Bright Minds Academy☀️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


በቻናላችን የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች
✅ entrance exam
✅extreme book & referance book
✅Textbook ( 9-12 )
✅Teachers Guide (9-12)
✅worksheet ( 9-12)
✅students info እና ለሎችን ለማግኘት
👇👇👇👇👇👇👇
@Ethio_Students_only
For comment @EthioStudentsOnly_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


#NGAT_EXAM

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በቀጣይ ወር ይሰጣል።

የ2017 ትምህርት ዘመን አጋማሽ ዓመት የ NGAT ፈተና ከጥር 7-9/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለሚሰጠው ፈተና ይመዝገቡ፦
https://ngat.ethernet.edu.et/login

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖


He Did not qualify ____ the job
#Ethio_Students_only

❤️.to

⚡️.since

👏. With

👍.For


___is an essential but difficult skill in learning a new language

#Ethio_Students_only

👍.write

❤️.writes

😍.To write

😱.writing

✅ React to right Answer ✅


🎯ፊዚክስ  ፈተና ላይ ጥሩ ውጤት እየሰራችሁ ካልሆነ ወይም ደካማ ከሆናችሁ   እነዚህን 3 ነገሮች ከማወቅ ጀምሩ ። ሌሎቹ ቀስ ብለው ይደርሳሉ ።


I , Measurement and Units:

1. SI Units: Familiarity with the standard international (SI) system of units (meter, kilogram, second, etc.) is essential.


II . Motion and Forces:

1. Kinematics: This involves describing motion without considering the causes. Focus on:
  -Distance and Displacement: The difference between scalar and vector quantities.
  - Speed and Velocity: Understanding average and instantaneous speed/velocity.
  -Acceleration: How changes in velocity are described.
  - Graphs of Motion: Interpreting distance-time and velocity-time graphs. Relating slope to speed/acceleration.

2. Dynamics: This examines the causes of motion, focusing on forces.
  - Newton's Laws of Motion: Understanding the concepts of inertia, force, and acceleration. Relating force and mass to acceleration.
 -Forces: Identifying different types of forces (gravity, friction, normal force, tension). Drawing free-body diagrams.
  - Weight and Mass: The difference between these fundamental properties.


III. Energy:

1. Work and Energy:
  - Work: Defining work as the product of force and displacement in the direction of the force. Understanding when work is done and when it isn't.
  - Kinetic Energy: Energy of motion. The relationship between kinetic energy, mass, and velocity.
  - Potential Energy: Stored energy (gravitational potential energy is a good starting point).
  - Conservation of Energy: Energy cannot be created or destroyed, only transformed.

━━━━━━━━━━━━━━━━━


📑 የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ምን ላይ ናችሁ ?ምን እያሰባችሁ ነው ? ምንስ ይሰማችኋል?


#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ  ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ የጥሪ መልዕክት ስህተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

✨ Share with your  Friends
 


#HaramayaUniversity

በ2017 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥር 2-4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
የኅብረተሰብ ሳይንስ ተማሪዎች በቬተርነሪ ካምፓስ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ካምፓስ።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➫ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ እና ትራስ ልብስ

✨ Share with your  Friends
 


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ የጥሪ መልዕክት ስህተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡


#ትምህርት_ሚኒስቴር

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሜ እገዳ ተጣለባቸው፡፡

ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ከጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውንና በትግበራ ወቅት ክፍተት የታየበት "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡

በዚህም ማሻሻያው ተጠናቆ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስከሚላክ ድረስ በሁሉም ተቋማት የፕሮፌሰርነት ዕድገት አሰጣጥ ለጊዜው መታገዱን ሚኒስቴሩ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ለተቋማቱ በጻፈው ደብዳቤ ገልጾ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ "አንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክልከላውን በመጣስ፣ መመሪያውን ባልተከተለ፣ ግልጽነት በጎደለው፣ ወጥነት በሌለው እና ከትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ሪፎርሞች ጋር በሚጣረስ መልኩ የፕሮፌሰርነት ዕድገት መስጠት መቀጠላቸውን ለመረዳት ችለናል" ብሏል በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን ታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለተቋማቱ የተላከ ደብዳቤ።

ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረው የገለፀው ትምህርት ሚኒስቴር፤ የተቋማቱ ከፍተኛ አመራር አካላት እና የሥራ አመራር ቦርድ የተሻሻለው መመሪያ ተጠናቅቆ እስኪደርሳችሁ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡


#ጥቆማ

በ2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን መርሐግብር በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በማታ መርሐግብር በሁለተኛ ዲግሪ መማር የምትፈልጉ ተቋሙ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በማሟላት እስከ ታህሳስ 11/ 2017 ዓ.ም ድረስ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

ታህሳስ 17 እና 18/2017 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ከታህሳስ 23/2017 ዓ.ም እስከ ጥር 2/2017 ዓ.ም የመመዝገቢያ ጊዜ ነው የተባለ ሲሆን፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ቢሮ ቁ. 203 በአካል በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ማስገባት ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

✨ Share with your  Friends
 


❗️ጓደኛን ስትመርጥ . . . ❗️

📌አመለካከትህ የምትመርጠውን ጓደኛ ይወስናል፤ አብረህ የምትከርመው ጓደኛ ደግሞ በተራው አመለካከትህን የመወሰን ጉልበት ስላለው ወደ ሕይወትህ ዘልቆ እንዲገባ የምትፈቅድለትን ሰው በጥንቃቄ ምረጥ፡፡

📌“ጓደኝነት እንደ ሊፍት (Lift / Elevator) ነው፡፡ ወይ ወደላይ ያወጣሃል ወይም ደግሞ ወደታች ያወርድሃል” የሚል አባባል አለ፡፡ ሌላ ረዘም ላለ ጊዜ የከረመ አባባል፣ “በአጠገብህ የሚገኙ የአምስቱ ቅርብ ጓደኞችህ ጭማቂ ነህ” ይላል፡፡ እነዚህ አባባሎች ልቦናን የሚያነቃ እውነት ይዘዋል፡፡ የቅርብ ጓደኞችህን የያዝክበት የራስህ የሆነ ምክንያት ቢኖርህም፣ ለውጥ ለማምጣት በምትፈልግበት ጊዜ በዙሪያህ የሚገኙት ሰዎች ምን አይነት ሰዎች አንደሆኑ ማሰብ መጀመርህ አይቀርም፡፡

📌ከዚህ በታች ጓደኛን ስትመርጥ ሊኖርህ ስለሚገባ የምርጫ መመዘኛ የሚያስተምሩ ነጥቦችን ታገኛለህ፡፡

1. “ወደ ላይ” ምረጥ፡- የማደግና የመሻሻል ፍላጎቱ ካለህ የምትይዛቸው ጓደኞች ከአንተ ከፍ ያሉ እንዲሆኑ ትመከራለህ፡፡ ከፍ ያሉ ሰዎች ከፍ ያደርጉሃል፡፡ የበሰሉ ሰዎች ብስለትን ያስተዋውቁሃል፡፡ ይህንኑ ተመሳሳይ መርህ በመከተል የአንተን ላቅ ያለ ደረጃ ፍለጋ አንተን የሚቀርቡህ ሰዎች የመኖራቸው ሁኔታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ አንተ ግን ወደ ላይ መመልከትህን መዘንጋት የለብህም፡፡ 

2. ተመሳሳይ መርህ ያለውን ምረጥ፡- በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበት ሳንክድ፣ አመለካከትንና መርህን አስመልክቶ ግን ተመሳሳይነት ያላቸውን ሰዎች መቅረብ ስኬታማ ያደርግሃል፡፡ መርህን አስመልክቶ ልዩነታችሁ ከጎላ ሰዎች ጋር ጓደኝነት መያዝ፣ ወደፊት ከመራመድ ይልቅ ልዩነትን በማስታረቅ ዙሪያ የሚሽከረከር ግንኙነት ውስጥ እንድትቀር ያደርግሃል፡፡

