ስብዕናችን #Humanity


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Psychology


🔆እየጠየቁ መኖር መልስን፣
መልስን ፈልጎ ማግኘት ዕውቀትን፣
እውቀት ነፃነትን፣ ነፃነት ሙሉ ስብዕናን፣
ሙሉ ስብዕና ሠላምና እርካታን፣
እርካታ ደግሞ ደስተኛ ሆኖ መኖርን ያስገኛል፡፡
አብረን እንደግ !!
@EthioHumanity @Ethiohumanity
✍የተሰማቹን አጋሩን! ቤቱ ሁሌም ክፍት ነው፣ሃሳባቹን ፃፍፍ አርጉልን @EthioHumanitybot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Psychology
Statistics
Posts filter


🔔የሚሸጥ የልብስ ቤት ቁልፍ

✅ዋጋ 230ሺ ብር
✅የቤቱ ኪራይ 22000 ብር ነው

✅ቦታው ቤተል አደባባይ ታክሲ መውረጃው ጋር

☎️ 0911410771

👉 @Nagayta


🔴ትላንት ማታ የዓለምን ሚስጥር ይነግረኝ ዘንድ ጠቢቡን ለመንሁት
። ከብዙ እርጋታ በኋላም
“ፀጥ በል!... ምስጢሩ በዝምታ ተጠቅልሏልና ሊናገሩት አይቻልም!” ሲል አንሾካሾከልኝ
                                    -ሩሚ

📍ዝምታ ፈጣኑ እርጋታ ነው። ዝምታ ዝ...ግ ነው ፡ ካለትዕግስት የማይከፈት ምስጢር ፤ ዝምታ ዝቅ ነው ፡ አውቃለሁ የማይል ትሁት፡ ዝምታ ወርቅ ነው ፡ ከልብ ተቆፍሮ የሚገኝ ውድ ሐብት ነው።"

🔆ከውጫዊ ገፅታ የበለጠ ውስጣዊ ማንነት ይኑርህ፤ መልክህ፣አለባበስህ፣የምትነዳው መኪና አልያም የምትኖርበት ቤት ያንተን ዋጋ አይተምኑ። እንኳንስ ቁሳቁስህና ሀብት ንብረትህ ቀርቶ ሥራህ፣ ማእረግና ቤተሰብህ እንኳን ያንተ አይደሉም። የእኔ የሚባል ነገር የለም ፣ እሱ ነው ያጠፋን።

♦️አንተ ወደዚህ አለም ከመምጣትህ በፊት የነበረህ እውነተኛ ማንነት አለ ፣ እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡ የዚህ አለም ማንነትህ ሁሉም የውሸት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ይህ ሰውነትህ አፈር ነው፡፡ህይወት አይደለም፡፡ስምህም ሰዎች ተስማምተው የሰጡህ ጊዛዊ ታርጋ ነው፡፡ድግሪ ካለህም የሚናገረው ኮሌጅ ውስጥ ያሳለፍከውን ጊዜ ነው፡፡ ዝና፣ ትዳር፣ ስልጣንና እዚህ አለም ላይ እኔ ነኝ ብለህ የምታስባቸው ነገሮች ሁሉ አንተን አይደሉም፡፡

🔶እዚህ አለም ላይ አንተን የሆነ ነገር የለም፡፡ መከበርም፡ መዋረድም.... ድህነትም ፡  ሀብትም.... ዝናም ፡ መረሳትም..መማርም:አለመማር...መውለድም ፡ አለመውለድም ሆኑ ሁሉም የዚህ አለም ነገሮች ጊዛዊ ናቸው፡፡ይመጣሉ ይሄዳሉ፡፡ ጊዛዊ ያልሆነ ነገር አለ፡፡እሱን ያዘው፣ እሱም ህይወት ራሱ ነው፡፡ እውነተኛ ማንነትህ ይህ ነው፡፡

🔷"ያንን ማንንነት ለማግኘት ከጫጫታ መለየት አለብህ፡፡መጀመርያ አለም የጫነብህን ኮተት ከራስህ ላይ ልታራግፍ ያስፈልጋል፡፡ ትኩረትህን በውስጥህ ወዳለው ፈጣሪ ማይረግ አለብህ፡፡ህይወት አይታይም ፡ አይነካም፡ ቅርጽ የለውም፡ አይሞትም፡ አይገደብም አይገለጽም፡፡ህይወት ራሱ ፈጣሪ ነው፡፡ፈጣሪ አሁን ውስጥ ያለ የማይታይ ግንድ ነው፡፡አንተ ደግሞ የማይታይ ቅርንጫፍ ነህ፡፡ከዚህ ከማይታይ የፈጣሪ ግንድ ጋር ስትገናኝ ያንተ የማይታየው ቅርንጫፍ ያበራል፡፡ያለምንም ነገር መደሰት ትጀምራለህ

🌊በህብረተሰብ የጅምላ ጫጫታ ውስጥ የጠፋውን ግለሰባዊ የስብዕና ማንነትን ፈለገን እናግኝ። ጸጥታ፣ ዝምታ፣ እርጋታ ሀሴትን ፈጣሪ ልዩ ገፀ በረከቶቻችን ናቸው።የውስጥ ሰላሙን ያጣ ሰው፣ ውጫዊው ትርምስ ምኑ ነውን?ጠቢብ ግን ባንቀላፉት  መኃል መንቃትን ፥ ከብዙ ሰው ጫጫታ ዝምታን ይመርጣል ... በእርጋታና በጸጥታ የተሞላች ነፍስ የተመረጠች ነች

የሰከነ ልብ፣ አስተዋይ ልቦናን ፈጣሪ ያድለን!

        ውብ ቅዳሚት ለሁላችን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


🟡ሲያነቃቁን ለምን አንነቃም? ሙተን ይሆን እንዴ?

