ዶዳይ የኤሌክትሮኒክ ሞተር አምራች እና አከፋፋይ ድርጅት ለመጀመሪያዎቹ 250 ደንበኞ የታርጋ ወጪን ሸፈነይህ እርምጃ የኤሌክትሮኒክ ሞተርባይክ ባለቤትነትን በኢትዮጵያ የበለጠ ተደራሽ በማድረግእና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ብሩህ የወደፊት መንገድንከፍቷል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል።
ዶዳይ ደንበኞቹ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ280 በላይአባላት ያሉት የኤሌትሪክ ሞተር ብስክሌት ባለቤቶች ማኅበርበማቋቋም ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባለቤቶች የሚሰጠውንየታርጋ ፍቃድ አሰጣጥ ሂደት ለማቀላጠፍ ፈር ቀዳጅ ጥረትአድርጓልም ሲል ገልፇል።
ማህበሩ በሚያደርገው ዘላቂ ትራንስፖርት ሽግግር፣የባለቤትነት ልምድን የበለጠ ለማሳደግ እና አባላቱ ተገቢውንየከተማ ትራፊክ ደንብ ተከትለው አገልግሎት እንዲያገኙም ሆነእንዲሰጡ ድጋፍ ያደርጋልም ብሏል።
የዶዳይ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዩማ ሳሳኪ"ከ750 በላይ ኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶችን ሽያጭ በመፈፀማችን በጣም ደስተኞች ነን። የደንበኞቻችንን የታርጋወጪ በመሸፈን እና ይህን ማህበር እንዲመሰረቱ በማድረግየባለቤትነት ሂደቱን ከማቅለል ባለፈ የኢትዮጵያን የኤሌክትሪክተንቀሳቃሽነት አብዮት እያራመድን ነው። አላማችን ዘላቂትራንስፖርት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ ነው" ብለዋል።
“ይህ እርምጃ በኢትዮጵያ ከተሞች የትራንስፖርት መልክዓ ምድርአቀማመጥን እና አካባቢን የማይጎዱ መፍትሄዎችን በማስፈንየዶዳይን ዋነኛ ተልእኮ ያሳያል። ኩባንያው ከጊዜ ወደ ጊዜእየጨመረ የመጣውን የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ፍላጎትለማሟላት አስተማማኝ የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች እናየመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ኢንቨስት በማድረግ ላይ ይገኛል።”ሲሉ ተናግረዋል።
Source: fidelpostnews@Ethiopianbusinessdaily