ETHIO SCIENCE AND ASTRONOMY


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Blogs


አላማችን በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ የታነፀ ትውልድ መፍጠር ነው።
ሐሳብ አስተያዬት ለመስጠት👇👇👇
@Ethiospace1_bot
@unverseand 👈ለcross


Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Blogs
Statistics
Posts filter


ይሄንን ያውቃሉ ?

ዝቅተኛ አይኪው (IQ) ያለው ሰው ጭፍን ጥላቻ አለበት። በIQ ፈተና ላይ ዝቅተኛ ነጥብ በሚያመጡ ግለሰቦች ላይ በተጠና ጥናት መሰረት ብሔራዊ ወይም ሃይማኖታዊ የሆነ ጭፍን ጥላቻ እንደለባቸው ይገልጻሉ ፣ ከፍ ያለ የIQ ውጤት ያላቸው ግን ለተለያዩ አመለካከቶች ክፍት እና ተቀባዮችም ናቸው።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


Forward from: ETHIO SCIENCE AND ASTRONOMY
ልታዮቸው የሚገቡ ቪድዮዎች👇👇

1. አስገራሚው እና አስደናቂው ክስተት ፕሌኑ ምን ነበር ያጋጠመው ? 👇👇👇

https://youtu.be/L0AyJqH7WfQ


2. ሰማይ የተ ይገኛል ? 👇👇👇

https://youtu.be/ZK0IKCSlCY0

3. የ ኒኩለር ቦንብ እና ሶስተኛው የአለም ጦርነት 👇👇👇👇

https://youtu.be/1C3seEFAQQ8

4. ከ ፕላኔት ማርስ ላይ የተወሰዱ አወዛጋቢ እና አስፈሪ ምስሎች 👇👇👇👇

https://youtu.be/gY7iXTsQATU

4. ሲሆል/ገሀነም የተገኘበት ድንቁ እና አስገራሚው የሳይንቲስቶች ግኝት 👇👇
https://youtu.be/IQp-wIFrJ28


የእንቅልፍ አተኛኘት አቅጣጫ ጥሩ እና መጥፎ ጎናቸው!

1. በጀርባቸው የሚተኙ!
✔ ጥቅሙ

በጀርባ መተኛት ትራስ አከርካሪን የመደገፍ ሥራውን በትክክል እንዲወጣ ይረዳዋል። በትክክለኛው አለም ሁሉም ሰው ትራስ ሳይጠቀም በጀርባው መተኛት ይፈልጋሉ፤ ይህም አቅጣጫ አንገታችን ነፃ አቅጣጫ ላይ እንዲሆን ይረዳዋል። ከመጠን በላይ/ ብዙ ትራስ መጠቀም የአተነፋፈስ ሥርዓትን አስቸጋሪ ያደርገዋል።

በጀርባ መተኛት ውበትን ከመጠበቅ አንፃር ይመከራል፤ ሌሊቱን ሙሉ ፊታችን ለንጽህ አየር እንዲጋለጥ በማድረግ ይረዳል። የተጠቀምነው የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲክስ በትራሱ እንዳይጠረግ ከማድረጉ በተጨማሪ የፊት መሸብሸብን ወይም መጨማደድን ይቀንሳል።

✔ ጉዳቱ

ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ እጦት በጀርባ ተንጋሎ ከመተኛት አቅጣጫ ጋር ይያያዛሉ። በነገራችን ላይ በጀርባ መተኛት ከእንቅልፍ እጦት ጋር በቅርበት የተገናኘ ነው ለዚህም ነው ዶክተሮች በጎን አቅጣጫ በኩል መተኛትን እንደመፍትሄ የሚመክሩት።

በጀርባችን በምንተኛበት ወቅት የመሬት ስበት ሃይል የምላሳችን ሥር ወደ አየር ቧንቧ አቅጣጫ እንዲታጠፍ ያስገድደዋል ይህም ሥርዓተ ትንፈሳን በማስተጓጎል ጎረቤትን እንቅልፍ የሚነሳ አስቀያሚ ማንኮራፋት እንዲፈጠር ያደርጋል።

ጥሩ እንቅልፍ የሚተኙ እና ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎችን በማነፃፀር የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፦ ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎች አብዛኛውን የመኝታ ጊዜ የሚያሳልፉት በጀርባቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል።

2. በጎናቸው የሚተኙ!