(አሌክስ አብርሃም)

💡ለመጀመሪያ ጊዜ self-help book የሚሏቸውን ሳነብ በጣም ነቅቸ ነበር!  አስታውሳለሁ የ Rhonda Byrne ን The secret  ሳነብ በጣም ከመንቃቴ የተነሳ ለስራ እጀን ከመጠቀም ይልቅ አዕምሮየን ለመጠቀም ወስኘ ነበር። ለምሳሌ መብራት አጥፍቸ ከመተኛት ተኝቸ መብራቱ ልክ እንቅልፍ ሲወስደኝ ይጠፋል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ፤ጧት ስነሳ እንደበራ ባገኘው አልደነቅም፣ ከእንቅልፌ ከመንቃቴ አንድ ደይቃ በፊት በራሱ ጊዜ እንደበራ አምናለሁ። የወሩ የመብራት ሂሳብ ግን የነገረኝ ሌላ ሆነ፤ ተው ወንድሜ በጣም አትንቃ አለኝ። እናም እያጠፋሁ መተኛት ጀመርኩ። ከ1890 ዓ/ም ጀምሮ መብራት ሀይል መብራት ያላጠፋበት ብቸኛ ወር ነበር። ስንነቃ አይወዱ😀

🕯ኦሾን ያነበቡ የኔ ዘመን ወጣቶች ደግሞ "ሐይማኖት ባህል ገለመሌ ከጫነብን ፍዘት ወጣን" አሉና በየመንገዱ ፀጉራቸውን በመፍተል መቆዘም ጀመሩ፤ ይህንንም "ውስጣዊ ንቃት" አሉት። ከአመታት በኋላ ሁሉም ጠበል ገብተው  እየጮሁ ከንቃታቸው በጣም ነቁ። በቀን አምስቴ ኡዱ የሚያደርጉ፣ ለጁመዓ የሽቷቸው  መዓዛ ከሞያሌ  የሚጣራ ፣ እንዴት ያሉ ንፁህ ሙስሊም ወዳጆቸ ሳይቀሩ ጀዝበው ገላቸውን መታጠብ አቁመው  ነበርኮ!  ስንት ተቀርቶባቸው ተመለሱ። የዛን ሰሞን ወጣቱ ሁሉ ውስጣችን በራልን እያለ ስንት ጨለማ ተከናነበ። ራሳቸውን ያጠፉም ነበሩ። ኦሾና አለቃ ገብርሃና ተረታቸው እንጅ ኑሯቸው አያምርም።

🔦ይሄው በዚህኛው ዘመን ደግሞ አነቃቂወች እንደአሸን ፈሉና "ያሰብከውን ትሆናለህ፣ ነኝ በል፣ አለኝ በል፣ ደርሻለሁ በል፣ እችላለሁ በል፣ በሀሳብህ መኪና አስነሳ፣ አሉ፤ ወጣቱ የሀሳብ መኪና አስነሳ፤ በሀሳብ ሲጋልብ ራሱ ጋር ተጋጨ፣ ቤተሰቡ ጋር ተጋጨ፣ አገሩ ጋር ተጋጨ፣ፈጣሪው ጋር ተጋጨ ።  ከሆነስ ሆነና  ለምንድነው  በዚህ ዘመን ይሄ ሀሁሉ አነቃቂ ንግግር ያላነቃን? የእውነት የሆነ ጊዜ ያነቃን ነበርኮ፣ እየቆየ ግን እንኳን ሊያነቃን ያስተኛን ጀመረ፤ እኮ ለምን?

📍የህክምና ባለሙያወች ከተሳሳትኩ አፉ ብለው ያርሙኝና  በእነሱ ሙያ  Drug tolerance የሚሉት ነገር አለ አሉ፤ በትክክል ከተረዳሁት ለሆነ ህመም የተሰጣችሁ መድሀኒት ከሆነ ጊዜ በኋላ በሽታችሁ ጋር ይግባቡና ፍሬንድ ይሆናሉ። በሽታው መድሃኒቱን ይላመደዋል።ጉቦ እንደበላ ደንብ አስከባሪ በሽታችሁ መንገድ ዳር ሲያሰጣችሁ መድሀኒቱ እንዳላየ ያልፈዋል። ለምሳሌ የእንቅልፍ ችግር ገጠማችሁና በሐኪማችሁ የእንቅልፍ ኪኒን ታዘዘላችሁ እንበል ፤ የመጀመሪያ ሰሞን ድብን ያለ እንቅልፍ ያስወስዳችኋል፤ እየቆየ ሰውነታችሁ ሲላመደው መድሀኒቱን ውጣችሁም ቁልጭ ቁልጭ ስትሉ ታነጋላችሁ። ወይ አይነቱን ወይ መጠኑን ባለሙያ ካልቀየረው በቃ ለውጥ የለም። አይ መጠኑን ራሴ እቀይረዋለሁ ብላችሁ ጨመር አድርጋችሁ ከወሰዳችሁ ደግሞ ትተኙ ይሆናል ግን እንደገና ላትነሱ ትችላላችሁ።

🔑ወደህይወት ስናመጣው እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ሰዓት ማንኛውንም ማነቃቂያ ከመላመድ አልፈን እንደዘፈን ሸምድደነው አብረን እየደገምነው ነው። ገና ፊቱን ስታዮት አብራችሁ  "ብሮሮሮሮሮ" አትሉም?!  ለዛ ነው ከነዋሪ መካሪና ዘማሪ የበዛው። የፈለገ ብንመከር ብንዘከር ብንሰበክ ብንወገዝ ወይ ፍንክች። አሁን ሞራል፣ ሐይማኖት፣ የአገርም ይሁን የሰው ፍቅር፣ ይሉኝታ ፣መማር ፣ የራስ ክብር ወዘተ አእምሯችን ተላምዷቸው ተራ ነገር ሁነውብናል።

✨የሞራል ተቋሞቻችን  በሞራል ድሽቀት ከተራው ህዝብ ቀድመው ባፍጢማቸው ተተክለዋል፤ የትዳር ሰባኪወቹ  ማግባትና መፍታት መድረክ ላይ እንደመውጣትና መውረድ ቀሏቸዋል፤እንደውም የጓዳቸውን ውድቀት እንደባንዲራ በአደባባይ እየሰቀሉ እዮልን ባይ ሆኑ።  አሁን እንደህዝብ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው የሚያነቁን ወይ (((ብር ማጣት))) አልያም (((ብር ማግኘት))) ይሄ የመጨረሻው ዶዝ(መጠን) ነው! 

