ብስራት Sport™️ (101.1)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Bookmaking



Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Bookmaking
Statistics
Posts filter








Forward from: ኢትዮ ቀመር
በእውነት ይሄን አይተህ ካልተገረምክ አንተን ምንም አያዝናናህም ማለት ነው 😳😳😳‼️




ኢትዮ ቀመር:
ሊንኩን በመጫን አይታችሁ ከወደዳችሁት Like አርጉና ደገፍ አርጉኝ ቤተሰብ 🙏👇👇👇

https://youtu.be/5NjpK8DHH54?si=yioclUzAI5hDO6kO

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️እስኪ እሁድን ከሰአት ይሄን አስገራሚ እውነተኛ ታሪክ ልጋብዛችሁ 🥰


Forward from: ኢትዮ ቀመር
10 አስገራሚ እና አስደንጋጭ Video በቀጥታ ስርጭት ላይ የታዩ




አርጀንቲና 🅰

ፈረንሳይ 🔵


🏛️ እለቱን በትውስታ Part 3

☑️64' ላይ ካዛ ብላንካ በጩኸት ተናወጠ።🔊 ተደጋጋሚ ጥፋት ሲሰራበት የነበረው ያ ትንሹ ምባፔ 👦 ነው። በሰአቱ 20 አመቱ ላይ የሚገኝ የነበረው #ምባፔ በግል ብቃቱ የግብ ክልሉ ውስጥ ገብቶ በግራ እግሩ በግራ በኩል አክርሮ የመታው ኳስ የአርጀንቲናውን ግብ ጠባቂ🧤 #አርማኒን ጥሳ ገባች። ኮሜንታተሩ ጎልልልልል ሲል አበደ። በቴሌቭዥን 📺 መስኮት፣ ስታዲየም 🏟️ እና በራዲዮ 📻 ጨዋታውን የሚከታተሉት የፈረንሳይ ደጋፊዎች አበዱ። ይህ ግብ 🥅 የአርጀንቲናውያንን ህልም 😣 አጨለመ። የጨዋታው ውጤት ተቀየረ ፈረንሳይ 3 አርጀንቲና 2 ሆኑ፤ ጨዋታው ግን በዚህ ውጤት የቀጠለው 4 ደቂቃ ብቻ ነበር።⏳ በ68' አሁንም የ20 አመቱ ኪሊያን ምባፔ አስቆጠረ።ስታዲየሙን ለቀው ወጡ፤ ፈረንሳይ 4 አርጀንቲና 2፤ ግቡ አርጀንቲናውያንን ተስፋ ያስቆረጠ ነበር።😢 

☑️ግቡ ለደጋፊው ተስፋ ቢያስቆርጥም ቢሆንም አርጀንቲና ተጨዋቾች ተስፋ አልቆረጡም ነበረ። በተደጋጋሚ እየሞከሩ ነው። ፈረንሳዮች ጥፋት አብዝተዋል ማቱዊዲ እና ፓቫርድ ቢጫ🟨 ተመለከቱ።

☑️ ጨዋታው 4 ለ 2 በሆነ ውጤት መደበኛው ሰአት ተጠናቀቀ። አርጀንቲና ተስፋ ወደ መቁረጡ እየመጡ ነው። ነገር ግን በጭማሪው ቋሚ ሆኖ ያልጀመረው አጉዌሮ አስቆጠረ። ለአርጀንቲናም ተስፋን ሰጠ። የፈረንሳይ ተጨዋቾች ያላቸውን ሰጡ። አርጀንቲናዎችም ሞከሩ። ኦተመንዲ ፖግባ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ተሰጠው ጅሩድም ከኦተመንዲ ጋር ግብ ግብ በመፍጠሩ ቢጫ ተመለከተ።
☑️በመጨረሻም አርጀንቲናውያንን በእንባ ያራጨ ፈረንሳዮችን በደስታ ያስፈነደቀችው የመጨረሻዋ የፊሽካ ድምፅ🔊 ተሰማች። ተጠባቂ የነበረው ጨዋታ በፈረንሳይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። 🥳 አርጀንቲናዎች ምንም እንኳን በጨዋታ ቢበልጡም ለሽንፈት አልታደጋቸውም።
ℹ️ይህ ጨዋታ ለአጉዌሮ የመጨረሻው የአለም ዋንጫው ጨዋታ ነበረ( በልብ ህመም ከእግር ኳስ ስለተገለለ)።
ℹ️ፈረንሳይም በጥሎ ማለፉ አርጀንቲናናን በማሸነፍ የጀመረችው ጉዞ ሻምፒዮን ሆነው አጠናቀዋል።
ℹ️ዘንድሮም ሁለቱ ሀገራት በፍፃሜው ተገናኝተዋል። ምን አልባት አርጀንቲና ለመበቀል ይህ እድሏ ሊሆን ይችላል። ፈረንሳይም በተከታታይ ዋንጫውን በመሳም ታሪክ ለመስራት ይጫወታሉ። የፍፃሜ ጨዋታው እሁድ በኸሊፋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ምሽት 12:00 ሲል ይጀመራል።
ማን ያሸንፋል?


