ሪፖርተር (Ethiopian Reporter)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Ethiopian Reporter (ሪፖርተር) በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሴንተር በሳምንት ሁለቴ እየታተመ የሚወጣ ጋዜጣ ነው፡፡ ጋዜጣው ለነጻ ፕሬስ፣ ለነጻ ሐሳብናና ለነጻ መንፈስ መስፈን ይተጋል፡፡ Facebook: https://www.facebook.com/EThReporter Twitter: @EthioReporter LinkedIn: linkedin.com/in/ሪፖርተር-ሪፖርተር-123415146

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


‹‹የምርጫ 97 ወቅትን በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ትልቅ ውድቀት ነው የማየው›› ዓለማየሁ አረዳ (ዶ/ር)፣ የቅንጅት አባል የነበረው የኢዴሊ የቀድሞ ሊቀመንበር

‹‹ምሁሩ›› የሚል ርዕስ በሰጡት አጠቃላይ የኢትዮጵያን ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታና የምሁራንን ሚና በተነተኑበት የ2014 ዓ.ም. መጽሐፋቸው፣ ብሔር የሚለው ሐሳብ የለም፣ በማኅበራዊ ምሕንድስና የተፈጠረ ሐሳብ እንጂ የሚጨበጥ ነገር አይደለም የሚል ሐሳብን የሚያስተጋቡ ምሁራን በዓለም ደረጃ መኖራቸውን ይጠቅሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ በማኅበራዊ ምሕንድስናም ሆነ በምናብ የተፈጠረ ምንም ይሁን ምንም ብሔር በሚባለው ጥላ መሰባሰብ በኢትዮጵያ በገሀድ የሚታይ እውነታ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ በዚሁ መጽሐፍ አያይዘው ባነሱት ሐሳብ ደግሞ የብሔር ፖለቲካና ብዝኃነት በሰፈነበት አገር የዴሞክራሲ ተቋማትን መቅረፅና ዴሞክራሲን መገንባት ፈተና መሆኑን የሚናገሩ ምሁራንን አስተያየት አጣቅሰው ያቀርባሉ፡፡ የዛሬው የቆይታ እንግዳ ዓለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) በዚሁ መጽሐፋቸው የዴሞክራሲንና የብሔር ጥያቄን አቻችሎና በአግባቡ አስተናግዶ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ማስተግበር ስለሚቻልበት ሁኔታ ሰ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140213/


በጅምላና ችርቻሮ ንግድ የሚሰማሩ 40 የውጭ ኩባንያዎች ፈቃድ መውሰዳቸው ተነገረ

በያሬድ ንጉሤ
በሚያዝያ 2016 ዓ.ም. የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ ንግድ እንዲሳተፉ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተፈቀደ በኋላ፣ 40 የውጭ ኩባንያዎች ፈቃድ መውሰዳቸውን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ለውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ ንግድ እንዲሳተፉ ፈቃድ ከተሰጠ በጣም አጭር ጊዜ እንደሆነ የገለጹት የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የንግድ ዘርፉ ፈቃድ የሚመራበትን አሠራርና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች የተመለከቱ ጉዳዮች ተጠናቀው ወደ ሥራ ከተገባ አምስት ወራት መቆጠራቸውን የገለጹት፣ ሦስተኛው ‹‹ኢንቨስት ኢትዮጵያ›› ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በመጪው ግንቦት ወር እንደሚከፈት ይፋ በተደረገበት ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ያፀደቀው መመርያ ቁጥር 1001/2016 ከፀደቀ በኋላ፣ ለረዥም ጊዜ ዝግ የነበረው የጅምላና ችርቻሮ የገቢና ወጪ ንግድ ዘ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140249/