3. ተመሳሳይ ግብ ያለውን ምረጥ፡- የዚህ ምርጫ ጥቅሙ የመደጋገፍና የመበረታታት ጉዳይ ነው፡፡ ለምሳሌ፣ አንተ ያለህ ግብ ሕብረተሰብህን የማገልገል ከሆነና የቀረብከው ጓደኛ ዋና ግቡ በገንዘብ የመበልጸግ ብቻ ከሆነ የጋራ የሆነን ሃሳብ በመወያየት የሞራልና የተግባር ድጋፍ መለዋወጥ ሊያስቸግራችሁ ይችላል፡፡

4. በስኬትህ ደስ የሚለውን ምረጥ፡- በተሳካልህ ቁጥር ከአንተ ጥቅምን እንደሚፈልግ የሚያሳይ፣ ስለስኬትህ ስትነግረው ብዙም ሃሳብ የማይሰጥ፣ ስኬትህን አስምልክቶ ከአንተ ጀርባ ለሌሎች የሚያወራና የመሳሰሉት ባህሪይ የሚያንጸባርቅን ሰው ጓደኛ ከማድረግህ በፊት ደግመህ ልታስብበት ይገባል፡፡

5. በውድቀትና በችግር የማይለይህን ምረጥ፡- ሁሉም ነገር በተሟላልህ ወቅት አብሮህ ሆኖ፣ ሁኔታዎች እንደ ቀድሞው አልሆን ሲሉህና ነገሮች ሲፈራርሱብህ ከአንተ ዘወር የሚል ባህሪይ ያለበት ሰው አይበጅህም፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ከአንተ ከሚያገኙት ጥቅም አንጻር ብቻ የሚቀርቡህ ናቸውና ስሜትህን ጠብቅ፡፡

6. እውነቱን የሚነግርህን ምረጥ፡- እውነቱን የማይነግርህ ሰው ከምታይበት ባህሪ አንዱ አንተ ጋር ሲሆን አንተን ደስ የሚልህን ብቻ እየመረጠ የመንገር ሁኔታ ነው፡፡ እውነተኛ ወዳጅ ግን እየወደደህና እያከበረህ፣ ቢያምህም እውነቱን ይነግርሃል፡፡ ይህ አይነቱ ሰው ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም፡፡

7. ማንነትህን የሚቀበልን ምረጥ፡-- ስህተትህን ሳይደብቅ እውነቱን እየነገረህ፣ ነገር ግን ማንነትህን ከነስህተትህና ከነጉድለትህ የሚቀበልን ሰው ማግኘት ታላቅ እድል ነው፡፡ እንዲህ አይነቱን ሰው ካገኘህ ለጓደኝነት አትለፈው፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው ባወቀህ መጠን አይንቅህም፤ እንዲያውም በወዳጅነቱ እየተመቻቸ ይሄዳል፡፡ በተጨማሪ፣ እውነተኛ ወዳጅ ዘርህን፣ መልክና ቁመናህን፣ እንዲሁም ሁለንተናህን የሚቀበል ሰው መሆኑን አትዘንጋ፡፡

8. መስመርህን የሚያከብርን ምረጥ፡- ጨዋ ጓደኛ መሆንና ማድረግ የማትፈልገውን ያከብራል፤ የግል ሕይወትህን አስመልክቶ የፈቀድክለት ድረስ ነው የሚገባው፡፡ በአንተ ህይወት መብተኝነት አይሰማውም፡፡ የሚበጅህ ጓደኛ፣ ጓደኝነት ማለት በየቀኑ መገናኘት፣ አብሮ ውሎ አብሮ ማደር፣ አብሮ መላስና መቅመስ እንዳልሆነ በሚገባ ያውቃል፡፡ ሌላ ማሕበራዊና ግላዊ ህይወት እንዳለህም በማወቅ ለቀቅ ያደርግሃል፡፡ ልቡ ግን ሁል ጊዜ ከአንተ ጋር ነው፡፡

9. ድብቅ ያልሆነውን ምረጥ፡- ማን እንደሆነ፣ ምን እንደሚያደርግ፣ ከየት እንደሚመጣና ወደ የት እንደሚሄድ በቅጡ የማይታውቀውን ሰው ከመወዳጀት ቆጠብ ማለት ይበጅሃል፡፡ ጓደኛ ሊታይ፣ ሊደመጥ፣ ሊዳሰስ ይገባዋል፡፡ በተለያዩ የማሕበራዊ የመገናኛ መረቦች ላይ “በስም” እና “በፎቶ” ለተዋወከው ሰው ሁሉ ልቦናንና ስሜትን መክፈት ከመስመር ያወጣሃል፣ አልፎም የስሜት ቁስል መሆኑ አይቀርም፡፡

