መንግስት ለቀጣዩ ዓመት 780 ቢሊየን ብር በጀት ማዘጋጀቱ ተሰማ‼️
የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በብርቱ የኢኮኖሚና የፀጥታ ፈተና ውስጥ ሆኖ ከሁለት ወር በኋላ ለሚጀምረው አዲሱ የበጀት ዓመት 780 ቢሊየን ብር በጀት ማዘጋጀቱን ዋዜማ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ስምታለች።
አዲሱ በጀት ካለፈው ዓመት በጀት ጋር ሲነፃፀር የአንድ መቶ ቢሊያን ብር ያህል ብልጫ አለው። የ 2014 ዓ.ም በጀት የአጋማሽ አመቱ ጭማሬ ተዳምሮ 680 ቢሊየን ብር ነበር።
ዘንድሮን በበርካታ መሰናክሎች ያሳለፈው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በቀጣዩ ዓመት የበለጠ ፈተና የሚጠብቀው ሲሆን መንግስት አሁን ያሰናዳው 780 ቢሊየን ብር በጀት ከፍ ያለ ጉድለት ሊገጥመው እንደሚችል በበጀት ዝግጅቱ ወቅት በተደረጉ ምክክሮች ላይ መነሳቱን ስምተናል።
ለ2015 ዓ.ም የተያዘው በጀት ከ 2014 ዓ.ም የ100 ቢሊየን ብር ጭማሬ ይኑረው እንጂ በብር የውጭ ምንዛሬ ተመን ሲሰላ ብዙም ለውጥ የሚታይበት አይሆንም።
©wazema radio
@Esat_tv1