#እንኳን_አደረሳቹ #ታኅሳስ_19
"እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" (ሉቃ 1:19) እና ስለ ነቢዩ ሙሴ "... ስለ ሕዝቡ ባይቆም ኖሮ ሊያጠፋቸው ተናገረ።" (መዝ 125) ... ሁለቱን አነጋገሮች እናስተውላቸው። አንዱ በዚህች ምድር የተደረገ "ስለ ሕዝብ መቆም" (ምልጃ) ነው። ሌላው ደግሞ በመንፈሳዊው ዓለም በቅዱሳን መላእክት የሚደረግ "መቆም" (ምልጃ) ነው። አንዱ በእስንፋሰ እግዚአብሔር ዘመድ በሆነ (በሰው) የተደረገ ነው።... ሌላው ደግሞ በፍቅር እና በመንፈሳዊ ኅብረት አዛማጅነት የሚደረግ ነው።... ሰው ከክርስቶስ በተቀበላት ቤተ ክርስቲያን እና ቤተ ክርስቲያንነት በእርሱም ትክክለኛ እውነታ (Reality) ቅዱሳን ምልጃን ያደርጋሉ። ... በሌሎች ሰዎች የሕይወትና ሞትን መንፈሳዊ ትርጉም ባላገናዘበ፣ ክርስቶስ መጥቶ የ3 ዓመት ትምህርትን "በግል ለግል ያስተማረ" ይመስል ቤተ ክርስቲያንን "ግል" (individual) ብቻ ባደረገው አስተሳሰብ፣ የእውነት ውሏን በትሕትና ከመፈለግ ከማግኘትም ይልቅ በቲፎዞነት፣ "ከእኔ (ከእኛ) በላይ አዋቂ" በሚል የኅሊና ጥመት ባደከመው ዘንድ ቅዱሳን አይማልዱም። ሰው "ጌታ ይበቃኛል" በማለት ራሱን ያታልላል እንጂ "እኔ ለራሴ እበቃዋለሁ" እያለ መሆኑን ከመረዳትም የዘገየ ነው።
የመልአኩን ረድኤት አይለይብን። በቅዱሳን ጸሎት ይማረን።
(ዲያቆን ሚኪያስ አስረስ)
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