💎ሰው ክብሬ፣ ገመናየ ፣ማንነቴ የሚለውን ነገር ሁሉ ይዞ ገበያ ከወረደ ምን ይመልሰዋል?! ከዚህ በኋላስ? ምን ያነቃን ይሆን?  ምክንያቱም በብር የሚመጣ ንቃት በአንዴ አይረካም፤ እንደአደንዛዢ ዕፅ  በየቀኑ መጠኑን እየጨመሩ ካልወሰዱት መጨረሻ የለውም። መመለስም መቀጠልም የማንችልበት አውላላ ሜዳ ላይ የሚያስቀር መርገምት ነው!! ምን ላድርግ ቸገረኝ፣ የማደርገው አጣሁ ልሙት እንዴ ታዲያ  በሚል ሰበብ ከሰውነት ድንበር ከምንርቅ በየግላችን "ይሄንኛው ነገሬ ለገበያ ከሚቀርብ ሞቴን እመርጣለሁ" የምንልለት የሆነ መስመር ልናሰምር ግድ ነው። ሰው ራሱ ወስኖ ያሰመረውን መስመር ከሞት በስተቀር ምን ያሻግረዋል?!

✍አሌክስ አብርሃም

        ሸጋ ቅዳሚትን ተመኘን!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


🔴ዛሬ ስለማለት መብት እንናገራለን... የምንለውን እንድንል የሚሉትን እንዲሉ ስለመፍቀድ እናወራለን...

🔷ምንድነው ግን እንዲህ አመክንዮ አልባ ያደረገን? ፣ የማለት በር ይከርቸም.. እኛ ብቻ እናውራ የሚያሰኘን ምን ይሆን?... የሌላውን የማለት መብት እግር ከእግር ተከትለህ ስታብጠለጥል የምትጠቀመውን መብት እኮ ነው ተተቺህ የተጠቀመው ፣ እንዳንተ አለማሰብን ስህተት ያደረገው ማን ነው?... እስኪ አንዳንዴ እንኳን ከተባለው ነገር በፊት ለመባሉ እውቅና ስጥ።......ከዚያ አባባሉን ከግለሰቡ ነጥለህ.. በማስረጃ አስደግፈህ.. ወይም ደግሞ ከእይታህ አዋቅረህ ተች... ገና ለገና 'ሃሳቡ ከሃሳቤ ተጣርሷልና .. ቅኝቱ ከቅኝቴ ተፋልሷልና እገሌ የያዘው የረዘዘው ምንትስ የነካው እንጨት ይሁን' ማለት የእውነት Fair አይደለም።

በግሌ የማለት መብት መጋፋታችን ብቻ አይደለም የሚያሳስበኝ አንዳንዴ ወደላይ ምን ካላልን የምንለው ነገር አለን። ያለሙያችን ፣ ያለሜዳችን... ይሄ እውነተኛን ሂስ በስሜት አረንቋ ውስጥ ይደብቅብናል። በዚህ መሃል ፍሬና ግርዱ ተቃቅፎ ይኖራል ፣  አንዳንዴ አንዳንዶች ራሳቸውን እንዲሰድቡ መፍቀድም ብልህነት ነው...

♦️ሌላ የምንረሳው ነገር ደግሞ ተቺውም ሆነ ተተቺው የትችት ሰበብ የሆነው ፣ ነገሩ ያብብ ..... እርስ በእርስ ያማምር ዘንድ አስፈላጊ መሆናቸውን ነው። እርስ በርስ ካልተያየን እንዴት ልናድግ እንችላለን?... የኔ ስህተት ባንተ ክህሎት ይቃናል... ያንተ ጥፋት በእርሷ ጥቁምት ይፋቃል እንጂ አትድረሱብኝ በሚል ስሜታዊነት እንዴት ይጎለምሳል?... 'አትንኩኝ የሹም ዶሮ ነኝ' ለማን ይበጃል?...

🔷የአንዳንድ ነገሮች ድጋፋችን ጭፍን ስሜት ይጫነዋል ፣ ዳንኤል ክብረት አንድ መድረክ ላይ ".. ወጣቱ ባዶ ቅናት ይቀናል..." ሲል ሰምቼዋለሁ... ባዶ ቅናት ስለጉዳዩ በቂ ግንዛቤ ሳይዙ በጥቅል ስሚያ ላይ ከመመስረት የሚመነጭ ስሜት ነው። አንድ ሳር ቅጠሉ ሆ.. የሚልለትን ሰው/ስራ ሌላው ሰው ሲተች የኛን ድንቅ የማሳየት መንገድ መከተል አይደለም የሚቀናን፣ እንዴት እነካለሁ በሚል ቅኝት መደንፋት እንጂ፣ በዚህም ምክንያት እኛም ስለነገሩ ሳናውቅ.. ተቺውም ከስህተቱ ሳይታረቅ ይቀራል... ከትችቱ ቁምነገር የመገብየቱ ነገርማ አይታሰብም.......።

♦️ምን ለማለት ነው?... የተባለው ነገር ፈጽሞ የማንቀበለው ሊሆን ይችላል... አለመቀበላችን ግን የመባል መብቱን መጋፋት የለበትም... ልክነትና ስህተት በመቀበል/መተዋችን ውስጥ ቦታ የለውም... በነገሩ ተፈጥሮ ውስጥ እንጂ...

🔶 ስለዚህም... 'እንዴት እንዲህ ትላለህ?' ሳይሆን 'እንዲህ ማለትህ ከዚህ ከዚህ አንፃር ስህተት ነበር' ማለትና ለውይይት በር መክፈት የተሻለ ነው... ለምን ቢባል ... አንዳንዴ ተመሳሳይ እሳቤንም በተለያየ ቋንቋ እያወሩ 'የተለያዩ' መምሰል አለ... አንዳንዴ ሽንጥ ገትረው የተሟገቱለትን ጉዳይ አድሮ መተውና በሌላኛው ሰው ጫማ ውስጥ መገኘት አለ... ደግሞ አንዳንዴ የትችቱ መልስ ዝምታ መሆን ተቺውን ወደራሱ እንዲያይ ዕድል ሰጥቶት መግባባት አለ...