✔ ጥቅሙ

በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች በአንድ ላይ! ማህፀን ውስጥ እንዳለ ጽንስ እግራቸውን እጥፍጥፍ አድርገው የሚተኙ እና እግራቸውን ዘርግተው የሚተኙ ሰዎች፤ አብዛኛው ማህበረሰብ በጎን በኩል እንደሚተኙ ሪፓርት ተደርጓል።

በእርግዝና ወቅት በግራ ጎን በኩል እንዲተኙ ዶክተሮች ይመክራሉ፤ ምክንያቱም ወደ ልብ ያለውን የደም ፍሰት ስለሚጨምር ነው ይህም ለእናት እና ልጅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው። በእርግዝና ወቅት በጎን በኩል እንድትተኚ ይመከራል ምክንያቱም በጀርባ በኩል መተኛት የታችኛው ጀርባ ላይ ግፊት ይፈጥራል (በአብዛኛው ፌንት እንድታደርጊ አስተዋጽዎ ያድርጋል)። እንደሚታወቀው በእርግዝና ወቅት በሆድ በኩል መተኛት አይቻልም።

✔ ጉዳቱ

በተመሳሳይ ሁኔታ በግራ ጎን በኩል መተኛት ሆድ እና ሳንባ ላይ ጫና እንዲፈጠር ያደርጋል። ሁሉም በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች እንደሚያውቁት በዚህ አቅጣጫ በሚተኙበት ወቅት የእጅ መደንዘዝ ሊያጋጥም ይችላል።

ጭንቅላትን እጅ ላይ አስደግፎ መተኛት የተለመደ አቅጣጫ ነው። ነገር ግን በጡንቻ እና ነርቭ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያስከትላል። ጭንቅላትን (አጠቃላይ ሰውነትን) በአንድ እጅ ላይ ማሳረፍ የደም ፍሰትን ይከለክላል በተጨማሪም ነርቭን ወደታች ይጫናል።

3. በሆዳቸው የሚተኙ!

✔ ጥቅሙ

በሆድ በኩል መተኛት ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ ችግርን ያስቀራል። ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባለው ጎኑ በሌሊት ሠዓት ቦርጫችን ወደ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል።

✔ ጉዳቱ

በሆድ በኩል መተኛት በአብዛኛው እንደሚታወቀው በጣም አስቀያሚ የሚባል የአተኛኘት አቅጣጫ ነው። የአከርካሪ የተፈጥሮ መንጋደድን በማዛባት ቀጥ እንዲል ያደርገዋል ይህም የታችኛው ጀርባ ህመምን ያስከትላል።

ሌሊቱን ሙሉ ጭንቅላትን ወደ አንድ አቅጣጫ አድርጎ መተኛት የአንገት ህመምን ያስከትላል። ይህ የአተኛኘት አቅጣጫ ምርጫዎ ከሆነ ትራስ በመጠቀም ሰውነትዎ በአንድ አቅጣጫ መተኛትም ያለማምዱት።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


የአለማችን ውዱ ስልክ

ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ሙባይል የአለማችን እጅግ ውዱ ሞባይል ሲሆን እስካሁን በአለማችን ላይ 3 ሰዎች ብቻ ናቸው ያላቸው:: ሞባይሉ በሩሲያ የሚገኝ ሲሆን ዋጋው ደግሞ 1.6 ሚሊየን ዶላር ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