ጂቡቲ የኢትዮጵያ ስቅታ

አምና በሚያዝያ ወር በጂቡቲ በዘነበ ከባድ ዝናብ የተነሳ ከወደብ ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅና ሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦችን ማስመጣት ባለመቻሉ፣ በኢትዮጵያ ያለው ገበያ ለቀናት ሲተራመስ መሰንበቱ ይታወሳል፡፡ ነዳጅ ማደዎች አካባቢ ከሚታየው የተሸከርካሪዎች ረዣዥም ሠልፍ ጀምሮ፣ በሸቀጣ ሸቀጦች ገበያም ውስጥ አንፃራዊ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ይህ በሆነ በዓመቱ ከሰሞኑ ደግሞ የነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈተረው ችግር ከጂቡቲ ወደብ እንቅስቃሴ መስተጓጎል ጋር በቀጥታ ሲያያዝ ነበር፡፡ ከሰሞኑ ለተፈጠረው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በተለይ ከረመዳን ፆም ጋር የተያያዘ ምክንያት የቀረበ ሲሆን፣ በፆም ወቅት የወደብ አገልግሎቱ ሠራተኞች በመደበኛ ሰዓት ስለማይሠሩ መስተጓጎሉ የተፈጠረው በዚህ የተነሳ ነው የሚል መላምት ሲሰማ ነበር፡፡
ከሰሞኑ ለ1.2 ሚሊዮን ቶን ናፍጣ፣ እንዲሁም ለ650 ሺሕ ቶን ቤንዚን ግዥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ያወጣው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት፣...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140228/


በነዳጅ የሚሠሩ ባለሁለትና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ተወሰነ

በነዳጅ የሚሠሩ ባለሁለትና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መወሰኑን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በተለምዶ ባጃጅ የሚባሉት ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችና ባለሁለት እግር ሞተር ብስክሌቶች ወደ አገር ውስጥ ማስገባት እንደማይቻል የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ በሪሁ ሐሰን ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትር ደኤታው ይህንን ያሉት ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. አሃድ ቢዝነስ ግሩፕ፣ በአገር ውስጥ የተመረቱ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ባለሁለትና ባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ማቅረቡን በወዳጅነት ፓርክ በተዘጋጀ ሥነ ሥርዓት ሲያስታውቅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለነዳጅ እስከ ስድስት ቢሊዮን ብር እንደምታወጣ የተናገሩት አቶ በሪሁ፣ ‹‹በታዳሽ ኃይል ላይ ያለንን ዕምቅ አቅም ተጠቅመን ከውጭ ከሚገባውን ደረጃውን ያልጠበቀ፣ ነዳጅ ላይ ጥገኛ ከመሆንና አዙሪት ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140240/


#ማስታወቂያ

በየቀኑ እንሸልምዎ!

በቴሌግራም ገፃችን ብቻ!

ባንካችን ከሚያዚያ 1 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በየቀኑ ከቀኑ 5፡30 ጀምሮ የጥያቄና መልስ ውድድር በቴሌግራም ገፃችን ላይ የሚያካሄድ ሲሆን፤ ቀድመው ለመለሱ አስር ተሳታፊዎች ልዩ የፋሲካ ሽልማት አዘጋጅቷል፡፡

በውድድሩ ላይ ተሳታፊ ለመሆን እና ለመሸለም በቅድሚያ የባንካችንን የቴሌግራም ገፅ ይቀላቀሉ፡፡

የቴሌግራም ገፃችን- https://t.me/HibretBanket

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!

📞 ለበለጠ መረጃ ወደ 995 ነፃ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ፡፡

🌐 ትክክለኛውን የማህበራዊ ገፆቻችንን እና ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ፡፡

Telegram | Facebook | Instagram | LinkedIn | X | YouTube | Website

#GetReady #QuizAlert #Fasika #Bank #HibretBank #TelegramQuiz


#ማስታወቂያ

Torban Hojii Gaarii Qabaadhaa!
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልዎ!

