✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ይህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ታላላቅ የድሮና አዳዲስ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቁ መጽሐፍት በPDF ያቀርባል
አቤኔዘር ዘተዋህዶ
https://youtube.com/@Abeenezar_mulu
ለማስታወቂያ ስራ
👇
@asrategabriel
@lesangeez127
@Orthodox_Addis_mezmur
@Orthodox_spiritual_poems
@Eotc_books_by_pdf_group

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter




ራዕይ  ምንድን ነው?
ከስኬት ጋር ምን ያገናኘዋል?

ለአዲስ ዓመት እራሳችንን እንዴት እናዘጋጃለን

በተጨማሪ  ሙሉ ትምህርት በተከታታይ ይቀርባል ጥያቄ አስተያየት ከአላቸው እዛው ላይ አስቀምጡ። 

አንዳንድ ትምህርቶች በነፃ ስታገኙ  በደንብ ተጠቀሙበት

https://youtu.be/h_BTAT24h_o?si=b5WogLDi1xqlJC1Z

https://youtu.be/h_BTAT24h_o?si=b5WogLDi1xqlJC1Z


ለእናንተ በጣም አስፈላጊ ትምህርት ነው ስለእውነት በደንብ ተማሩ  

በቀረው እግዚአብሔር ይጨመርበት


እንኳን አደረሰን

👉 የዛሬው ይሄው
✅  ሁሌም በቀን አንድ በቲክቶክ  ቪዲዮ ያግኙ  


የህይወት ልምድ ከስነልቦና ባለሙያ Bini Girmachew

https://vm.tiktok.com/ZMrW31Xo5/
https://vm.tiktok.com/ZMrW31Xo5/




​​​​ፍልሰታ ምን ማለት ነው⁉️

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ለዚህ ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ "ፍልሰታ ማለት ፈለሰ /ተሰደደ/ ከሚለው ግስ የወጣ ነው።"

‹ፍልሰት› ማለት ደግሞ የተለያየ ትርጕም ቢሰጠውም ‹ፍልሰታ  ለማርያም› ተብሎ ሲገለጽ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው  ወደ ማያልፈው ዓለም ከመቃብር የወጣችበት (የተነሣችበት) ቀን ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ ከሥጋዊው ዓለም ወደ መንፈሳዊው ዓለም የተሸጋገረችበት ማለት ነው፡፡››

ቀሲስ ስንታየሁ አባተም በተመሳሳይ መልኩ ስለ ፍልሰታ እንዲህ በማለት ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡ 

‹ፍልሰታ ለማርያም› የሚለው የግእዝ  ቃል ሲኾን ‹ፍልሰታ› ማለት ደግሞ ‹ፈለሰ› ከሚል ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ‹ፍልሰት› ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ መሔድን (መፍለስን) ያመለክታል፡፡ እመቤታችን ካረፈች በኋላ የሥጋዋን መፍለስ አስመልክቶ ሐዋርያት የእመቤታችን ሥጋ የት እንደ ተቀበረ አላወቁም ነበርና እግዚአብሔር የእመቤታችንን ሥጋ እንዲገልጥላቸው የጾሙት ጾም ነው፡፡

ሐዋርያት ሁለት ሱባዔ ጾመው የእመቤታችንን ሥጋዋን ሰጥቷቸው  ትንሣኤዋንና ዕርገቷን በማየት በረከት ያገኙበት ጾም ነው፡፡ ስለኾነም ምእመናን ፍልሰታ ለማርያምን ከልጅ እስከ አዋቂው በጾም በጸሎትና በመቍረብ በጋራ በፍቅር፣ በሰላም ያሳልፉታል፡፡›› 

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እንዳብራሩት ቅዱስ ዮሐንስ እመቤታችንን እንዲጠብቃት ከተደረገ በኋላ ሐዋርያት ‹‹የእመቤታችን ነገር እንዴት ነው?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹እመቤታችንማ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ናት›› ብሎ ነገራቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ሐዋርያት እመቤታችን ከመቃብር መነሣቷንና ማረጓን ማየት አለብን፤ እንዴት ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ እንቀራለን ብለው በመንፈሳዊ ቅናት በመነሣሣት ነሐሴ አንድ ቀን በዕለተ ሰኞ ሁለት ሰባት ሱባዔ ያዙ፡፡ በዐሥራ አራተኛው ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ሥጋ አንሥቶ ሰጣቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ እመቤታችን በ፷፬ ዓመቷ ጥር ፳፩ ቀን ዐርፋ ነሐሴ ፲፬ ቀን ተቀብራለች፡፡

