“ ዛሬ ዩናይትድ ይሸነፋል የሚል ኳስ አያውቅም “
የሪያል ሶሴዳዱ ዋና አሰልጣኝ ኢማኖል አልጓሲል በዛሬው ጨዋታ የአሸናፊነት ግምቱን ለቡድናቸው የሚሰጡ ሰዎች " ኳስ የማያውቁ ናቸው " ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ ጥሩ ውጤት እያገኙ ባይሆንም “ ምርጥ አሰልጣኝ ያለው ምርጥ ቡድን ነው “ ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።
አክለውም “ የአሸናፊነት ግምቱን ለሪያል ሶሴዳድ የሚሰጡ ሰዎች ምንም የእግርኳስ እውቀት የሌላቸው እና ተጋጣሚያችንን የማያውቁ ናቸው " ብለዋል።
" ለእኔ ማንችስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን የማሸነፍ ግምት የምሰጠው ክለብ ነው " ኢማኖል አልጓሲል
https://t.me/Ethioallball