📍ፈረንሳዊዉ ቮልቴር ለአንድ ጓደኛው በፃፈው ደብዳቤ ላይ ለማለት መብት መቆሙን ያሳየበት መንገድ ድንቅ ነበር... እንዲህ ብሏል:
"I disapprove of what you say, but I will defend to the death your right to say it."


ፍቅርን ከመስጠት በላይ ዕዳ አይኑርባችሁ!!❤️

                             ✍ ደምስ ሰይፉ

         ፏ ያለች ቅዳሚት ለሁላችን😉

@BridgeThoughts
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


🛑 The Golden Rule

ኢየሱስ በወንጌሉ ያስተማረው፤ ነብዩ ሙሀመድም በአስተምህሮቱ ፣ ቻይናዊው ፈላስፋ ኮንፊሽየስም በፍልስፍናው የሚመክረው ተመሣሣይ ሃሳብ ያለው አባባል አለ፡፡ ይሄ አባባል በየትኛውም እምነት ተከታይ አማኝ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሃሳብ ነው፡፡ አይደለም እምነት ላለው ሰው ቀርቶ በኢአማኙም ዘንድ የሚደገፍና የሚከበር ሃሳብ ነው፡፡ ሕሊና ያለው ሰው ሁሉ በዚህ ሃሳብ ይስማማል፡፡ ይሄ አባባልም ወርቃማው ህግ ይባላል፡፡ ወርቃማነቱ በሁሉም ሠዎች ዘንድ ተቀባይነቱን መሠረት ያደረገ በመሆኑ ያገኘው ስያሜ ነው፡፡
ሕጉም እንዲህ ይላል፡-

🔑‹‹ለራስህ የማትፈልገውንና የማትመርጠውን ነገር ሌሎች ላይ አትጫን!›› ወይም ‹‹አንተ ላይ ሊሆንብህ የማትፈልገውን ነገር ሌሎች ላይ አታድርግ! (“Never impose on others what you would not choose for yourself.")

🔷ይሄን ሕግ ተለማምዶ መተግበር የቻለ ሠው በሌሎች ሰዎች ላይ ስቃይ፣ እንግልት፣ ማፈናቀል፣ ማሰደድ፣ ግድያ አይፈፅምም፡፡ የወገኖቹን፣ የብጤዎቹን ንብረታቸውንና ጥቅማቸውን፣ መብታቸውንና ነፃነታቸውን ያከብራል፡፡ ‹‹ነግ በእኔ›› በሚል ሌሎችን እንደራሱ ይወዳል፡፡

📍‹‹ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ›› የሚለው ታላቅ ሕግ ወርቃማውን ህግ አቅፎና ደግፎ ይዟል፡፡ ራሳችንን የምንወድበትን ያህል ከፍታ ሌሎችን መውደድ ከቻልን ዓለም ሠላማዊና በፍቅር የተሞላች ትሆናለች፡፡ እኛ ላይ ሊሆን የማንፈልገውን ሌሎች ላይ እንዲደርስባቸው አንመኝምም፣ አናደርግምም፡፡

ነገር ግን በገሃዱ ዓለም የሚታየው እውነታ ከዚህ በተቃራኒ የቆመ ነው፡፡ ትዕዛዙ ሳቢና በሁሉም ሠዎች ዘንድ የተወደደ ቢሆንም የሠው ልጅ ግን በተግባር እየኖረበት አይደለም፡፡ የአንዱ መጥፋት ለሌላው መልማት ዋና ምክንያት እስኪመስል ድረስ በተንኮል፣ በሴራ ፖለቲካ፣ በጥላቻ ጥልፍልፍ ደባ መጠፋፋት የዘመናችን ልማድ ከሆነ ሠነባብቷል፡፡ ራስን መውደድ ብቻ የተጋነነበትና ሌሎችን እንደምንም በመቁጠር ሰውነትን እስከመዘንጋት ተደርሷል፡፡ የሰው ልጅ በራሱ ወገን እንደአውሬ እየተባረረ ይጨፈጨፋል፣ አካሉ ይጎድላል፣ ይገደላል፡፡ በጣም ብዙ በደልና ስቃይ በገዛ ብጤው የሰው ልጅ ይደርስበታል፣ በወገኑ ይጨቆናል፡፡

💡ነገር ግን የታላቅነት ሚስጥር፣ የአዋቂነት ጥጉ ሌሎችን በነጻ መውደድ እንጂ ጥቅምና መብታቸውን ጨፍልቆ ክፋትና ጭካኔን፣ ተንኮልና ሴራ መስራት አይደለም፡፡ በዚህ ዘመን የፖለቲከኝነት ጣሪያው፣ የታዋቂነት ዙፋኑ ሴራ ጎንጉኖ ሌሎችን መጣል እንጂ በሀሳብ ልዩነት ተከባብሮና ተግባብቶ መኖር አይደለም፡፡ መቼም ቢሆን ታላቅነትና ሊቅነት ሌሎችን በማቀፍ እንጂ በመገፍተር የሚገለፅ አይሆንም፡፡

ለዚህ ጉዳይ የኮንፊሽየስን ምክር ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ አንድ ቀን ኮንፊሽየስ ለተማሪዎቹ ምክር በመስጠት ላይ ሣለ፤ አንዱ ተማሪ አቋረጠውና፡-
‹‹ታላቅ መሆን እፈልጋለሁና መንገዱን አሳየኝ›› አለው፡፡ ኮንፊሽየስ ሲመልስ፡-
‹‹ታላቅ የሚባል መንገድ የለም፤ ነገር ግን ሰው መንገዱን ታላቅ ያደርጋል›› አለ፡፡