ይኹንና ሐዋርያት ቢቀብሯትም ትንሣኤዋንና ዕርገቷን አላዩም ነበር፡፡ ትንሣኤዋንና ዕርገቷን ያየው ሲቀብሯት ያላየው ሐዋርያው ቶማስ ነው፡፡ ቶማስ እንዲያስተምር ሕንድ አገር ዕጣ ደርሶት አስተምሮ በደመና ሲመለስ ነሐሴ ፲፮ ቀን እመቤታችን ስታርግ ሕዋ ላይ ተገናኙ በማለት ሊቀ ማእምራን ደጉ ያስረዳሉ፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለጽ ምእመናን ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገቷ የሚዘከርበት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነ ጾም ነው፡፡ በየዓመቱ ሕፃን አዋቂው ሳይቀር የእመቤታችን ፍቅር አድሮባቸው ጾሙን ይጾማሉ፣ ያስቀድሳሉ፤ ይቈርባሉ፡፡

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው⁉️

የፍልሰታን ጾም ከሌሎቹ አጽዋማት ልዩ የሚያደርገው ምንድን ነው? ለሚለው ጥያቄ ሊቀ ማእምራን ደጉ ምላሽ ሲሰጡም. "ኢትዮጵያ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር በመሆኗ እና ሕዝበ ክርስትያኑ ለእመቤታችን ልዩ ፍቅር ስላላቸው መሬት ላይ እየተኙ፣ ጥሬ እየበሉ በሰላም በፍቅር ይጾሙታል፡፡ 

ምእመናን ፍልሰታን ከሌሎች አጽዋማት በተለየ መልኩ መሬት ላይ እየተኙ ይጾሙታል፡፡
ይህ ደግሞ የእመቤታችን ፍቅር ስለሳባቸው ነው ፍቅር›› በማለት ያብራራሉ

         🤗ወስብሐት ለእግዚአብሔር🤗
እመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን  መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን

ይህን ጽሑፍ ሼር በማድረግ ሁሉም ምእመናን ለምን
እንደሚጾም እናሳውቀው🙏🏾

አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

🤗 መልክአ ፍልሰታ በግዕዝ ዜማ ከነ ምልክቱ
                👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/A6zG7fbyqZ0
https://youtu.be/A6zG7fbyqZ0
https://youtu.be/A6zG7fbyqZ0

•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


🙏ይቅርታ ጠይቆም ተሳድቦም ይሆናል ?!

ትራንስፖርት ላይ ነበረኩ ከመገናኛ ወደ ሜክሲኮ የሚሄድ ባስ ላይ ወደ ፒያሳ የሚሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ በጣም የተሰላቸች አንዲት እህት

እዚህ ከምቆም ብላ ወደ ሜክሲኮ በሚሄደው ሄጄ ከዚያ ወደ ምፈልገው ቦታ ብሄድ ይሻላል ብላ ወደ ሜክሲኮ የሚሄደውን ባስ ተሳፈረች።

በዚህ ቅጽበት ባሱ ለመንቀሳቀስ በመዘጋጀት ላይ እያለ ወደ ፒያሳ የሚሄደው ባስ መጣ ይህቺው እዚህ ከመቆም ብላ አቆራርጣ የተሳፈረችው እህት ወደ ሰፈሯ የሚሄደውን ባስ እንደመጣ በመመልከቷ

አሽከርካሪ ሹፌሩን በስህተት ነው የገባሁት አቁምልኝ ብሉት ብላ ተማጸነች ተሳፋሪዎችም ተሳስታ ነው ብለው በማሰብ ከወጣት እስከ አዛውንቱ እባክህ አቁምላት ተሳስታ ነው እያሉ ይለምኑላት ጀመሩ ባሱም ተንቀሳቅሶ ስለነበረ መቆም ባለመቻሉ ትንሽ ወረድ ብሎ የትልልቅ ሰዎችን ልመና በመመልከት መቆም የሌለበት ቦታ ላይ ለማቆም እየተዘጋጀ እያለ በጣም ይቅርታ አቁምልኝ ተሳስቼ ነው ብላ ተማጽኖዋን አሰማች ሹፌሩም እሱን ሊያስቀጣ የሚችል ቦታ ላይ አቁሞ እንድትወርድ አደረገ ።

ልክ እንደ ወረደች ግን ምቀኛ ስትል ተናገረች ይህን ነገር የተመለከቱ ሹፌሩን ለምነው ያስወረዷት ትልቅ ሰው
ይቅርታ ጠይቀውም ተሳድበውም ይሆናል ?
ሲሉ ራሳቸውን ጠየቁ እውነታቸውን ነው።

እስቲ ይህን ወደ ራሳችን ህይወት እናምጣው እና በህይወታችን እግዚአብሔርን በህይወቴ ተሳስቼአለሁ ኃጢአት ሰርቼአለሁ በድዬአለሁ ብለን ለምነን የእግዚአብሔርን ጊዜ ባለመጠበቅ ምላሽ እስከ ሚሰጠን ህይወታችንን እስኪያቃናልን መጠበቅ ተስኖን አረኸ በቃኝ ማረኝ በማለት በመደጋገም ጠይቀን ጊዜው ደርሶ ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ ትክክለኛ ኑሮ ለመጀመር ስንል እኔ አሁን ነው እንዴ የጠየኩህ ምነው ዘገየህ ብለን ልመናችንን ሁሉ ከንቱ የምናደርገው ስንቶቻችን ነን??

እግዚአብሔር በህይወታችን የሚሰራበትን ሂደት የሚያውቀው እግዚአብሔር ራሱ ነው በትእግስት ጠብቀን ሥራውን ሲሰራ ደሞ የምናማርር ከሆነ ሁልጊዜም ቢሆን የምስጋናን ህይወት አንለምደውም ስለዚህ ከሰዎች ስህተት እንማር

ብልህ ከሰው ይማራል
ሞኝ ከራሱ ይማራል ይላሉና አባቶቻችን

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ጸሐፊ ፦ ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ
አቅራቢ ፦ ✞ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት📚

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_spiritual_question
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


ከማኅፀን እስከ ሽምግልና
ሚጠብቀኝ ምህረትህ ነውና
ለምስጋና ወደ ቤትህ ልግባ
ልሰዋልህ የከንፈሬን መባዕ

የሰጠኸኝን ዕድሜ አንተን ለማገልገል አድርግልኝ አሜን !!

ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ተደገፍሁ፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ሁልጊዜም ዝማሬዬ ለአንተ ነው።
 ለብዙዎች መደነቂያ ሆንሁ፤ አንተ ግን ብርቱ መጠጊያዬ ነህ።
 አፌን ምስጋና ምላ ሁልጊዜ ክብርህንና ግርማህን እዘምር ዘንድ።

መዝሙረ ዳዊት 71፥6-8

🙏🤗ተመስገን🤗🙏


🌨በዚህ ክረምት ሁለቱን ወር የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ‼️
|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን

የጀርመን ሀገራት ግእዝን PHD ድረስ አስተምረው በማስመረቅ ላይ ናቸው እኛ ግን በእጅ የያዙት ወርቅ ሆኖብናል ይህን በማሰብ ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ በቴሌግራም ONLINE ስልጠና ሰጪ ተጀምሯል ።

የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁ እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

💵#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከተማሩበት 🪪Certificate(የምስክር ወረቀት) ጋራ

ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251914946589 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓






🌨በዚህ ክረምት ሁለቱን ወር የግእዝ ቋንቋን ይሰልጥኑ‼️
|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን

የጀርመን ሀገራት ግእዝን PHD ድረስ አስተምረው በማስመረቅ ላይ ናቸው እኛ ግን በእጅ የያዙት ወርቅ ሆኖብናል ይህን በማሰብ ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ በቴሌግራም ONLINE ስልጠና ሰጪ ተጀምሯል ።

የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁ እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

💵#ለሁለት ወር የመማሪያ ሙሉ ክፍያ #250ብር ብቻ ከተማሩበት 🪪Certificate(የምስክር ወረቀት) ጋራ

ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251914946589 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓


👉🏽 ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?


 በወጣትነት ወራት ስለ አባል ዘር ሥራና ውጤት ለማወቅ ካለ ጉጉትና ለተቃራኒ ፆታ የሚኖር ዝንባሌ ከመጨመሩ የተነሣ ወንዶችም ይሁኑ ሴቶች የመራብያ አካላቸውን በመነካካት ጾታዊ ስሜት እንዲሰማቸውና የስሜት እርካታ እንዲያገኙ ሆን ተብሎ የሚፈጸም ተግባር ሴጋ ወይም ማስተርቤሽን በመባል ይታወቃል።
  የዚህ ጽሁፍ አላማ ስለ ግለ ወሲብ በዝርዝር ማብራራት ሳይሆን ማስተርቤሽን የተባለውን የዝሙት ኃጢአት የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው ተወዳጆች ሆይ እያወራን ያለነው ከወንድ ጋር በአካል ዝሙት ፈጽማ የማታውቅ ነገር ግን የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሷን በራሷ ለማርካት ማስተርቤሽን ስለፈጸመች ሴት ወይም የዝሙትን ጣዕም ለማጣጣም ራሱን በራሱ ለማርካት ማስተርቤሽን ስለፈጸመ ወንድ ነው።

እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ከተቃራኒ ጾታ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ሳያደርጉ ለእንደዚህ አይነት የዝሙት ተግባር በመጋለጣቸው ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ ከወንዱ ጋር በምንጣፍ አንድ አልሆንኩም ነገር ግን ማስተርቤሽን ፈጽሜለሁኝ ድንግል ልባል እችላለሁ?
እና ለድንግላን የሚፈጸመውን ሥርዓተ ተክሊልስ ለእኔ ሊፈጸምልኝ ይችላልን?
 የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ነው።


ማስተርቤሽን ሲፈጽም የኖረም ሰው ኃጢአቱን አምኖ ሲመለስ ድንግል ልባል የድንግልና ሥርዓትም ሊፈጸምልኝ አይገባም በሚል በተሰበረ መንፈስ ነው እንጂ በይገባኛል የሚል የትዕቢት ሐሳበ በልቡ የያዘ መንፈሳዊ ኪሳራ ውስጥ መሆኑ ግልጽ ጉዳይ ነው።
የሚል ጥያቄ በአእምሯቸው የሚፈጠረው ፍቅር እግዚአብሔር ሲጎድልብንና ራስ ወዳድ ስንሆን ነው።

ምክንያቱም ማስተርቤሽን ቪድዮ ሴክስ ፎን ሴክስ የመሰለ ብዙ ኅቡረ ዝሙት እየፈጸምን ያሳስበን በደልነቱ ሳይሆን ተክሊል መፈጸም አለመፈጸም መሆኑ ነው።
እንዲህ አይነት አስተሳሰብ "የቤተ ፈት" አስተሳሰብ ይባላል።
ቤተ ፈት የምትባለው ባል አግብታ እየኖረች ከጊዜ በኋላ ባሏን ፈታ የኮበለለች ሴት ናት።
ከሄደችም ችግር ሲያጋጥማት የሚታያት ባሏን መበደሏ ሳይሆን ከባሏ ጋር በምትኖርበት ጊዜ የነበራት ምቾት እና ክብር ነው።
አባታችን አዳምን ግን የቤተ ፈት ልማድ አላገኘውም ማለትም ኃጢአት ሰርቶ ከገነት በተባረሩ ጊዜ ፈጣሪዬን አስቀየምኩት ስለ በደሉ ያለቅስ ነበር።
እንደዚህ ሁሉ ሰው በልዩ ልዩ የዝሙት ኃጢአት በተሰነካከለ ጊዜ "ድንግል ነኝን?"
"ተክሊል ይገባኛል?" እያለ ያወጣውና ያገኘውን እያሰበ ከመተከዝ" አንተን ብቻ በድልሁ በፊትህም ክፋትን አደረኩ መዝ 51፥4

ተወዳጆች ሆይ ከድፍረት የሚገኝ ምንም አይነት መንፈሳዊ በረከት የለም። ድፍረት መንፈሳዊ ኪሳራን ለዚህ ነው ቅዱስ ዳዊት እንደዚህ ያለው "የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባርያህን ጠብቀኝ ያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ" መዝሙር 19፥13
 ምን አልባት አንዳንድ ካህናት ስለዚህ አይነት ኃጢአት ግንዛቤ ሳይኖራቸው ቀርቶ ተክሊል ፈጽሚ ተክሊል ፈጽም ቢሉን እንኳን ራሳችንን ዝቅ አድርገን አይገባኝም😔 ልንል ያስፈልጋል።

•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ ትችላለች⁉️

 ➦በወር አበባ ጊዜ የሚከለከልስ ጸሎት አለ?

➦ተወዳጆች ሆይ ሴት ልጅ በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታያት ከሱባኤ የመውጣትና የመቆየቷ ነገር እንደ ገዳሙ ሥርዓት ይወሰናል፡፡ ከሱባኤ ትወጣለች ማለት ሱባኤን (አርምሞን) ትፈታለች፣ተአቅቦዋን ትተዋለች ማለት ሳይሆን እስከምትነፃ ድረስ ገዳሙ ባዘጋጀው ቦታ ቆይታ መጨረስ ትችላለች፡፡ በሱባኤው ላይ ወይንም መውጫው ሲቃረብ የወር አበባ ቢታያት ሱባኤውን ማቋረጥ ሳይሆን በጊዜያዊ ቦታ መጨረስ ይገባታል፡፡
ብዙዎች እህቶቻችን ሱባኤ የምንይዙት በድንገት ነው፡፡
➦ይህ ችግር እንዳይገጥማችሁ ሱባኤ ከመግባታችሁ በፊት ቀናችሁን ቆጥራችሁ አስተካክላችሁ ብትይዙ የበለጠ ትጠቀማላችሁ፡፡ ሰይጣን ያለጊዜው በወር አበባ ሊፈትናችሁ ስለሚችል ቀናችሁን እንደጨረሳችሁ ሱባኤ ብትይዙ ይመረጣል፡፡ በተለይ ዓይነ ጥላ ከዓይነ ጥላም ገርግር ዓይነ ጥላ ያለባቸውና መተት እና ድግምት የተደገመባቸው እህቶቻችን ያለ ጊዜና ያለ ቀኑ በሚመጣ የወር አበባ በሱባኤ ወቅት ይፈተናሉ፡፡ ምስጋና ለእመቤታችን ይሁንና እመቤታችን ንፁህ አይደላችሁም በማለት ጸሎታችሁን ቸል ስለመትል የያዛችሁትን ሱባኤ ቀጥሉ፡፡ ምክንያቱም የእኛ ርኩሰት የእመቤታችንን ንፅህና ስለማያሳድፍ ጸሎታችንን ትሰማናለች፡፡