🏛️ እለቱን በትውስታ Part 2

⏩ ጨዋታው በካዛን አሬና ስታዲየም 10:00 ሲል በአርጀንቲናዊው ኔስተር ፒታና ዋና ዳኛ መሪነት ተጀመረ፤ስታዲየሙ ድባቡ ልዩ ነበረ። ጨዋታው ቀጥሏል ❿' ደቂቃ ላይ ደረሰ። ግን ➊➊' ደቂቃ ላይ የአርጀንቲናን ልብ የሰበረ ነገር ተከሰተ፤ማርከስ ሮጎ ምባፔ ላይ የግብ ክልል ውስጥ ጥፋት ሰራ። ዳኛው ፊሽካውን ነፉ ፍ/ቅ/ምት ለፈረንሳይ ተሰጠ፤ቢጫ ካርድ ለሮጎ። ፍ/ቅ/ምቱን #ግሬዝማን አስቆጠረ ፈረንሳይ 1️⃣ አርጀንቲና 0️⃣ ሆኑ የአርጀንቲና ደጋፊዎች ተጨነቁ።
➮ጨዋታው ቀጠለ! አሁንም ምባፔ ጥፋት ተሰራ ታግሊያፋኮ ቢጫ 🟨 ተሰጠው። 40' ደቂቃ ላይ ነን የውጤት ለውጥ የለም በጨዋታው አርጀንቲና በልጠዋል ተደጋጋሚ ሙከራ እያደረጉ ነው።
➮በመጨረሻም በ41' ደቂቃ ሙከራቸው ፍሬ አፈራ የቀድሞው የፒኤስጂ ተጨዋች #ዲማርያ ከ35 ያርድ ርቀት ላይ የመታት ኳስ ሎሪስን ጥሳው ገባች። ሜዳው በአርጀንቲና ደጋፊዎች ጩኸት ተሞላ🔊 ። ኮሜንታተሩም የሚገርም ምት እና ግብ ከፒኤስጂው አጥቂ፤ በሚል አሞገሰው። በዚሁ ውጤት ወደ መልበሻ ክፍል አመሩ።

➡️ 15 ደቂቃዎች ረፍት በኋላ ድራማዊው ክስተት ሊያስመለክተን የሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታ ተጀመረ። ነገር ግን ጨዋታው በተጀመረ በ3 ደቂቃ ውስጥ ፈረንሳይን ያስደነገጠ ክስተት ተፈጠረ፤ ሁለት ቁጥሩ የአርጀንቲና ተከላካይ የሆነው #ሜርካዶ በሜሲ የተመታው ኳስ ከፖል ጋር ተጋጭታ ስትመለስ አስቆጠራት። ካዛን አሬና ስሜቶች የተገላቢጦሽ ሆኑ፤አርጀንቲና 2️⃣ ፈረንሳይ 1️⃣።

⏩ጨዋታው ግሏል 🔥 ሁለቱም ግብ ለማስቆጠር እየጣሩ ነው። አሁንም ባኔጋ ምባፔ ላይ በሰራው ጥፋት ቢጫ ካርድ ተመለከተ።

➡️ፈረንሳይ በሀዘን 😔 ተውጣ ሳለ በ57' ደቂቃ ላይ ኮሜንታተሩ ጎል ብሎ ጮኸ🔊፤ፈረንሳይ አገባች፤አሁንም ተከላካዩ #ፓቫርድ ለፈረንሳይ አስቆጠረ። አሁን የሁለቱም ሀገራት ደጋፊዎች ስታዲየም 🏟️ ውስጥም ከቴሌቪዥን 📺 መስኮትም የሚመለከቱት ተጨንቀዋል።

ℹ️ ጨዋታው ቀጠለ 60' ፣61'፣62' ⏳ ደቂቃዎች ሄዱ አርጀንቲና ትደበድባለች ፈረንሳይም ካውንተር እየሞከሩ ነው። ድንገት ግን ካዛ ብላንካ በጩኸት ተናወጠ።🔊 ጎልልልል ኦኦኦኦኦ...


