#Tigray
“ በጀት ተፈቅዷል። ትክክለኛ ቁጥሩን በሚመለከት ግን ገና እንነጋገራለን ” - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የፌደራል መንግስት፤ ለትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ ለመልቀቅ መስማማቱ ገለፁ።
አቶ ጌታቸው ፤ የፌደራል መንግስት ለትግራይ ክልል በጀት ለማስተላለፍ ከስምምነት ላይ መድረሱን የገለፁት ለ “ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ” ድረገፅ በሰጡት ቃል ነው።
ምንም እንኳን በጀት ለማስተላለፍ ስምምነት ላይ ቢደረስም የሚለቀቀውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ግን ገና ውይይት እንደሚካሄድ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?
“ በጀት ተፈቅዷል። [ትክክለኛ] ቁጥሩን በሚመለከት ግን ገና እንነጋገራለን ”
NB. ከተሾሙ በነገው ዕለት አንድ ሳምንት የሚሞላቸው አቶ ጌታቸው ረዳ 11 የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላትን ይዘው ከፌደራል መንግስት ጋር ለመነጋገር በአዲስ አበባ ከተማ ይገኛሉ።
የትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ መቼ እና ለምን ነበር የተቋረጠው ?
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመስከረም 2013 ባስተላለፈው ውሳኔ ነው የትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ የተቋረጠው።
የበጀት ድጋፍ እንዲቋረጥ የተደረገው፤ ክልሉ ከፌደራል መንግስት እውቅና ውጭ “ኢ-ህገ መንግስታዊ ምርጫ አካሄዷል” በሚል ነው።
Credit -
www.ethiopiainsider.com