በዓለማችን ላይ ምርጥ የትምህርት ስርዐት ካላቸው ሀገራት መካከል ፊንላንድ ቀዳሚ ነች፡፡

ኢትዮጵያ ደግሞ 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ማለትም አስቀያሚ የትምህርት ስርአተ በመጠቀም፡፡

ፊንላንድ ውስጥ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት 9 ዓመት ብቻ ነው የሚማሩት፡፡ በእነዚህ 9 ዓመታት ውስጥ ፈተና የሚፈተኑት 1ጊዜ ብቻ ነው እሱም ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነው፡፡

የቤት ስራ የሚባል ነገር የለም ሁሉም ክፍል ውስጥ ነው የሚያልቀው፡፡ 1ኛ 2ኛ የሚባል የደረጃ አሰጣጥ የለም፡፡

ትምህርት ነጻ ነው፤ የሀብታም የደሃ ትምህርት ቤት ብሎ ነገር የለም ሁሉም ቦታ እኩል የትምህርት ስርዓት ነው ያለው፡፡

አንድ መምህር ከ4 ሰዓት በላይ አያስተምርም፡፡"

ከእዚህ ምንድነው የምንረዳው በሃገራችን ላይ የትምህርት ስርዓት በራሱ ጨቋኝ እንደሆነ ነው!

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


አንዲት ዝንብ ከቤት ለመውጣት ፈልጋ ዝግ ከሆነ መስኮት ጋር ደጋግማ ብትጋጭ ይሳካላታል እንዴ?

ተዓምር ተፈጥሮ መስኮቱን ሰንጥቃው ካሎጣች በስተቀር መውጣት አትችልም፤ ይሄኔ ትንሽ ዞር ዞር ብትል እኮ ክፍት በር ይኖራል እሷ ግን አሁንም እየደጋገመች ከመስኮቱ ጋር ትጋጫለች። ይህቺ ዝንብ ጠንክራ ብትሰራም ማሰብ ስላልቻለች ከቤት ውስጥ መውጣት አልቻለችም!

ወዳጄ ያንተም ችግር ጠንክሮ ከመስራት ሳይሆን ትክክለኛውንና የምትወደውን ስራ ካለማሰብህ ይሆናል እየለፋህ ምንም ጠብ ያላለወ እህቴ ጥረትሽን ባደንቅም ለትክክለኛውና ለምትወጂው ሙያ አስበሽ እየለፋሽ ካሎነ እንደ ዝንቧ ከመስኮቱ ጋር እየተጋጨሽ እንደሆነ አስቢ።

(ከዳዊት ድሪምስ 'ትልቅ ህልም አለኝ' መፅሀፍ የተወሰደ ሀሳብ)


ሰለ ዩፎዎች እና ኤልያኖች ያሉት መረጃዎች ለምን ይደበቃሉ ?

ዩፎዎች ወይም የተለዩ ፍጥሮች በኛ መሬት ላይ እንደሚኖሩ አንዳድ መረጃዎች ይጠቁማሉ ነገር ግን ከወሬ ባለፈ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ አካል ጥፍቷል

ይሁን እንጂ መረጃ ኑራቸው የደበቁም አልታጡም በአንድ ወቅት የአሜሪካ ፕረዝዳንት ለመሆን ተቃርበው የነበሩት የዲሞክራተስ እጩ ኤራሊ ክሊንተን "እኔን ከመረጣቹ ሰለዩፎች ያሉትን መረጃዎች አጋልጣለው እንዲውም ሚስጥራዊው ቦታ "Area 51 " ለሕዝብ ክፍት ይደረጋል " ማለታቸው አነጋጋሪ ሁኖ ነበር አሳዛኙ ነገረ ሴትዬዋ በ "alian" ዎቹ ተቀደሙ መሰለኝ ምርጫውን ሳያሸንፉ ቀሩ 😪