➦ጸሎት ከፈጣሪ የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ እግዚአብሔር ጊዜን እየጠበቀ በዚህ ጊዜ እሰማችኋለሁ በዚህን ጊዜ አልሰማችሁም አይልም፡፡ በወር አበባ ጊዜ አይጸልይም ማለት የቤተ-ክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን የሰነፉ ሰይጣን የተንኮል እና የእንቅፋት ስብከት ነው፡፡ የሰይጣንን እንኳን ጸሎት ትተን ቀርቶ እየጸለይን ፈተናችንን እኛና እግዚአብሔር ነው የምናውቀው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ እንደ እኛ ግራ ለተጋቡት የተሰሎንቄ ምእመናን "ሳታቋርጡ ፀልዩ" በማለት ፀሎት በየትኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ፅፎላቸዋል።

➦ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እስከ መንጻቷ ቤተ-ክርስትያን ነው መግባት የማትችለው እንጂ፣ ጸሎት ማቋረጥ የለባትም፡፡ ጊዜን ተብቆ አለመጸለይ ለሰይጣን በር መክፈት ነውና ትንሿን ጸሎታችንን ማቋረጥ የለብንም፡፡
ተወዳጆች ሆይ ጌታችን ደመኛን እንጂ ደምን አይጠየፍም አይጠላም፡፡ ቢጠየፍማ ለአሥራ ሁለት ዓመት ሰውነቷ በደም ሲጨቀይባት የነበረችውን ምስኪን ሴት መለኮት ጋ ጠጋ ብላ ልብሱን ነክታ ልትድን ቀርቶ መርገምንና ሌላ በሽታን ሸምታ በተቀሰፈች ነበር፡፡ ጌታችን ግን መልካም አመጣጧን ፣ የዓመታት ጭንቀቷን ተመልክቶ ከነደሟ ተቀብሎ በልቧ የነበረውን አውቆ ፣ የደሟን ምንጭ አድርቆ፣ እምነቷን አድንቆ፣ ከጤናዋ ጋር በሰላም ወደ ቤቷ መልሷታል፡፡ /ማቴ. 9፣18-26, ማር. 5፣21-43, ሉቃ. 8፤41 ይመልከቱ/
ወለላይቱ የእመብርሃን ልጆች የእመቤታችንን ባህርይ አላወቅንም እንጂ፤ እርሷ ጥዩፍነት ከቶ በባህሪዋ የለም፡፡

➦የዛሬውን አያድርገውና ሁላችንም ስንወለድ እናቶቻችን በምጥ ሰዓት ከነደማቸው በጸሎትና በጭንቀት ጠርተዋት አወዋልዳቸዋለች፤ አሁንም ታዋልዳቸዋለች፡፡ በአራስራቸው ጊዜ ከእነሱ አትለይም፣ እስከ ስሙም ‹የማርያም አራስ› ተብለው በስም ይጠራሉ፡፡

ሌሎች በወር አበባ ጊዜ አይጾምም ይላሉ፣ ከየት እንዳገኙት ባይገባኝም ይህች በወር አበባ አመካኝቶ፣ለመብላት አንኩቶ ይመስለኛል፡፡ በወር አበባ ጊዜ አንዳንድ እህቶቻችን ከፍተኛ የሕመምና የስቃይ ስሜት የሚሰማቸው ብሎም እስከ ሕክምና የሚያደርሳቸው ከሆነ ምናልባት መድሃኒት ሊወስዱ ስለሚችሉ እነርሱን አይመለከትም፡፡
➦ስለዚህ ያስለመድናቸውን ጸሎቶች ሁሉ መጸለይ እንችላለን፡፡ እራሳችሁን ከኃጢአት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ አንደበታችሁን ከሐሜት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ ሥራችሁን ከወር አበባ አንጽታችሁ፣በልባችሁ ማህደር ቂም እና ክፋት ቋጥራችሁ ብትጸልዩ ምን ዋጋ አለው? ከአንድ ሳምንት ከመርገም ጨርቅ ይልቅ በኃጢአት፣በክፋት ከሚጨማለቅ ሰውነት የሚቀርብ ጸሎት ከደመና በታች ነው፡፡ የወር አበባ በአንድ ሳምንት ይነጻል፡፡
ግን ከሰውነታችን አልነጻ ያሉን ስንት ኃጢአቶች አሉ፡፡
ስለዚህ ንጹህም ሆንን አልሆንን በርትተን ተግተን
ልንጸልይ ይገባል፡፡

👉🏽 ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን⁉️

 የሚለውን እንመለከታለን። 

🙏እስከዛው ይሄንን ለወዳጅዎ ለጓደኞችዎ ለሴት እኅቶች ያጋሩት🙏

ይቀጥላል...