💡እውነት ነው! ሰው መንገዱን ታላቅ የሚያደርገው ሰውነቱን በማረጋገጥ ነው፡፡ የመጀመሪያው ስኬት ሰውነትህን ፈትነህ፣ ስሜትህን ገርተህ ፣ ልቦናህን አቅንተህ ፣ ማስተዋልን ተግብረህ ሰው መሆንህን ማስመስከር ነው፡፡ ሰው መንገዱን ታላቅ የሚያደርገው ወደ ሰውነቱ መመለስ ሲችል ብቻ ነው፡፡ ሰው ሰውነቱን አጥብቆ መያዝ ከጀመረ የሌሎችን ሰውነት ያከብራል፡፡ የሌላው ሰውነት የተሠራውና የተዋቀረው እሱ በተሠራበት የሠውነት አካል መሆኑን ይረዳል፡፡ ሌላውም እንደእሱ ፍቃድ፣ ፍላጎት፣ መብትና ነፃነት እንዳለው ይገነዘባል፡፡ በዚህም በሌላው ላይ ክፉ አያደርግም፤ ነጻነቱን፣ መብቱን፣ ጥቅሙን፣ ወዘተ ያከብራል፡፡

ወዳጆች ሠብዓዊነት ማለት ሰውን ሁሉ ያለአድሎ ማፍቀር ነው፡፡ ዕውቀትም ሠውን ጠንቅቆ ማወቅ ነው፡፡ ማወቁ ለፍቅር ይዳርገዋል፡፡ ሰውን ያህል ድንቅ ፍጥረት የተረዳ ሰው በገዛ ወገኑ ላይ ክፉ አያደርግም፡፡ በራሱ ሊደርስበት የማይሻውን በሌሎች ላይ አያደርግም፡፡ ይሄን ህግ ሁላችንም ብንለማመደውና ብንተገብረው ሠላም፣ ፍቅር፣ ደስታ፣ መስማማት፣ መተቃቀፍ፣ መግባባት ሀብቶቻችን ይሆናሉ፡፡

📍እናም ሰው ሆይ አንተ ላይ የማትፈልገውን ሁሉ ሌሎች ላይ አታድርግ፡፡ ምን ስልጣን ይኑርህ፣ ምን ሊቅ ሁን፣ ምን ሃብት ይኑርህ፣ ምን ዝነኛ ሁን፣ ምን ዘመድ ይኑርህ፣ ምን ባለጊዜ ሁን፣ ምን ተከታይ ይኑርህ ሌሎችን በእጆችህ እቀፋቸው አንጂ አትገፍትራቸው፡፡ እጆችህን ለማቀፍ፣ ልብህን ለመውደድ፣ ዓይንህን ቅን ለማየት፣ አንደበትህን ለበጎ ቃላት ተጠቀምበት፡፡ ሕሊናህን ሌሎችን ለማፍቀር እንጂ በመጥላት አታባክነው!

                  ✍እሸቱ ብሩ ይትባረክ

          ያማረች ቅዳሜን ተመኘን ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthiohumanityBot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


እዚህ የሃሳብ ድልድይ አለ... 
እዚህ የመገናኛ ድልድይ አለ... 

__

ድልድይ
-

ሰው ከራሱ እውነት የሚገናኝበት የቆምታ ታዛ ነው... 
ከውክቢያ ተፋትቶ የሚያስተውልበት ፋታ ነው... 
ከእልፊት ጸጸትና ከመፃኢ ስጋት ተላቆ ከአሁንታ እውነት የሚገናኝበት ከፍታ ነው... 
__

ከሚተነፍግ የዓለም ጣጣ፣ ከማይሞላ የኑሮ ሩጫ እፎይ ማለት ሲሹ ጎራ ይበሉ... መልካም ማረፊያ ነው...

__

ይቀላቀሉ፣ ወዳጆችዎንም ይጋብዙዋቸው!!
_👇👇

@bridgethoughts
@bridgethoughts


ዛሬ ቅዳሜ ነው የኛ ሸሞንሟና ሸሞንሟኒት😊

የyoakin Bekele Pachiን ጹሁፍ
        ጀባ እንበላችሁ........

💫ዕድሜያቸው 30+ የሆኑ ሴቶች ይፀዱኛል:: በቃ ይመቹኛል:: እንደ ሰው በጥልቅ ማውራት የሚቻለው ከእነሱ ጋር ነው:: የምታወራው  ይገባታል ፣ የምታወራህ ይገባሃል ደርባባ ናቸው ፣ ሞገስ አላቸው ፣ አንደበታቸው ቁጥብ ነው የሚፈልጉትን ያውቃሉ:: ወዝጋባና ጢባራም አይደሉም:: ለጓደኝነት እና ለቁምነገር ምርጥዬ ናቸው::

💡አንባቢ እና አድማጭ ከሆኑ ደግሞ ክትት ያለ የበሰለ አቋም አላቸው:: ስለፈለከው አጀንዳ ቀለል ብሎህ ታወራታለህ ስለ ባይደን ፣ ስለራሺያ ፣ ስለ ሶሪያ ፣ ስለ ያ ትውልድ ፣ ስለ ጀብሃ ስለ ሻቢያ ፣ ስለ አድዋ ፣ ስለ ማይጨው ፣ ስለ ካራማራ:: ስለ Netflix ፣ ስለ አባ ገብረ ኪዳን ስብከት ፣ ስለ ሄኖክ ኃይሌ ትምህርት ፣ ስለ ምህረተአብ ቴቄል ፣ ስለ ተቀዳሚ ሙፍቲ መጅሊስ ፣

🔆ስለ ዮናታን መልካም ወጣት ፣ ስለ እመቤቴ ማርያም መራር ሃዘን ፣ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ፣ ስለ አምኖን ቅንዝራምነት ፣ ስለ ዮናታን እና ዳዊት ወዳጅነት ፣ ስለ ቶማስ ስኬፕቲካልነት ፣ ስለ ቮልቴር ቡና ሱስ ፣ ስለ ቫንጎህ ስዕልና ቺስታነት ፣ ስለ ካህሊል ጂብራን ብዕር ፣ ስለ አዳም ረታ ፣ ስለ ስብአት ገብረ እግዚአብሔር ጠሊቅነት ፣ ስለ ፌሚኒዝም ፣ ስለ ካቲታሊዝም ስለ ሙላቱ አስታጥቄ ጃዝ ፣ ስለ ግርማ በየነ ፣ ስለ Nina Simon ፣ ስለ ኤልያስ መልካ ቅንብር ታወራሃለች ፣ ታወራታለህ!