የሆነው ሁኖ የሴትዬዋ ንግግር ምንድነው አንድምታው በርግጥስ አሜሪካ መረጃው ኑሯት ደብቃው ይሆን? ወይስ እንዲው ለምርጫው ድምቀት ብላ ነው መልሱን ለናተ ተውኩት🤔

መረጃው ቢኖራቸው ለምን ይደብቁናል በሚለው ጥያቄ ዙሪያ ብዙ መላምቶች አሉ ሰለ አንዱ ዛሬ ልንገራቹ

አሁን በዚች ሰሀት የአለም መንግስታቶች የኛን አገረ ጨመሮ ይፎች ወይም የተለዩ ፉጡሮች መኖራቸውን አረጋግጠናል ቢሏቹ ምን ታረጋላቹ ወይም ምንድነው መልሳቹ ?

እጅጉን የሚረበሹ ብዙ ናቸው ይላል መላምቱ የነ አሜሪካ ወይም ሌሎች አገሮች የዩፎችን ወይም የኤልያኖችን መኖር የሚደብቁት ከዚህ አንፃር ነው በአሁኑ ዘመን ያሉ የሰው ልጆች የዩፎች ወይም የተለዩ ፍጡሮች መኖር የሚያስደነግጣቸው እና ሊሸከሙት የማይችሉት አይነት ዜና ነው ሰለዚህ እውነታውን በመደበቅ ውስን ሰዎች ብቻ እንዲያውቁት ይደረጋል።

የዩቲውም ቻናላችንን subscribe ወይም የለቀቅናቸውን ቪዲዮዎች ማየት ለምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ታገኙታላቹ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1


በአንድ ወቅት ፕላኔት የነበረቹ ፕሉቶ ፕላኔት አደለችም መባሉን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፍ እንደነበረ ያውቃሉ ?

በ 1930 በጎርጎርሲያን አቆጣጠረ የተገኘቹ ፕሉቶ በወቅቱ ዘጠነኛዋ ፕላኔት ተብላ ነበረ በ1990 ዎቹ በተደረገ ጥናት ደግሞ ከፕሉቶ በስተጀረባ እጅግ ግዙፉ የሆነ የአስትሮይድ ድንጋይ ክምችት መገኘት ችሏል።

በዚህ አስትሮይድ ከምችት ውስጥ ፕሉቶን የሚያክሉ እንዲውም የሚበልጡ ፕላኔተ ነገረ የአስትሮይድ ድንጋዮች ተገኝተው ነበረ።

ይሄንን ተከትሎ እንዚህን ሁሉ ድንጋዮች ፕላኔተ ብሎ መሰየም ያልተዋጠላቸው የ IAU አመራሮች አንድን ነገረ ፕላኔት የሚያስብሉ ሶስት ሕጎችን አውጥተዋል በዚህም የተነሳ ፕሉቶ ሶስተኛውን ሕግ ሳታሟላ ቀርታለቸ ይሄንን ተከትሎ ፑሉቶን ጨምሮ ሌሎች የአስትሮይድ ድንጋዮች ፕላኔት ሳይባሉ ቀርተዋል ።

ፕሉቶ ፕላኔት አደለችም ከተባለ ከ2006 ጀምሮ ውሳኔው ያልተዋጠላቸው ሰዎች አደባባይ በመውጣት ተቃውሞቻቸውን ሲያሰሙ ተስተውሎ ነበረ።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


