"ክብሬ ተነክቶ አልደራደርም" ኢራን
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የኢራኑ ሁለንተናዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሚኒ "ምዕራባውያን የኑክሌር ድርድርን ለተጽዕኖ ፈጣሪነታቸው ማረጋገጫ እየተጠቀሙበት ነው" ሲሉ ወቀሱ፡፡
አያቶላህ ይህን ሀሳብ የስጡት ዶናልድ ትራምፕ የኑክሌር ድርድርን በተመለከተ ስምምነት ላይ ካልተደረሰ ሀይል ልንጠቀም እንችላለን ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ዋሽንግተን ሀይል ልትጠቀም እንደምትችል ፍንጭ መስጠታቸው ኻሚኒን አባሳጭቷቸዋል፡፡
አንዳንድ ጫና መፍጠር የሚፈልጉ መንግስታት ድርድሩ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ ነገር ግን ዓላማቸው መፍትሄ ማምጣት አይደለም ብለዋል፡፡
"እነዚህ መሪዎች ዓላማቸው የሚፈልጉትን ሁሉ በአንድ አገር ላይ መጫን እና የተጽዕኖ ፈጣሪነታቸውን አድማስ ማስፋት ነው" የሚል አቋማቸውን አንጸባርቀዋል መሪው፡፡
አያቶላህ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት"ሶስት የአርውሮፓ አገራት ኢራን የ2015ቱን የኑክሌር ስምምነትን አላከበረችም" የሚል መግለጫ ማውጣታቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
" እናንተስ ግዴታችሁን ተወታችኋል ወይ ተብለውም መጠየቅ አለባቸው" በሚልም ሀሳባቸውን በጥያቄ መልክ አጠናክረዋል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በቀደመው የስልጣን ዘመናቸው የ2015ቱን የኑክሌር ስምምነት 2018 ላይ ጥለው መውጣታቸው አይዘነጋም፡፡
ሪፐብሊካኑ የኑክሌር ስምምነቱን (JCPOA) ሲያቋርጡ በኢራን ላይ ዳግም ማዕቀብ ጥለውም ነበር፡፡
ስምምነቱን አምስቱ ቋሚ የጸጥታው ምክር ቤት ዓባላት እና ጀርመን(ፒ5+1) በኦባማ የፕሬዚዳንትነት ዘመን መፈረማቸው ይታወሳል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የኑክሌር ድርድሮች ቢቀጥሉም በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል ባለው ፖለቲካዊ አለመግባባት ሳቢያ ነገሮች መልካቸውን እየለወጡ ይገኛል፡፡
ለዚህም ነው ኢራን ክብሬን እና ብሄራዊ ጥቅሜን የጠበቀ ውይይት እስካልተደረገ የኑክሌር ድርድር ብሎ ነገር የለም በሚል እየሞገተች የሚገኘው፡፡
ቴህራንን ያላማከለ የትኛውም ድርድር ረብ የለሽ ነው ብለዋል አያቶላህ አሊ ኻሚኒ
ዘገባው የአልጀዚራ እና የአር ቲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ
@Ethionews433 @Ethionews433