የከተማ መሬትን በድርድር በሊዝ ማስተላለፍ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው
የከተማ መሬትን ከጨረታ እና ከምደባ በተጨማሪ በድርድር በሊዝ ማስተላለፍ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።
አዲሱ የአዋጅ ረቂቅ፤ ከተሞች በምደባ ለማቅረብ ካዘጋጁት መሬት መጠን ውስጥ፤ ቢያንስ 20 በመቶውን ለቤት ግንባታ አገልግሎት መዋል እንዳለባቸው ግዴታ ይጥላል።
“የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ” እንደወጣ የተገለጸው ይህ አዋጅ፤ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 19፤ 2017 በሚካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እንዲቀርብ አጀንዳ ተይዞለታል።
በ2004 ዓ.ም የጸደቀውን “የከተማ ቦታን ስለመያዝ የወጣ አዋጅን” የሚተካው አዲሱ የህግ ረቂቅ፤ በስድስት ክፍሎች እና በ49 አንቀጾች የተከፋፈለ ነው።
በአዋጅ ረቂቁ ከተካተቱ አዳዲስ ጉዳዮች መካከል “መሬትን በድርድር በሊዝ ለማስተላለፍ” የሚፈቅደው ድንጋጌ ይገኝበታል።
አስራ ሶስት ዓመት ያስቆጠረው ነባሩ አዋጁ፤ የከተማ ቦታ በሊዝ እንዲያዝ የሚፈቀደው በጨረታ ወይም በምደባ ስልት ብቻ ነበር።
በአዲሱ አዋጅ የተካተተው “የድርድር” ስልት፤ “በጨረታ እና በምደባ አግባብ” ለተጠቃሚ ሊተላለፉ በማይችሉ የከተማ መሬቶች ላይ፤ አንድ አልሚ “ለተለዩ ሀገራዊ ፋይዳ ላላቸው አገልግሎቶች” መሬት በሊዝ ይዞ ማልማት የሚፈቀድበት ነው።
በፌደራል መንግስት ለሚተዳደሩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለከፍተኛ የትምህርት እና የጤና ተቋማት እንዲሁም ለምርምር ዘርፍ ፕሮጀክቶች የከተማ መሬት በድርድር ሊተላለፍ እንደሚችል በአዋጅ ረቂቁ ላይ ተዘርዝሯል።
🔵ለዝርዝሩ፦
https://ethiopiainsider.com/2024/14466/@EthiopiaInsiderNews