ሰለ ጠፈር ሊያውቋቸው የሚገቡ አስደናቂ እውነታዎች

1. ጠፈረ ሙሉ ለሙሉ ፀጥ ያለ ነው።

2. በዚህ ግዙፍ ዩንቨርስ ውስጥ ምን ያክል ከዋክብቶች እና ፕላኔቶች እንዳሉ በግልፅ አይታወቅም።

3. የኒውትሮን ክዋክብቶች በራሳቸው ዙሪያ በሰከንድ 600 ጊዜ ይዞራሉ።

4. ጨረቃ ላይ የሚገኘው የሰው ልጆች የጫማ አሻራ ለ 100 ሚልዬን ዓመታት ያክል ምንም ሳይሆን ሊቀመጥ ይችላል።

5. የቬኑስ አንድ ቀን ከመሬት አንድ ዓመት ጋር እኩል ነው።

6. ሁለት ብረቶችን ጠፈር ላይ ሁነን ብናነካካቸው ተጣብቀው ይቀራሉ

7. ከኛ ምድር 10 ቢልዬን የብርሃን ዓመት የሚርቅ ቦታ ላይ ሳይንቲስቶች እጅግ ግዙፍ ውሃ ጠፈር ላይ ተንሳፎ አግኝተዋል።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


🤔ይህንን ያውቁ ኖሯል❓

👉ውሾች የሰውን ልጅ ትንፋሽን ፣ ቆዳ ወይም ላብ በማሽተት አንድ ሰው በካንሰር በሽታ መያዝ አለመያዙን ማወቅ የሚያስችል ተፈጥሮአዊ ችሎታ አላቸው፡፡

©አስገራሚ

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


በጊዜ መጓዝ ወይም ታይም ትራቭል ይኖር ይሆን ?

በምስሉ ላይ የምታዩት ሰው በ1940 በካናዳ ዘመናዊ የሚመስል ግራፊክስ ያለው ትሽርት ለብሶ እና የፀሐይ መነፀር አድርጎ ከህዝብ መሃል ካሜራ ይዞ ፎቶግራፍ ተነስቶ ነበር በዛን ጊዜ ዲጂታል ካሜራም ሆነ ዘመናዊ ግራፊክስ ትሽርት አልነበረም ይህ ሰው ማን ነው በጊዜ ተጓዥ(time traveler) ወይስ ሌላ ነገረ አለም እስከዛሬ ያልፈታችው እንቆቅልሽ ነው።

©ከአለም gallery

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


በአንድ ወቅት ሩሲያዊ ዋናተኛ አየው ያለቸው የኤልያኖች ምስል ይሄንን ይመስል ነበር

እንደ ፈረጆቹ አቆጣጠር በ1982 ነበረ ነገሩ የተከሰተው ሩሲያዊ ዋናተኛ 50m ጥልቀት ካለው አንድ ሀይቅ ውስጥ ጥናቶችን ለማጥናት ወደ ሀይቅ ኦክስጅን ይዞ ይዘልቃል በወቅቱ ግን ያላሰበው እጅግ አሰፈሪ ነገርን ይመለከታል

ነገሩ እንዲ ነው በወቅቱ ዋናተኛው በሐይቅ ውስጥ ያየው የተለዩ ፍጥሮችን ወይም በእንግልዘኛው "aliens" ብለን የምንጠራቸውን ፍጡሮች ነበር።

በወቅቱ በቶሎ ከሀይቅ ውስጥ የወጣው ዋናተኛ ሁኔታውን ለማስረዳት ሲሞከር የሰማው ሰው አልነበረም ይባስ ብሎ ጋዘጤኞች በጥያቄ ያጣድፉት ጀመር በወቅቱ ስሜታዊ የሆነው ዋናተኛ በስተመጨረሻ ይሄንን ብሏል "እኔ ኤልያኖች አሉ የሚባለውን አስተያየት አልቀበልም ነበር ዛሬ ግን እኔ ለራሴ ያንን ጥያቄ በተግባር አይቼ መልሼዋለው እናተ አመናቹውም አላመናቹም ግድ አይሰጠኝ " የሚል አጭር መልስ ሰቷል።

በተጨማሪ የሩሲያ የባህር ሰርጓጅ መረክብ አምስት የማይታወቁ ነገሮችን ወይም ዩፎችን በውቂያኖስ ውስጥ ማየት ችሏል ከመርከቡ ጋርም የመጋጨት ዕድል የነበራቸው ሲሆን ከሆነ ሰአት በዋላ ግን ከይታ ውