797780

t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref1349797780


#BoranaUniversity

በ2017 ዓ.ም ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 እና 23/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ብርድልብስ እና ትራስጨርቅ።


✨ Share with your  Friend

@Elshio_Academy
@Elshio_Academy


Hi! We ___ before, have we ?
#ELSHIO_Academy

❤️. never

👍. haven't

✅ React to right Answer ✅


#UniversityofGonder

በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት 👉 ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል።


የምዝገባ ቦታ፡- ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

💥ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትሄዱ ከዚህ በታች የተገለጹትን ይዛችሁ እንድትሄዱ

✓ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ

✓ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ

✓ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ዋናን እና የማይመለስ ኮፒ

✓ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ

✓ አንሶላ፣ ብርድ ልብስና የትራስ ልብስ

(ሬጅስትራር ጽ/ቤት)

@Elshio_Academy
@Elshio_Academy


Reported speech የምንጠቀምበት ስሙ ራሱ እንደሚገልፀው report ስማደርግ ወይም ሌላ ሰው (ራሳችን) ከዚህ በፊት የተናገረውን ቃላት/ንግግር ለመዘገብ ወይም ለማስተላለፍ ነው።

Eg: He told me "I'm sick now."

መጀመሪያ [1] :- Quotation (ጥቅሶቹን) እናጠፋና በመቀጠል reporting verbs እንጨምራለን ብዙ ጊዜ የምንጠቀምባቸው reporting verbs : said, told, asked, ordered ናቸው።

✅ He told me that
❌ He told that አይባልም
✅ He said that
❌He said me that አይባልም
[told, asked የሚለው ስንጠቀም ከሱ ቀጥሎ objective pronouns (me, her, him, us, them) መጨመር መርሳት የለብንም። said ስንጠቀም ግን አንጨምርም።]

ሁለተኛ [2] ፦ Pronouns መቀየር
✅ He told me that he ...
✅ He said that he...
እዚ ላይ I የነበረውን ወደ he እና you የነበረውን ወደ her ቀይረናል

ሶስተኛ [3] ፦ የተፃፈበትን tense ወደኋላ አንድ tense መመለስ Present simple ከነበረ ወደ Past simple...
✅ He told me that he was sick ...

አራተኛ [4] ፦ የጊዜ እና ቦታ ቃላቶችን መቀየር
now - then • today • that day...

✅ He told me that he was sick then.
✅ He said that he was sick then.

ትእዛዝ ሲሆን ደሞ ordered የሚለውን reporting verb እንጠቀማለን።

"Study your lesson." He ordered me.
ሲቀየር He ordered me to study my lesson.

እዚ ላይ ከሌሎቹ የተለየ ነገር ያለው ordered ብለን objective pronoun እና to እንጨምራለን።

💎 ትእዛዝ ሲሆን tense ወደ ኋላ አንመልስም። እውነታ ሲሆን ወይም አሁንም ድሮ የተናገረውን ካልተቀየርም tense ወደ ኋላ ሳንመልስ report ማድረግ እንችላለን።
✅ He said "I work in an office." አሁንም እዛ የሚሰራ ከሆነ He said that he works in an office. ማለት እንችላለን።

💎 ጥያቄ ሲሆን ደሞ if ወይም whether ን እንጨንራለን።

He asked me "Can you give me some money?"
He asked me if I could give him some money.

share share

https://t.me/Elshio_ACADEMY
https://t.me/Elshio_ACADEMY


📑 የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ምን ላይ ናችሁ ?ምን እያሰባችሁ ነው ? ምንስ ይሰማችኋል?


#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ  ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ የጥሪ መልዕክት ስህተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

✨ Share with your  Friends
 


#HaramayaUniversity

በ2017 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥር 2-4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
የኅብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በቬተርነሪ ካምፓስ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ካምፓስ።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➫ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ እና ትራስ ልብስ

✨ Share with your  Friends
 


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ የጥሪ መልዕክት ስህተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡


አስደሳች ዜና

እንዲሁም  የአምና የ 2016 በድብቅ የተቀረፁ  የሪሜዲያል ፈተናዎችን በቴሌግራም ቻናላችን ላይ ታገኛላችሁ 

በ 2017 የሪሜዲያል ተፈታኝ ከሆናችሁ ግዴታ መቀላቀል አለባችሁ ።


           ቴሌግራም ቻናል ሊንክ 👇
           https://t.me/RE0707MAR


👉 Zoo ኤርድሮፕ

Zoo ኤርድሮፕ  በPPH ቶክን መሰብሰብ ነው።

ምሳሌ ስትጀምሩ 1000 animal feed ተሰጥቷቹ ከታስክ ጭምር በምታገኙት Animal ብትገዙ እሱን እያሳደጋቹ ሌላም እየጨመራቹ ብዙ ቶክን መሰብሰብ ትችላላቹ

ብዙ ቶክን መሰብሰብ ለምትፈልጉ ብዙ Animal feed ለማግኘት በስታር ማሳደግ ትችላላችሁ።

Daily check በየቀኑ Animal feed ይሰጣል + Riddle of the day በየ ቀኑ 1,000 Feed ይሰጣል በብዙ አካውንት ብትሰሩት ጥሩ ነው።

ለመጀመር 👉Zoo

ለመጀመር
ለመጀመር
ለመጀመር

👆በመንካት ይደምሩ 👆
@Elshio_Academy
@Elshio_Academy


ከተለመደው የተለየ ጎበዝ  ለማለት  በእንግሊዘኛ ፦

👍.Best

❤️.Ambitious

🥰.extraordinary

👏. Animosity

✅ React  to the right  Answer ✅


አንዲት ሴት እንዲህ ትላለች...

ቤቴን አጽድቼ ካስተካከልኩ በኋላ ወንድሜ ደወለ...ከባለቤቴ ጋር ልንጠይቅሽ እንመጣለን ኣለኝ። ኩሽና ገባሁ ለእንግዶቸ ያለኝ ላዘጋጅ።

ለመስተንግዶ ምንም አላገኘሁም! አንድ ነገር ላቀርብላቸው ብፈልግ፡ ምንም ማግኘት ኣልቻልኩም ጥቂት ብርቱካን ብቻ አገኘሁ… እናም ወዲያውኑ ሁለት ብርጭቆ ቀዝቃዛ ጭማቂ አዘጋጀሁ።

ወንድሜ እና ሚስቱ ሲገቡ ለመጀመሪያ ጊዜ እየጎበኘችን ያለው የወንድሜ ሚስት እናት ከሳቸው ጋር ነበረች።

ሁለት ብርጭቆ ለሚስቱና እናትዋ ኣቀረብኩላቸው። ኣንድ ብርጭቆ ውሃ ደግሞ ለወንድሜ። 7up እንደምትወድ ኣቃለሁ ኣልኩት።

ትንሽ ጠጣና ውሃ መሆኑን ኣወቀ። እናትየዋ እኔ 7up ነው የምፈልግ ለሆዴ ይመቸኛል እና ስጡኝ.. ትላለች። ግራ ገባኝ ደነገጥኩ …

ወንድሜ እንዲህ ሲል አዳነኝ: - አዲስ ብርጭቆ ከኩሽና ኣመጣለሁ ብሎ ብርጭቆውን ይዞት ሄደ። ከዚያም የጠርሙሱ መሰበር ድምፅ ሰማን፡

እናም ተመልሶ መጥቶ አማቱን እንዲህ አላት... የሚያሳዝነው ከኔ ወድቆ ብርጭቆውን ተሰበረ.. ግን ምንም አይደለም ሌላ ላመጣሽ ወደ ግሮሰሪ እሄዳለሁ... ኣላት።
አማቹ አያስፈልግም አለች...

ሲወጡ ወንድሜ ሲሰናበተኝ፡ አቅፎ በእጄ ገንዘብ አስጨበጠኝና እና እንዲህ አለኝ: ​​-ከኩሽናው 7up ማጽዳት እንዳትረሺ፡ ጉንዳኖችን እንዳያመጣ! ብሎ በፈገግታ እና በፍቅር ተሰናበተኝ..።
ራስሺን ተንከባከቢ ኣለኝ።
በዚህ መንገድ... ወንድሜ ጭንቀቴንና ጉድለቴን ሸፈነልኝ.. ስሜቴን ጠበቀልኝ..

ወንድማማችነት እንዲህ መሆን ኣለበት...

20 last posts shown.