የሞሪንጋ (ሽፈራው) ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር እንደሚከላከል በጥናት መረጋገጡ ተገለጸ‼️
በኢትዮጵያ 'ሽፈራው' እየተባለ የሚጠራው የሞሪንጋ ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር እንደሚከላከል በጥናት መረጋገጡ ተገልጿል፡፡ጥናት እና ምርምሩ ተግባራዊ እንዲሆን የጣሊያን መንግሥት፣ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዲስትሪ ልማት ድርጅት እንዲሁም የአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በጋራ የሰሩትን ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል፡፡
በአርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ በምግብ ቴክኖሎጂና ባዮቴክኖሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር አዲሱ ፍቃዱ፤ የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ተክል በሕጻነት ላይ የሚከሰተውን የመቀንጨር ችግር ጨምሮ ብዙ የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በጥናት እና ምርምር መረጋገጡን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በተክሉ ውስጥ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች የሚገኝበት በመሆኑ ከሌሎች ምግቦች ጋር በመቀላቀል በመጠቀም እንደሚቻል አንስተው፤ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፍ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችንም ማስቀረት እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በዋናነት ተግባራዊ የተደረገው ተክሉ በስፋት የሚበቅልበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ ዘይሴ ቀበሌ ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከተክሉ የተለያዩ ምርቶች እንደሚገኝበት እና ዘርፍ ብዙ ጠቀሜዎች እንዳሉት ተናግረዋል፡፡
በተገኘው ጥናት እና ምርምር መሰረት፤ ተክሉ በብዙ መልኩ የሚቀነባበርበት የፋብሪካ ግንባታ ተጠቀናቆ የተለያዩ ማሽኖችም መግባታቻውን አሐዱ ማረጋገጥ ችሏል፡፡የተጀመረው ፕሮጀክት ተግባራዊ እንዲሆን ያሉትን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሰራ ነው? ሲል አሐዱ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ላነሳው ጥያቄም፤ የመንገድ እና የኤሌትሪክ አገልግሎት ችግሮች እንደሚፈቱም ተናግረዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የኢንደስትሪ ልማት ድርጅት ተወካይ እና የፕሮጀክቱ ቴክኒካል አማካሪ ዶክተር ለምለም ሲሳይ በበኩላቸው፤ በገጠር ላሉ ሴቶች የኑሮ ማሻሻያ ያስፈልጋል በሚል ከመንግሥት በቀረበው ጥያቄ መሰረት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ መደረጉን አንስተው ከክልሉ መንግሥት ጋር በጋራ እንደተሰራም አስረድተዋል፡፡የሞሪንጋ ወይም የሽፈራው ተክልን አብዛኛው የኢትዮጵያ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የካንሰር አይነቶችን እና ደምግፊትን ጨምሮ ሌሎች በሽታዎችን ለመከላከል እንደሚጠቀሙበት የሚታወቅ ነው፡፡
@Esat_tv1@Esat_tv1