•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺






☦👉🏾 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች⁉️
👉🏾 ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን❔
👉🏾 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን❓
ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን‼️
👉🏾 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል❕
👉🏾 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው❓
👉🏾 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው⁉️



የፍልሰታ ፆም ገብቶ ሱባኤ ከመያዛችን በፊት ማወቅ ያሉብን ነጥቦች ስለሆኑ ነው። ከላይ ላሉት ጥያቄ መልስ ማግኘት ትፈልጋላችሁ⁉️

            ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያሳውቁ‼️


       በ ⛪️ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ📚 ቻናል ብቻ

ዛሬ ማታ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ይለቀቃል
                @Eotc_Books_By_Pdf
                @Eotc_Books_By_Pdf
                @Eotc_Books_By_Pdf

•➢ ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄

🔔አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ሚድያ💒
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg
    👆🏾𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒👆🏾

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔻 
@Orthodox_Addis_mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
@Lesangeez128
   🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 🔺


"ወሏሂ ዑራኤል ደግ ነው"

ተፃፈ @BiniGirmachew

ልክ ታቦታቱ ሲወጡ ነበር ዑራኤል የደረስኩት። ደመና ቢሆንም ምእመናን ከግቢው ተርፈው መንገዱን ዘግተውታል። በጭንቅንቁ መሀል ማለፍ እንደማልችል ሲገባኝ ካለሁበት ሆኜ ፀሎቴን አድርሼ ልመለስ ስል ግን ከኋላዬ ቆመው የሚለምኑት ሽማግሌ ቀልቤን ሰረቁት።

አይነ ስውር ናቸው፤ በዛላይ የሙስሊም ቆባቸውን ደፍተዋል፤ አንገታቸው ላይ ደሞ "ለአሏህ ብላችሁ ስለአይነብርሀን"የሚል ወረቀት አንጠልጥለው ከዘራቸውን እንደያዙ ቆመው ሳይ ባለማመን ለትንሽ ደቂቃ አስተዋልኳቸው የሚያልፈው ሁሉ ከቦርሳው እየፈተሸ ከኪሱ እየመዘዘ በሀዘኔታ የሽማግሌው ኪስ ውስጥ ብር እየጨመረ ሲያልፍ እሳቸውም ያለእረፍት እየመረቁ ስመለከት ደሞ ከምርቃታቸው ለመቀበል እኔም ተጠግቼ ያለቺኝን ኪሳቸው ጠብ አድርጌ ላልፈሰ ስል እጄን ይዘውኝ
አሏህ ይስጥልኝ...አሏህ ይጠብቅልኝ....ልጄ እባክህ መውጫው ጠፍቶኝ ይኸው ቆሜያለሁ ከዚህ ግርግር ውስጥ አስወጣኝ ልጄ..
እሺ አባባ ችግር የለውም... ግን እንዴት እዚህ ግርግር ውስጥ(የምለው ጠፍቶኝ ዝም አልኩ አይ የዛሬውስ ተአምር ነው።እኔ እዚህ እመጣለሁ ብዬ መች አሰብኩና።

ባለቤቴ ታማብኝ አልጋ ከያዘች ቆየች የሚረዳን የለም። እሷን ማሳከም አደለም ማጉረስ አቅቶኝ ጠዋት ዱአ አድርጌ ለልመና ስወጣ ከአንድ እንደኔው ካረጁ ሽማግሌ ጋ ተገናኘን።መንገድ ሊያሻግሩኝ ሲሉ ብቻ ችግሬን ነገርኳቸው። እሳቸውም ከኔጋ ብትመጣ ብዙ ብር ታገኛለክ አሉኝ።እኔም አምኜ ተከትያቸው እዚህ መጥተን ግርግሩ መሀል ስንደርስ ግን መጣሁ ብለውኝ ተሰወሩ።
ስማቸውን አላቅም።

ነጠላ መልበሳቸውን ብቻ አስታውሳለሁ በመሀል በመሀል ደሞ አይዞህ ኡራኤል ደግ ነው ይሉኝ ነበር።ታድያ እኔ እስኪመጡ ብዬ በቆምኩባት ቅፅበት ሰወች እየመጡ ብር በኪሴ ይከቱልኝ ጀመር።ይሄኔ ደነገጥኩኝ ሰውየው ለምን እዚህ እንዳመጡኝም ገባኝ።

አፌን አውጥቼ አለመንኩም፤ ቤተክርስትያን ጋ መሆኑን አውቄም ስለ አሏህ አላልኩም፤እጄንም አልዘረጋሁም!!የሚሆነው ነገር ቢደንቀኝ ግን የሚሰጡኝን ተቀብዬ በማውቀው አሏህ ይስጥልኝ እያልኩ እየመረቅኩ ኪሴ ሲሞላ አንተ ደረስክ።