ፊቷን ጥላው ካገኘሃት ደግሞ ምነው ውሃ ጠፋ ፣ አብሲት ተበላሸ ፣ የቂቤ ዋጋ ጨመረ?  ፣ ጎረቤት ለቅሶ አለ? ፣ በርበሬ አልተፈጨም? ምናምን ምናምን ትላታለህ!

⚡️መሸት ብሎ እንደ ኡመር ኻያም ወይን ከቀማመሰች ደግሞ ስለ አንገት ስር Cuddle ፣ ስለ For Play ታወራታለህ ፤ አፏን ሸፍና ወፍራም ሳቅ እየሳቀችና (አታሳፍረኝ አይነት) ጎንህን ጉሽም እያደረገች እሷም ታወራሃለች::  ሃሳብ ትለዋወጣለህ ፣ ትስቃለህ ፣ ትዝታ ትፈጥራለህ።

💡ፍቅራቸው የሚቆየው እንደ ወሲብ ለአምስት ደቂቃ ሳይሆን ለዘለአለም ነው:: ምክንያቱም ፍቅራቸውን የሚተክሉት በእግሮቻቸው መሀል ሳይሆን ከዛ ከፍ ብለው በልቦቻቸው ውስጥ ብሎም በአዕምሯቸው ውስጥ ነው:: ፍቅር የሚይዝህ ከአካላዊ አቋሟ ሳይሆን ከአስተሳሰቧ ፣ ከስብዕናዋ ፣ ከነፍሷ ነው::

ፍቅር ሞልቶ የሚፈስበት
ደርባባ ቅዳሜ ተመኘን!❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


💎የራስ ቀለም

"በዚህች አለም እንተን የሚመስል ሰው ተፈጥሮ አያውቅም ወደፊትም አይፈጠርም በቃ አንተ አንተን ሆነህ ብቻ አንዴ ተፈጥረሀል..." - ዴልካርኔጊ

💡 በራሳቹ ቀለም እጅግ ውብ ናቹህ በራሳቹ አለም እንደመልአክት ታብረቀርቃላቹህ በራሳቹህ መንገድ እንደንጉስ ትራመዳላቹህ ። ውበታቹህ እርሱ ነው እናንተነታቹህ የነፍሳቹህ ብርሀን መንገድ ነው። አለም በቀደደላቹህ ቦይ እንድትፈሱ ፈጣሪያቹህ አልተጠበበባችሁም በእናንተ የተጠበበ'በትን ህይወት ለመኖር ወደ ልባቹህ መቅደስ ብቻ ፍሰሱ... እግራቹህን ከልባቹህ ጋር አስተሳስሩ ልባቹህ ወደ መራቹህ ሂዱ ፣ ይሄ ነው ህይወት....... ይሄ ነው መተንፈስ..... ይሄ ነው መንቀሳቀስ.....

⏳በእግርህ ከመተማመንህ አስቀድሞ ፡ የምትጓዝበት መንገድ ይኑርህ ፤ ምክንያቱም በዚህች ተራራማ ፣ ሜዳማ ፣ በረሃማና ረግረጋማ ዓለም ላይ እግር ያላቸው ሁሉ አይጓዙም መንገድ ያላቸው እንጂ ፡ ስለሆነም ከርምጃህ መንገድህ ይቅድም !"። ህይወትህን ከፉክክር አልቀው ወደ ተፈጥሮ ዝለቅ በፀሀይ መውጣት እና መጥለቅ ተመሰጥ በከዋክብቶች ፊት ዳንስን ደንስ ከጨረቃዋ ጋር ተወያይ በፅጌሬዳ ፍካታዊ ውበት ነፍስህን ከስነፍጥረት ጋር አዋህደው።
                  
የሕይወት ጎዳናህ ርዝማኔ ዕድሜህን የመወሰን አቅም ስለሚኖረው ፣በቀን ከፀሐይ ተዋህደህ አርቀው ፣ በምሽትም ከጨረቃ ተማክረህ አርቅቀው ፤ ስጋህን ከጀምበሯ ሙቀት አላምደው ፡ ነፍስህንም ከጨረቃዋ ብርሃን አስታርቀው ፤ፀሐይዋን የሚጋርድህ ፡ ከጨረቃዋም የሚደብቅህ አንዳችም ኃይል የለም ፤ ራስህ ካልሆንክ በቀር።

⌛️ተራራማ ፣ ሜዳማ ፣ በረሃማና ረግረጋማ የሕይወት ጎዳናህን ከጀምበሯ ዕለታዊ የብርሃን ዕድሜ አንፃር አንፅረህ በማስተዋል አስልተህ ቀምረው ፤ ተራራውን ፣ ሜዳውን ፣ በረሃማውንና ረግረጋማውን ምድራዊ ስፍራና የጎዳናህን አካል በጨረቃዋ ጥበባዊ ምስጢር መስጥረው ፤ ከጨረቃዋም የውበት ውቅያኖስ ቀለም በሰዓሊነት መንፈሳዊ ብሩሽህ እየጨለፍክ አስውበው።

📍ተፈጥሯዊ ነህና ስጋዊ ዓይንህ በቀን ብርሃን የመመልከት አቅም እንዳለው ሁሉ በምሽት የጨለማ ጊዜም መንፈሳዊ ዓይንህ የጠራ የማስተዋል ኃይልን ታድሏልና ሳትደናገጥ ሳትፈራ በራስ መተማመን ቀን ያየኸውን ተራራ ተንደርደረው ፣ የውቅያኖሱን ሞገድም ሰንጥቀህ ቅዘፈው ፣ በረሃማውን ረግረጋማውንም የጎዳና አካል፣ በእባብ ብልህነት በጊንጥም ፅናት በሌሊት ወፍ ምስጢራዊ አከናነፍ ተምሳሌታዊ ስልት በዝግታ በማስተዋል፣ ከጊዜም ሙዚቃዊ ስልተ-ምት ጋር ተዋህደህ በመዝናናት፣ መንፈሳዊ ክንፍህን እያርገበገብክ በዳንስህ ክነፍ-ብረር-ድረስ እንጂ ከአላማህ ፈፅሞ እትቁም።

💡ነፍስህን ለማደስ ከፀሐይዋ ብርሃን ሙቀት ውሰድ ፡ ከጨረቃዋም ብርሃን ውበትን ቅዳ ፤ልብ በል… ተፈጥሮ የሙዚቃ መሳሪያ ..... አንተ ዳንሰኛ.... ሕይወትም ሙዚቃ ናት። ፀሐይ ጨረቃና የሰማይ ከዋክብትም በጎዳናህ ክበባዊ ዙሪያ በሰልፍ እንደተኮለኮሉ በዳንስህ ለመዝናናት እንዳሰፈሰፉ ተመልካቾች መሆናቸውን ልብ በል።

🔑በተፈጥሯዊው ሕግ መሰረት ካንተ የሚጠበቀው የሕይወትን ሙዚቃ በነፍስ መንፈሳዊ ክንፍ እየደነስክ ጎዳናህን በዳንስ ልትበርበት እንደምትችል ብቻ ማመን ነው። ከሺ አመታት በፊት የተፃፈው ታላቁ መፅሃፍ ከሽህ አመታት ቡሃላም ይናገራል 'ዕመን እንጂ አትፍራ !' የትርጉሙ ምስጢር የጥበብ ተምሳሌትነቱም ይህ ነውና።

✍ Tupaca Ela

             ውብ ሰንበት❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot




📍ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳችንም በህይወት አንገኝም። ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡

🕯በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት የነበሩ፡፡ የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ አላፊ ጠፊ ሆነው እናስተውላቸዋለን፡፡ ሌላው ይቅርና በሽታ እንኳን ሩቅህ አይደለም፣ የተዘረጋው እጅ አሁን በቅፅበት ማጠፍ ሊቸግርህ  ይችላል። በሃብታችን በእውቀታችን በዝናችን .... አለን ባልነው ነገር ሁሉ መማፃደቁ ከንቱ ነው .... ሌላው ቢቀር የዘረጋነውን  የምናጥፈው በፈጣሪ ቸርነት ነው።

💡ታላቁ እስክንድር ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ ፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ። ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው።

🔷ብርሌ በመሰለ ዓለም ፡ መጥፊያው ሰፊ መልሚያው ጠባብ በሆነ ኑሮ፣ በዙፋን ላይ ካለ ንጉስ  በፈጣሪው የታቀፈ አማኝ ይበልጣል!! Impermanenceን በቅጡ የተረዳነው ያህል ሆኖ ያታልለናል። በሕይወት መንገድ ስለ ጤዛነት ብዙ እያየንም አልማር ብሎ የፈተነን አንጎላችን ብዙ ያነበብነና ያወቀ ይመስለዋል።

ማጠቃለያው፣

📍ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ እንደ ትልቅ ሀብት የምናያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡

ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መከባበርን እናስቀድም፣ከጀርባ መወጋጋት፣ መጠላለፍ አክሳሪ ነው፡፡ ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ የሰው ሕይወት በምድር ላይ በጣም አጭር ናት። ኑሮ ማለት ደግሞ በውልደት እና በሞት መካከል ያለ የመሸጋገሪያ ጊዜ ነው። በድንገት ተጀምሮ በድንገት የሚቆም የመሸጋገሪያ ጊዜ.......

💡ቃሉም እንደሚለው "ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና።ያዕ 4፡14

💡ሀዲሱም እንዲል "ምድር ላይ ስትኖር እንደ እንግዳ እንደ መንገደኛ እንደ አልፎ ሂያጅ ሆነህ ኑር" (ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ )

🔑 በዚህ ዓለም ላይ ምንም ቋሚ የሚባል ነገር የለም እንኩዋን ሰውና ግዑዝ ነገር ሁሉ አላፊ ነው . . . እንደ አልፎ ሂያጅ አልሆንም ብንልም ማለፋችን አይቀርምና መልካም ስራን ለነፍሳችን እናስቀድም ዘንድ ፈጣሪ ያግዘን።
         
                 ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


📍ተከታይህ ከህሊና ድህነት አያድንህም፤ ሃብት ንብረትህ አስተሳሰብህን አይቀርፅም፤ ወዳጆችህ ውስጣዊ ሰላም አይሰጡህም። በእውነት ካልተመራህ፣ በስረዓት ማሰብ ካልቻልክ፣ ጥያቄህን ካልመረጥክ፣ ተግባርህን ካልቆጠብክ ጉዞህን እንጂ መውደቂያህን አታስተውልም፤ ጭብጨባውን እንጂ ስህተትህን አትረዳም፤ ድጋፍህ እንጂ ጥፋትህ አይገባህም።

አዕምሮህን ክፍት ማድረግህ ሚዛናዊ ማንነት እንዲኖርህ ያደርግሃል። መስማት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ይሰማህ ይሆናል፤ የሚወድህም ይከተልህ ይሆናል፤ የሚያምንብህም እንዲሁ ሊያሽቃብጥልህ ይችላል። እውነታ በሌለበት ግን ማንም ሰው እስከመጨረሻው አብሮህ እንደማይቆይ እወቅ። ጥልቁ ማንነትህ እንጂ የያዝከው ጊዜያዊ ንብረትና ዝና ነፃ አያወጣህም።

🔷ስትታወቅና ከፊት ስትሆን በእውቀት እና በጥበብ ካልተጓዝክ ብዙ ነገር ታበላሻለህ፡፡ በሰዎች ሙገሳና አድናቆት በሞቅታ መስመር ትስታለህ፡፡ ዛሬ ላይ  ሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ተከታይ ለማግኘት ካሰብክ ካንተ ሚጠበቀው  ለገንዘብ ተገዝተህ ወጣ ያለ አቋም መያዝ፣ ሌላ ፆታን ማራከስ፣ ሌላውን ብሄር  በመጥፎ ማውገዝ ነው። ያኔ ማን ይሆን እሱ! እያለ ሁሉም ካለበት ቦታ እየሮጠ ይመጣልሃል።

♦️ወዲህ ግን ቁምነገር የሚጽፉ ተከታያቸው ጥቂት ብቻ የሆኑ ጠንካራ የማህበረሰብ አንቂዎች አሉ። ግና ሰው ስለራሱ ነውርና እንከን ለመስማት የሸሸበት የረሳበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ከዕውቀት ከጥበብ ይልቅ ስላቅና ፣ ዘለፋን  ያስበለጠበት ዘመን ላይ እንገኛለን። እስቲ ይሄን ሥልጣኔ ያለንበትን ነገር በጥሞና ተመልከቱ። የዘመንኛው ቁሳዊ ሥልጣኔ ግኝቶችን ልብ እንበል። ዓለም ላለባት ችግር መፍትሔ ከመሻት ይልቅ፤ ግኝቶቹ ራሳቸው ከምንም የከፋ ችግር እየሆኑ እንዲያውም የቀደሙትን ችግሮች እስከማስረሳት ደርሰዋል። ግኝቶቹ ከሚያስከትሉት ጠንቅ ይልቅ በግኝቶቹ የሚገኘው ኃይል ገንዘብና ዝና ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶታል ።

🔑እናም ወዳጄ ቁምነገሩን ስንቅ አርግ

ዋናው ጉዳይ የሰው ክትትል ወይም ጭብጨባ አይደለም፤ ከፈጠረህ አምላክ አንፃር ትክክል ከሆንክ የፍጡራን ክትትል አያሳስብህ። ፊት መሆን በሚችል ስብዕና ከፊት ቁም፣ ጊዜህን አፍ በመካፈት አትብላው፣ አለምን የገዙ ፣ በአስተሳሰብ ሊቅነታቸው አርአያነታቸውን የምንከተላቸው ፈላስፎች ፣ ተመራማሪዎች፣ የህይወት መንገድ እያመቻቹልን እነሆ በዚህ ተጓዙ፣ ያኛው የብዝኋኑ መንገድ አሜኬላና እንቅፋት አለው። የዓለም ምስጢራት የሚገለጡት በስውር መስመር ነው እያሉ አመላክተውናል።

ለሰው ልጅ በተሰጠው ወንበር ላይ ቁጭ ብለን ሰው የመሆናችንን፣ ሰው የመባላችንን ልዩ ገፀ-በረከት የሚያጎናፅፉን ሀብቶቻችን እንከተል።

💡ህሊና ይፈርዳል፣ የእራሱን ብይንም ይሰጣል። ስለተጨበጨበልህ እውነት ተናግረሃል ማለት አይደለም፤ ተቃውሞ ስለበዛብህም ውሸት ተናግረሃል ማለት አይደለም። ለሁሉም ሰው የተሰጠው ህሊና የመንገድህ መሪ፣ የንግግርህ ቆንጣጭ፣ የተግባርህ አራሚ ነው። ለመፍረድ አትቸኩል፤ ለንግግር አትጣደፍ፤ እውነታውን በጥላቻህ አትሸፍን፤ በእውቅናህ ሰላምን አትግፋ፤ በተሰሚነትህ ክፍተትን አታስፋ። ውሸት የአብሮነት ምክንያት ሆኖ አያውቅም፤ ተንኮል ፍቅርን አንግሶ አያውቅም፤ ጥላቻም የሰላምን በር ከፍቶ አያውቅም።

♦️ሁሉን ያገኘህው በፈጣሪህ ሞገስ እንጂ አንተ አምጥተህው አይደለምና ለበጎ ተጠቀመው። እውነትን በፍቅር ያዝ፣ ለሰላም ግድ ይኑርህ፣ ለመከባበርም ቅድሚያ ስጥ። ትዕቢትን፣ ጉራን፣ ጀብደኝነትን፣ ጥቅመኝነትን ከውስጥህ አስወግደው የመልካምነትን ስብዕና ገንባ፣ ጥሩ መሪ ፣ ጥሩ ተከታይም ሁን።

    ደርበብ ያለች ቅዳሚትን ተመኘን 😉

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
💫May this Serve as a living tribute,
To Fendika Art Center.

Words of wisdom,
Shared by Melaku Belay ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
📍ሰው አገሩ ሰፈሩ ነው ህዝቦቼ እያለ ያደገው ጎረቤቶቹን ነው ።ማንነቱ የተጎነጎነው ከጎረቤቶች ማንነት እየተውጣጣ ጭምር ነው። ከሰፈር አግብቶ መውጣት በስራ ሌላ ቦታ መሄድ እና ያደክበት ስፍራ ሲፈርስ ልዩነቱ የትዬለሌ ነው ።

እሚፈርሰው ሰፈር ውስጥ ትዝታ ልጅነት ታሪክ ተጠቅልሏል ። ማህበራዊ ህይወት ያቆመን ህዝቦች ማህበራዊ ህይወታችን ሲበተን ማየት ድባቴው ካቅም በላይ ነው።

ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው ህልሙ ነው!
ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው ፀሎቱ ነው !
ምን አልባት እኛ ያለፈን የማይጠቅመን ነው!
ምን አልባት ያሳመመን ሊያስተምረን ነው!
ምን አልባት የሆንነው የሆኑትን እንድንረዳ ነው !
ምን አልባት የተበለሻሸው እንድንቀያይረው ነው!
ምን አልባት አማራጭ ያጣነው አማራጭ እንድናመጣ ነው !

"እኛ በህይወት ካለን ሌላ ካዛንቺስ እንገነባለን ፣ መኖር እስከነ-ትግሉ እስከነ ፈተናው ደስ ይላል"።

                       ✍አዳህኖም ምትኩ

  የካዛንቺስ ውብ ፈርጥ አለማየሁ ገላጋይ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot

20 last posts shown.