🏛️ እለቱን በትውስታ part 1

ℹ️እለቱ 2018 ነው፤የሩስያው አለም ዋንጫ ከ32 ሀገራት 16ቱን አለም ዋንጫው ቀንሷል። አለም ዋንጫው ሩስያን 🇷🇺 ፣ጃፓንን🇯🇵 ፣ስፔንን 🇪🇸 ፣ኡራጋይን 🇺🇾 ፣ፈረንሳይን 🇫🇷 ፣ሜክሲኮን 🇲🇽 ፣አርጀንቲናን 🇦🇷 ፣ቤልጅየምን 🇧🇪 ፣እንግሊዝን 🏴󐁧󐁢󐁥󐁮󐁧󐁿 ፣ኮሎምቢያ 🇨🇴 ፣ስዊዘርላንድ 🇨🇭 ፣ስዊድን 🇸🇪 ፣ዴንማርክ 🇩🇰 ፣ክሮሽያ 🇭🇷 ፣ብራዚል 🇧🇷 ፣ ፖርቹጋል 🇵🇹 16ቱ የቀሩት ሀገራት ናቸው።

ℹ️የ2018ቱ አለም ዋንጫ ጨዋታ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ አርጀንቲናን 🇦🇷 ከ ፈረንሳይ 🇫🇷 አገናኝቷል። ጨዋታው እንደ ፈረንጆቹ Jun 30, 2018 ላይ ቀጠሮ ተይዞለት በቀጠሮው ሊደረግ ነው። ስታዲየሙ በደጋፊዎች ተሞልቷል። አርጀንቲና ከ ፈረንሳይ።
ℹ️ሁለቱ ሀገራት ለ12ኛ ግዜ መገናኘታቸው ነበር፤ አርጀንቲና 🇦🇷 በሰአቱ በአለም ዋንጫው በተጋጣሚያቸው ላይ ቢያንስ 3 ግቦችን አስቆጥረው ነው የመጡት። ይህ ደግሞ ከ1986 በኋላ ሲሆን ለመጀመሪያ ግዜ ነበር።
ℹ️ፈረንሳይ 🇫🇷 በበኩሏ በ1978 በአርጀንቲና ከተሸነፈች በኋላ ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ጋር ያደረገቻቸው ያለፉትን ዘጠኝ ጨዋታዎች አልተሸነፈችም።

ማን ያሸንፋል ፈረንሳይ ወይስ አርጀንቲና?
❗️ጨዋታው ሊጀመር ነው❗️
☑️ በፈረንሳይ 🇫🇷 በኩል ሎሪስ በግብ ጠባቂ ፣ፓቫርድ፣ቫራን፣ኡምቲቲ፣ኸርናንዴዝን በተከላካይ ፖግባ እና ኮንቴ በተከላካይ አማካኝ ምባፔ፣ ግሬዝማን እና ማቱዊዲ በመሀል ከፊት ጅሩድን በማሰለፍ በ4-2-3-1 አሰላለፍ ወደ ሜዳ ገቡ ።

☑️አርጀንቲና 🇦🇷 በበኩሏ አርማኒን በግብ ጠባቂነት፤ታግሊፊኮ፣ሮጆ፣ኦታመንዲ እና ማሼራኖን በተከላካይ ቦታ፤ ባኔጋ፣ ማሼራኖ፣ፔሬዝ በመሀል፤ዲማሪያ ሜሲ እና ፓቮን በአጥቂ ቦታ በ4-3-3 አሰላለፍ ገቡ።

☑️ጨዋታው በካዛን አሬና ስታዲየም 🏟️ ልክ ⏳10:00 ሲል በአርጀንቲናዊው ዳኛ ኔስተር ፒታና አስጀመሩት። ስታዲየሙ በጩኸት ተናጋ ግማሹ አርጀንቲና ግማሹ ፈረንሳይ ይላል...




