የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች በGoogle Translate ሥርዓት ውስጥ ተካተቱ‼️
የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚተረጉመው Google Translate ተጨማሪ 24 ቋንቋዎችን ወደ ሥርዓቱ ማስገባቱን አስታውቋል። ከዚህ ውስጥም የአፋን ኦሮሞ እና የትግረኛ ቋንቋዎች መካተታቸው ተገልጿል።
አዲስ ከተካተቱት ቋንቋዎች ጋር ተደምሮ አገልግሎቱ 133 የዓለም ቋንቋዎችን መተርጎም ያስችለዋል ተብሏል። ከዚህ ቀደም የአማርኛ ቋንቋ በስርዓቱ ውስጥ ተካቶ አገልግሎት ላይ መዋሉ ይታወሳል።
ድርጅቱ ይህንን አገልግሎት ይፋ ያደረገው በትላንትናው ዕለት ሲሆን እስከ ሳምንቱ መጨረሻ ድረስ ለሁሉም ተጠቃሚዎች ተደራሽ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
@Esat_tv1