ይኸው ብር በብር ሆንኩኝ የለመንኩት አላሳፈረኝም ሰውየውም ደግ ብለው የጠሩት ኡራኤል ቸል አላላቸውም።የኔ ልጅ ምንም ችግር ቢገጥምህ ፈጣሪህ ጥሎ አይጥልህምና እምነትህ በሱ ይሁን። አንተም ደሞ ሁሌ ለሰወች ደግ ሁን "በሚታየው እጅህ ስትሰጥ የማይታየው የአምላክ እጅ ይከተልካል' እኔ ቤተክርስትያን
ደጅ ደርሼ አላቅም።

ዛሬ ግን ብመጣ ከምግብ አልፎ ሚስቴን የማሳክምበት ብዙ ብር ኪሴን ሞላው።አየህ ክርስትያኑ ሙስሊም ነው ብሎ በንፍገት አላለፈኝም ደግነት ዘር የለውም፤ሀይማኖት የለውም ፤ቋንቋ የለውም ፤ማንም ማንንም ቢረዳ አምላክ ለሱ ጨምሮ ይሰጠዋል እንጂ የዋጋውን አያጣም።

አሁን ደስ ብሎኛል ሚስቴም ትታከማለች ጭንቄ ቀሏል የሠጠኝ አይጉደልበት አሏህ ይጨምርላችሁ ደሞ ሚስጥር ልንገርህ??(እጄን ጠበቅ አድርገው ጆሮዬ ስር እየተጠጉ እሺ አባባ ይንገሩኝ ምንድነው? ) አልኳቸው የሚሉኝን ለመስማት እየጓጓሁ
"ወሏሂ ኡራኤል ደግ ነው"ብለውኝ የእውነት ሳቁ እኔም የእውነት ደስ ብሎኝ እየሳቅኩ ታክሲ አስይዣቸው መርቀውኝ ተለያየን።

"ወሏሂ ኡራኤል ደግ ነው"

@Eotc_Books_By_Pdf
@Eotc_Books_By_Pdf
@Eotc_Books_By_Pdf


በጎፋ ዞን የተጎዱ ወገኖቻችን እናግዝ


8091 የፈለጋችሁትን የብር መጠን በመጻፍ sms ይላኩ
የጎፋ ዞን የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ ፈንድ። 1000511561276

እግዚአብሔር አምላክ በምህረቱ ይጎብኘን ። 🙏🙏

ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን 😭

ሼር እናድርግ ሼር የወንድማዊነት ። 🙏

ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ


Greetings! I'm honored to share the compelling history of our campaign to build the first ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH Referral hospital for the Mekane Hiwot Chobi Beata Lemariam Monastery community.

Introduction:
Welcome to our mission to create lasting change! At the heart of our endeavor is the Mekane Hiwot Chobi Beata Lemariam Monastery, dedicated to serving our community with compassion and resilience.

Current Situation:
In the heart of our community, healthcare remains a challenge. Limited access to medical facilities has left many vulnerable, facing health crises without proper support.

Monastery's Mission:
Driven by our monastery's commitment to compassion and service, we envision a hospital that will stand as a beacon of hope, delivering quality healthcare to those in need.

Impact:
By supporting this project, you're contributing to a profound impact—improved healthcare accessibility, saved lives, and an enriched quality of life for countless community members.

Project Details:
Your donations will directly fund the construction, equipping, and operation of this hospital. We're transparent about our goals, with detailed plans for every stage of the project.

Timeline:
We're eager to initiate this transformative project swiftly. With your support, construction will commence soon, and we anticipate the hospital to begin serving the community within a realistic timeframe.

Supporting Media:
Explore the visual narrative of our cause through images and videos showcasing the current healthcare challenges and the future we're striving to create.

Testimonials:
Listen to the voices of our community, sharing heartfelt testimonials about the pressing need for a hospital and the positive impact it will have on their lives.

Call to Action:
Your support matters! Join us in making this vision a reality by contributing financially, spreading awareness, and becoming a crucial part of this uplifting journey.

Together, let's build a legacy of healing and hope. Thank you for being a driving force in creating a healthier, happier community.
Aba Tekle Silassie G/Hiwot
ለመካነ ሕይወት ጮቢ በአታ ለማርያም ገዳም ማህበረሰብ ሆስፒታል ለመገንባት ያደረግነውን አሳማኝ ታሪክ ሳካፍል ክብር ይሰማኛል።

መግቢያ: *
ወደ ተልእኮአችን እንኳን በደህና መጡ ዘላቂ ለውጥ ለመፍጠር! የጥረታችን አስኳል መካነ ሕይወት ጮቢ ለማርያም ገዳም ወገኖቻችንን በርኅራኄ እና በጽናት ለማገልገል የተዘጋጀ ነው።

