የመገናኛ ብዙኃን ፈቃድ መስጫ መስፈርቶች
በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/13 አንቀፅ 37 ንዑስ አንቀፅ 2 መሰረት ባለሥልጣኑ ፈቃድ ከመስጠቱ በፊት የአመልካቾችን ብቃት ለመመዘን የሚያስችል ዝርዝር መስፈርት የሚያወጣ ሲሆን፣ መስፈርቱ የሚከተለትን ነጥቦች ያካተተ መሆን አለበት፡-
ከብሮድካስት አገልግሎት ቴክኖሎጂ እድገቶች ጋር በተያያዘ ሊሰጥ ከታሰበው አገልግሎት የሚጠበቅ የቴክኒክ ጥራትና አመልካቹ በኘሮጀክት ሀሳበ-ሥራው የዘረዘራቸው መሣሪያዎችና ቴክኖሎጂዎች አገልግሎቱን ለመስጠት ያላቸው ብቃት፤
አመልካቹ አገልግሎቱን ለመስጠት ያለው ተስማሚነት፣ ድርጅታዊ ብቃት፣ የሥራ ልምድና ሙያዊ እውቀት፤
የአመልካቹ የፋይናንስ አቅምና ምንጭ፣ አስተማማኝነትና ሥራውን ለማስኬድ ያለው ዝግጁነት፤
በአመልካቹ ኘሮጀክት ሀሳበ-ሥራ የተዘረዘሩ የፕሮግራሞች መርሐ ግብርና በፕሮግራሞቹ የተካተቱ ማኅበራዊ ፍሊጎቶች፤ እና፣
አመልካቹ ለአገልግሎቱ የመደበው የሥርጭት ጊዜ፡፡
በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይጎብኙ፦
ድረ ገጽ
www.ema.gov.etፌስቡክ
https://www.facebook.com/ethiopian.media.authority/ኤክስ (X)
https://twitter.com/ethmediaauth?lang=en