#Siinqee_Bank    #Baankii_Siinqee    #ሲንቄ_ባንክ
#EMPOWERED_TOGETHER


#ማስታወቂያ


#ማስታወቂያ

ጭማሪው በዓልዎን ያደምቃል!
*
ባንካችን መጭውን የትንሣዔ በዓል ምክንያት በማድረግ
ከሚያዝያ 2 እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
ከባህር ማዶ በኢትዮ ዳይሬክት (#EthioDirect)፣ ካሽ ጎ (#CashGo) እና ፋስት ፔይ (#FastPay) የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎች፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ለሚላክላቸው ደንበኞቹ
ከእለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በተጨማሪ በተላከው በእያንዳንዱ ዶላር ላይ

የ12 ብር ተጨማሪ ጉርሻ ያበረክታል!
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #eidmubarak #gift #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #EthioDirect #CashGo #mto #fastpay
****
- የ EthioDirect መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• IOS፡ https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491

- የ CashGo መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bankofabyssinia.cashgo&hl=en&gl=US
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/cashgo/id1559346306

- የ fastPAY መተግበሪያ ለማግኘት
•Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.fastpay.android
•IOS: https://apps.apple.com/us/app/fastpayet/id1666650448


ባለፈው በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተከሰተው የትራፊክ አደጋ 45 በመቶው አምራች የኅብረተሰብ ክፍል ላይ መሆኑ ተገለጸ

በ2016 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተከሰተው የትራፊክ አደጋ 45 በመቶው አምራች የኅብረተሰብ ክፍል ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባልሥልጣን ገለጸ፡፡
ባለሥልጣኑ ይኼን የገለጸው ሚያዝያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሌሎች አጋር ተቋም ጋር በጋራ በመተባበር በከተማ አቀፍ ደረጃ ለ9ኛ ጊዜ የፖሊስ መረጃን በመጠቀም ያዘጋጀውን ዓመታዊ የመንገድ ደኅንነት ሪፖርት ይፋ ባደረገው መግለጫ ነው፡፡   
የከተማዋን ወቅታዊ የመንገድ ደኅንነት በሰፊው ዳሷል በተባለው በዚህ ሪፖርት መሠረት፣ በመዲናይቱ በ2016 ዓ.ም. በጀት ዓመት 401 ሰዎች በመንገድ ትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን፣ ከ2015 ዓ.ም. አንፃር በሰባት ሰዎች መቀነሱ ተነግሯል። የከባድ አደጋ ጉዳት መጠን ሦስት በመቶ መቀነሱ ተገልጿል። 45 በመቶ የሞት አደጋ የተመዘገበው አምራች የኅበረተሰብ ክፍል በሆኑት ከ20 እስከ 39 ዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ላይ ነው ተብ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140231/


የመሬትና የአፓርታማ ቤቶች ዋጋ ያሽቆለቆለባትና የቤት ኪራይ ዋጋ የናረባት አዲስ አበባ

የመኖሪያ ቤቶችና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎች ዋጋ ወርዷል፡፡ በሕግ መሬት መሸጥ መለወጥ ክልክል ነው ቢባልም መሬት እየተሸጠ ነውና የዚህም ዋጋ እየቀነሰ ከመጣ ሰነባብቷል፡፡ ሰሞኑን የተደረገ የመሬት ሊዝ ጨረታ ዋጋም እንደ ቀድሞ የተጋነነ አለመሆኑም የሚያሳየው ነገር አለ፡፡ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሽያጭና ግዢን የተመለከቱ መረጃዎች ከዚህ ቀደም ይወጣላቸው ከነበረ ዋጋ ተንሸራቷል፡፡ የሪል ስቴት ኩባንያዎች በካሬ እያሰሉ የሚሸጡበት ዋጋ በእጅጉ መቀነሱንም ከአልሚዎች እየተለቀቁ ያሉ ማስታወቂያዎች ምስክር ናቸው፡፡ 
በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ትልቅ ንብረት የሚታዩት እነዚህ ቤትና መሰል ግንባታዎች በቀደመው ዋጋቸው ሊሸጡ አለመቻላቸው ብቻ ሳይሆን እነዚህን ንብረቶች ለመግዛት ገበያ የሚወጡ ሰዎች ቀንሰዋል፡፡ በውጭ ምንዛሪ ያውም የጥቁር ገበያን እያጣቀሱና እያሰሉ የሚሸጡ ሪል ስቴቶች ዛሬ ለሽያጭ አዘጋጅትናል ያሉትን የተገነባና ያልተገነባ መኖሪያ ቤት በአገር ው...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140222/


ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በገጠመው የውጭ ምንዛሪ ችግር የማምረት አቅሙ ወደ 17 በመቶ መውረዱን አስታወቀ

ከአራት ዓመታት በፊት ከብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከ(ሜቴክ) ወደ ኢትዮ ኢንጂነሪነግ ግሩፕ የተቀየረውና በታኅሳስ ወር 2017 ደግሞ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ሥር የሆነው የማሽነሪ ማምረቻና መገጣጠሚያው የመንግሥት የልማት ድርጅት፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘቱ አጠቃላይ የማምረት አቅሙ ወደ 17 በመቶ መውረዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
ባለፉት ሦስት ዓመታት ለማግኘት ካቀደው አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ 3.2 በመቶ  የሚሆነውን ብቻ በማግኘቱ፣ እሴት የመፍጠር አቅሙ ከአንድ በመቶ በታች መውረዱ የድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡ በ2017 በጀት ዓመት ስምንት ወራት የነበረው የማምረት አቅም 27 በመቶ መሆኑን፣ የአምስት ዓመት አማካይ ደግሞ 17 በመቶ ላይ መቆሙን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የስምንት ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140246/


በተለያዩ ሥፍራዎች የሚፈጸሙ ዕገታዎችና ግድያዎች መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ጥያቄ ቀረበ


የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዕገታ የሚስፋፋው በሚዲያው ምክንያት ነው ብሏል

በተለያዩ ሥፍራዎች እየተፈጸሙ ያሉ ዕገታዎችና ግድያዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ አሽከርካሪዎችና የታጋቾች ቤተሰቦች ጥያቄ አቀረቡ፡፡
መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ‹‹አሊዶሮ›› በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል ሲጓዝ በነበረ ‹‹ፈለገ ግዮን›› የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ፣ አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ታፍነው ከተወሰዱበት ዕገታ፣ አንድ ሚሊዮን ብር ከፍለው ስለተመለሱ አክስታቸው ለሪፖርተር የተናገሩ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የደጀን ከተማ ነዋሪ፣ ዕገታ ዜጎችን እያማረረ ነው ብለዋል። አስተያየት ሰጪው ታጣቂዎቹ አክስታቸው እንዲለቀቁ 1.5 ሚሊየን ብር ጠይቀው እንደነበር ተናግረዋል፡፡  
ዕገታው መፈጸሙን የሚገልጽ የድጋፈ ደብዳቤ ከደጀን ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት አጽፈው  ገንዘብ በማሰባሰብ አንድ ሚሊየን ብር...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140258/


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
#ማስታወቂያ

💫ለመላው የክርስትና ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳችሁ እያለ ቴምር ሪልስቴት ለበአል ልዩ ቅናሽ ይዘልዎ መቷል!!

📍ፒያሳ  ከምኒልክ አደባባይ ፊት ለፊት 3ኛውንና የመጨረሻውን የንግድ ሱቅ በመሸጥ ላይ እንገኛለን።
✅ 2B+G+5 የሆነ
✅ በ3.9ሚሊዮን ሙሉ ክፍያ
✅ በ1 አመት ተኩል የሚረከቡት
✅ በቂ የመኪና ማቆሚያ ያለው

🔔በተጨማሪም
📍  በአያት አደባባይ ግንባታው ከ80% በላይ የደረሰ ሳይት ጨምሮ
✅ በፒያሳ-ሊሴ እና
✅ በሱማሌ ተራ
አፓርትመንቶችን እስከ 35% በሚደርስ ቅናሽ ይዘንልዎት መተናል

💫 ዋና ዋና መለያዎች
✅ እየኖሩበት የሚከፍሉበት አማራጭ ያላቸው
✅ ከ10% ጀምሮ መክፈል መቻልዎ
✅ በተለያዬ ቦታ የሳይት አማራጭ መኖሩ
✅ በኢትዮጵያ ብር ያለ ምንም ተጨማሪ ክፍያ መዋዋል መቻልዎ
👌ከባለ 1- ባለ 3 መኝታ

ለተጨማሪ መረጃ
🤳 09-16-94-89-32/ 09-37-71-32-25


ለምሬት ምክንያት የሚሆኑ ድርጊቶች ይታሰብባቸው!

በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ በጉልህ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል አንደኛው፣ በየዘመናቱ የኖሩ ልሂቃን ለልዩነታቸው ዕውቅና ሰጥተው በሰከነ መንገድ ለመነጋገር አለመቻላቸው ነው፡፡ ጉልበተኛው ደካማውን ለማንበርከክ እንጂ ፍላጎቱን ለማዳመጥ በማይፈልግበት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞ ውስጥ፣ ከንግግርና ከድርድር ይልቅ በኃይል መፈታተሽ በመለመዱ ለሕዝብ ምሬት መንስዔ የሆኑ በርካታ ጥፋቶች ደርሰዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ ያለፉት ሃምሳ ዓመታት የፖለቲካ ጉዞም የሚያሳየው ይህንኑ ነው፡፡ ኤርትራ ከኢትዮጵያ የተለያየችበት የ30 ዓመት ጦርነት፣ በትግራይ ለ17 ዓመታት የተካሄደው ጦርነት፣ በባድመ ምክንያት ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት፣ ትግራይን ጨምሮ አማራና አፋር ክልሎችን የለበለበው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በሕዝብ ላይ ያደረሱት ሰቆቃ አይዘነጋም፡፡ ከጦርነት በመለስ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ባለመቻሉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የደረሰው ምሬት ተነግሮ የ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140237/


"የ97ቱን ምርጫ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ትልቅ ውድቀት ነው የማየው" አለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) ፣ አንጋፋ ፖለቲከኛ
ሙሉ ቪዲዮውን ለማየት ይህን ሊንክ ይጫኑ: https://youtu.be/98pZGz4J3m8


በአማራ ክልል የመምህራን ግድያና ሕፃናት እንዳይማሩ የሚደረገው ማስፈራራት እንዲቆም ለኮሚሽኑ አጀንዳ ቀረበ

በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ከመጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው አገራዊ የምክክር መድረክ፣ በመምህራን ላይ የሚፈጸም ግድያና ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዳይሄዱ የሚደረገው ማስፈራራት ሊቆም እንደሚገባ ተሳታፊ መምህራን ለኮሚሽኑ አጀንዳ እንዲሆን አቀረቡ፡፡
በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት፣ በመምህርነት የሚያገለግሉ የተናገሩት የምክክሩ ተሳታፊ መምህር ዓለምነህ ገዛኸኝ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ነፍጥ ያነገቡ ኃይሎች ከመማር ማስተማሩ ሒደት ላይ እጃቸውን ሊሰበስቡ ይገባል፡፡ ‹‹የአማራ ክልል ቀውስና ግጭት ውስጥ ከገባ ሁለት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህም ጊዜያት በርካታ ቁጥር ያላቸው መምህራን ተገድለዋል፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹በመንግሥትና በታጣቂዎች መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተደርሶና አለመግባባቶች በውይይት ተፈትተው የመማር ማስተማሩ ሒደት ጤናማ ሆኖ መቀጠል ይኖርበታል፤›› ያሉት መምህሩ፣ ይህንን...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140091/


ዘወትር እሁድ የሚጠብቁት የሪፖርተር ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ይዞ በገበያ ላይ ይገኛል
በድረገጻችን https://www.ethiopianreporter.com/ ላይም ያገኙታል።

----------||----------
የሪፖርተር ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2Iv9bZB
ትዊተር↠ https://bit.ly/35qeNwV
ቴሌግራም↠ http://bit.ly/37OFEnC
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3p0jUQY

የ ስራ ማስታወቂያዎች ↠ EthiopianReporterJobs.com


ስሙን ወደ ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማኅበር የቀየረው የቀድሞው ሠራዊት ማኅበር

የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍና ልማት ማኅበር በስሙ ምክንያት የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካት ባለመቻሉ ስሙን ‹‹የኢትዮጵያ ሠራዊት ማኅበር›› ብሎ መሰየሙን አስታውቋል፡፡
የቀድሞው ኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍና የልማት ማኅበር መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ባዘጋጀው መድረክ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ሃምሳ አለቃ ብርሃኑ አማረ እንደተናገሩት፣ ማኅበሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የቀድሞው ሠራዊት አባላትንና ቤተሰቦቻቸውን ጭምር አቅፎ በመላው አገሪቱ 302 ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን አቋቁሟል፡፡ የአባላቱን የጡረታና የሕክምና መብት ለማስከበር ጉዳዩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ለስድስት ዓመታት ያህል ያቀረበው ጥያቄ መልስ ያልተገኘበትን ምክንያት በመፈተሽ ማኅበሩን ወደ ተሻለ አደረጃጀት ማሳደግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ለዚህም ስኬታማነት በነባሩ ስም መጠራቱ ቀርቶ ብሔራዊ የኢትዮጵያ ሠራዊት ማኅበር ተብሎ እንዲጠራ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ 
የአየር ኃይል፣ የባህር ኃይል...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140143/


‹‹ሁሌም ኦሊምፒያን እሆናለሁ፣ የአትሌቶችና የአትሌት ተወካዮች ተሟጋችም እሆናለሁ››

አዲሷ የኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተመራጭ ፕሬዚዳንት ኪርስቲ ኮቨንትሪ፣ ባለፈው ሳምንት የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) በናሚቢያ ባዘጋጀው የአትሌቶች ስብሰባ ላይ የተናገሩት፡፡ በኢንተርናሽናል ኦሊምፒክ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴትና አፍሪካዊት ሆነው በቅርቡ በመጋቢት የተመረጡት የቀድሞ ውጤታማ አትሌት የነበሩት ዚምባቡዌያዊቷ ኮቨንትሪ፣ በንግግራቸው ‹‹እኔ ኩሩ አፍሪካዊ ኦሊምፒያን ነኝ። የአፍሪካ አትሌቶችን ጉዞ፣ ተግዳሮቶችና ድሎች ከራሴ ጉዞ በመነሳት ተረድቻለሁ፤›› ብለዋል፡፡ በስፖርት ሕይወታቸውም ይሁን በአፍሪካና በአይኦሲ የአትሌት ተወካይ ሆነው፣ ወይም በአገራቸውና በኦሊምፒክ እንቅስቃሴ በተለያዩ ኃላፊነታቸው ያሳኳቸው ተግባሮች በቡድን በመሥራት እንደሆነ ያመለከቱት የቀድሞ የዚምባቡዌ የስፖርት ሚኒስትር ኮቨንትሪ፣ በአዲሱ የሥራ ድርሻቸውም ተመሳሳይ የአንድነትና የቡድን ሥራ አካሄድ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆናቸውን አስምረውበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140140/


ለሦስት ቀናት የታገደው የኢትዮጵያ ፕሪየሚየር ሊግ የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ይቀጥላል ተባለ

ባለቤትነቱ የሱፐር ስፖርት ሆኖ ነገር ግን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አማካይነት በቀጥታ ሥርጭት ለኅብረተሰቡ ሲደርስ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታ እንዲቋረጥ የተደረገው በደጋፊዎች መካከል ተገቢ ባልሆኑ የመልዕክት ልውውጥ ምክንያት እንደሆነ የሊጉ አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ፡፡
የሊጉ አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የቀጥታ ሥርጭቱ በሚተላፍበት ጊዜ አስተያየት ለመቀበል በተዘጋጀው ሳጥን በተለይም የ23ኛ ሳምንት ጨዋታ በሚተላለፍበት ወቅት በደጋፊዎች ያልተገቡ የእርስ በርስ መልዕክት ልውውጦች ምክንያት፣ የፌስቡክ ኮሙዩኒቲ ስታንዳርድ የተቋሙን ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ለሦስት ቀናት ታግዶ እንዲቆይ አድርጓል፡፡
በዚህም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛው ሳምንት የመጀመሪያና የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች በሊጉ አክሲዮን ማኅበር ማኅበራዊ ትስስር ገጽ እንደማይተላ...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/140111/

20 last posts shown.