💫 Share with your  Friends💫
 
🙌Post በምናደርጋቸው React አድርጉ😊

@Elshio_Academy
@Ethio_students_Only


የጥናት  ዘዴ

✅የSQ3R ዘዴ ተማሪዎች ጠቃሚ እውነታዎችን እንዲለዩ እና በመማሪያ መጽሐፋቸው ውስጥ መረጃ እንዲይዙ የሚያግዝ የማንበብ ግንዛቤ ቴክኒክ ነው። SQ3R (ወይም SQRRR) የንባብ ግንዛቤ ሂደት አምስት ደረጃዎችን የሚያመለክት ምህጻረ ቃል ነው። ለበለጠ ቀልጣፋ እና ውጤታማ የጥናት ክፍለ ጊዜ እነዚህን ደረጃዎች ይሞክሩ

🅰️- Survey የዳሰሳ ጥናት

🔹ሙሉውን መጽሐፍ ከማንበብ ይልቅ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በመዝለል እና በማንኛውም አርእስት፣ ንዑስ ርዕሶች፣ ምስሎች ወይም ሌሎች እንደ ገበታዎች ያሉ ጎላ ያሉ ባህሪያት ላይ ማስታወሻ በመያዝ ይጀምሩ።

🅰️- Question: ጥያቄ

🔻በምዕራፉ ይዘት ዙሪያ ጥያቄዎችን ይቅረጹ፣ ለምሳሌ፣ ይህ ምዕራፍ ስለ ምንድን ነው? ስለዚህ ጉዳይ አስቀድሜ የማውቀው ነገር ምንድን ነው?

🅰️-Read; አንብብ

🔺ሙሉውን ምዕራፍ ማንበብ ጀምር እና ለቀረጻካቸው ጥያቄዎች መልስ ፈልግ።

🅰️-Recite

🔹አንድን ክፍል ካነበቡ በኋላ ያነበቡትን በራስዎ ቃላት ያጠቃልሉት። ዋና ዋና ነጥቦችን ለማስታወስ እና ለመለየት ይሞክሩ እና ከሁለተኛው ደረጃ ማንኛውንም ጥያቄዎች ይመልሱ።

🅰️-Review ግምገማ

🔻ምዕራፉን ከጨረሱ በኋላ ሙሉ በሙሉ ለመረዳት ጽሑፉን መከለስ አስፈላጊ ነው. በፈጠሯቸው ጥያቄዎች እራስዎን ይጠይቁ እና የሚፈልጉትን ማንኛውንም ክፍል እንደገና ያንብቡ።
⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨⌨
@Elshio_Academy
@Ethio_students_Only


Part of leaves that can be opened or closed to control gas exchange & water loss.
Poll
  •   Guard Cell
  •   Stomata
  •   Cellulose
  •   Cell wall
215 votes


1300 Math Formulas by Golden Art.pdf
2.2Mb
🏆 1300 Mathematics Formulas 😮‍💨

✅ከ9-12 ያሉ የMath formulaዎችን የምታገኙበት Best pdf ነው። ተጠቀሙት🥰

👍👍👍👍👍👍👍👍


#ተቋርጦ የነበረው መብራት ወደ ነበረበት እየተመለሰ ነው :: -


#BuleHoraUniversity

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ታህሳስ 7 እና 8/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- ስምንት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖


🇮🇪 Which country flag is it ?
#Ethio_Students_only

👍. Ecuador

❤️.Ireland

👏.India

🥰. Myanmar

✅ React to the right Answer ✅


remedial-hub.pdf
792.3Kb
⭐️Chemistry 2015 Remedial Question

🙌Post በምናደርጋቸው React አድርጉ😊

@Elshio_Academy
@Ethio_students_Only


I  will pay ____ advance.
#Ethio_Students_only

👍. in

👏.on

😘.at

❤️.for

✅ React to right Answer ✅

20 last posts shown.