አሁን ያለው ሁኔታ:
በማህበረሰባችን ውስጥ፣ የጤና አጠባበቅ ፈታኝ ነው። የሕክምና ተቋማት ያለው ውስንነት ብዙዎችን ለአደጋ እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል፣ ተገቢውን ድጋፍ ሳያገኙ የጤና ቀውሶች ይጋፈጣሉ።

የገዳሙ ተልእኮ:
ገዳማችን ባለው ርህራሄ እና አገልግሎት ቁርጠኝነት በመነሳት የተስፋ ብርሃን ሆኖ የሚቆምና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለተቸገሩት የሚያደርስ ሆስፒታል እናስባለን።

ተጽእኖ:
ይህንን ፕሮጀክት በመደገፍ በጥልቅ ተፅእኖ ላይ እያበረከቱ ነው—የተሻሻለ የጤና እንክብካቤ ተደራሽነት፣ የዳኑ ህይወት እና የበለጸገ የህይወት ጥራት ስፍር ቁጥር ለሌላቸው የማህበረሰብ አባላት።

የፕሮጀክት ዝርዝሮች: *
የእርስዎ ልገሳ በቀጥታ የዚህን ሆስፒታል ግንባታ፣ መሳሪያ እና ስራ ይሸፍናል። ለእያንዳንዱ የፕሮጀክቱ ደረጃ ዝርዝር እቅዶች ይዘን ስለ ግቦቻችን ግልጽ ነን።

የጊዜ መስመር:
ይህንን የለውጥ ፕሮጀክት በፍጥነት ለመጀመር ጓጉተናል። በእርስዎ ድጋፍ፣ በቅርቡ ግንባታው ይጀመራል፣ እናም ሆስፒታሉ በተጨባጭ የጊዜ ገደብ ውስጥ ማህበረሰቡን ማገልገል ይጀምራል ብለን እንጠብቃለን።

ደጋፊ ሚዲያ: *
ወቅታዊ የጤና አጠባበቅ ፈተናዎችን እና ለመፍጠር የምንጥርበትን የወደፊትን በሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች የምክንያታችንን ምስላዊ ትረካ ያስሱ።

ምስክርነት:
ስለ ሆስፒታል አስቸኳይ ፍላጎት እና በህይወታቸው ላይ ስለሚያመጣው አዎንታዊ ተጽእኖ ከልብ የመነጨ ምስክርነቶችን በማካፈል የማህበረሰባችንን ድምጽ ያዳምጡ።

ወደ ተግባራዊነት:
የእርስዎ ድጋፍ አስፈላጊ ነው! በገንዘብ በማበርከት፣ ግንዛቤን በማስፋት እና የዚህ አነቃቂ ጉዞ ወሳኝ አካል በመሆን ይህንን ራዕይ እውን ለማድረግ ይቀላቀሉን።

ተባብረን የፈውስና የተስፋ ትሩፋት እንገንባ። ጤናማ እና ደስተኛ ማህበረሰብ ለመፍጠር አንቀሳቃሽ ኃይል ስለሆናችሁ እናመሰግናለን።

አባ ተክለ ሥላሴ ገ/ሕይወት


ንግድ ባንክ 1000571767434
አሀዱ ባንክ 0000020010901
አቢሲኒያ ባንክ 19 55 66 88 7

ከውጭ ለሀገር በመሆን መረዳት እፈልጋለሁ ከአሉ እየው


https://gofund.me/c65fdd44

በወር ያቅሜን አስገባለሁ ካሉም  የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ

https://t.me/+wOLDz0XabUgxNGY0

https://www.facebook.com/share/p/aaEVmRHbQhTa77Ev/?mibextid=oFDknk

https://vm.tiktok.com/ZMMuAeB8P/


YouTube ላይ ማየት እፈልጋለሁ እስካሁን የተሰራሁን  ከአሉ  ደሞ


https://youtu.be/eldcORxKz4M?si=Y3-QfA0fzF_dns5-

chobibata@gmail.com

+251903280707 ቢሮ
+251931302636ሥራ አስኪያጅ ሮዳስ ጥግነህ
+251913569435 ዋና ሰብሳቢ ዳንኤል አስራት
አድራሻ ቢሮ ቦሌ ደንበል ፊትለፊት አበሩስ አጠገብ


ለእናንተ ልዩ ዜና

BGN የእናቶች እና የህፃናት ልዩ ህክምና ማዕከል የ24 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል


⚡ ሁሉም ህክምናዎች በእስፔሻሊስት እና ልዩ እስፔሻሊስት ይሰጣል

📍 አድራሻ-አ.አ ፣ ሀያ ሁለት: ጎላጎል አካባቢ ከመክሊት ህንፃ ጀርባ 300ሜትር ገባ ብሎ

ለህክምና ቀጠሮ ለመያዝ 

+251927707000/ 

+251941282829

20 last posts shown.