         🏆 ዱባይ ሱፐር ካፕ ጨዋታ

         ⏰  ተጠናቀቀ

ሊቨርፑል 4-1 ኤስ ሚላን
#ሳላህ 5'          #ሳሊማከርስ 29'
#ቲያጎ 41'
#ኑኔዝ 82' 88'
    
@Bisrat_Fm


ክርስቲያኖ ሮናልዶ ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ በስድስት አሰልጣኞች ስር ሰልጥኗል።👀

@Bisrat_Fm


" ሊዮኔል ሜሲ አያስፈራንም "

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ለፍፃሜው እንዲያልፍ የረዳች ግብ ያስቆጠረው ቲዮ ሀርናንዴዝ ለፍፃሜው ለመዘጋጀት አጭር ጊዜ እንዳላቸው ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።

እንደ ተጫዋቹ አስተያየት " ሊዮኔል ሜሲ አያስፈራንም ፣ አርጀንቲና ጠንካራ ስብስብ አላት እነሱን ለማሸነፍ ጠንክረን እንዘጋጃለን ያለን ጊዜ ግን ከእነሱ በአንድ ቀን ያነሰ ነው " ሲል ተደምጧል።

@Bisrat_Fm
@Bisrat_Fm


" ዋንጫውን ይዘን እንመለሳለን "

ወደ ኳታር በማቅናት በትላንት ምሽቱ ጨዋታ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ያበረታቱት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ዋንጫውን ይዘው እንደሚመለሱ ተናግሯል።

ፕሬዝዳንቱ ኢማኑኤል ማክሮን ሲናገሩም " አሰልጣኛችን ዴሻምፕ ፍፃሜዎችን አይሸነፍም ፣ በተጫዋችነት እና አሰልጣኝነት የዓለም ዋንጫውን አሸንፏል።

በአሁን ሰዓት ደግሞ ዳግም ለፍፃሜው ደርሷል ፣ ወደ ሀገራችን የምንመለሰው ዋንጫውን ይዘን ነው " ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።

@Bisrat_Fm
@Bisrat_Fm


ንግድ ባንክ የመጀመሪያዋን ሴት የውጪ ተጫዋች ሊያስፈርም ነው

ON: DECEMBER 15, 2022 
 
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያዋን የውጪ ዜጋ ተጫዋች ለማስፈረም የሙከራ ዕድል ሰጥቷል።

@Bisrat_Fm


የሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ንግድ ባንክ ወደ መሪነት ከፍ ሲል ኤሌክትሪክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስም አሸንፈዋል
 
ON: DECEMBER 14, 2022 
የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር ትላንትና በሦስት ጨዋታዎች ሲጀመር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ሦስት ነጥብ ሸምተዋል፡፡

@Bisrat_Fm


ከዓለም ዋንጫ መጠናቀቅ በኋላ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዲ ኤስ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ይቀጥላል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን የምስል መብት የገዛው ዲ ኤስ ቲቪ ወቅታዊው የብዙዎች ትኩረት የሆነውን የዓለም ዋንጫ ለተከታዮቹ ለማድረስ ከ8ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ሁለት ጨዋታዎች ጀምሮ ያለፉትን አራት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሳምንታትን እያስተላለፈ እንደማይገኝ ይታወቃል። አሁን ግን ለሊጉ ድምቀት የሰጠው ይህ ስርጭትም ከ13ኛ ሳምንት ጀምሮ እንደሚመለስ ድረ-ገፃችን አረጋግጣለች።
የዲ ኤስ ቲቪ የቀረፃ እና ፕሮዳክሽን ባለሙያዎች ነገ ዓርብ ድሬዳዋ እንደሚገቡ የሰማን ሲሆን የዓለም ዋንጫው እሁድ ከተጠናቀቀ በኋላ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ13ኛ ሳምንት ሰኞ ሲቀጥል የጨዋታ ሳምንቱን ሙሉ ለተመልካች እንደሚያደርሱ ተመላክቷል። በድሬዳዋ ስታዲየም ከሚደረገው የመጨረሻ ሳምንት ውጪ ግን ምናልባት በሜዳ አለመመቸት ምክንያት የተራዘሙት አራት ተስተካካይ ጨዋታዎች አዲስ ነገር እስካልተፈጠረ ድረስ ሽፋን ላያገኙ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

@Bisrat_Fm

20 last posts shown.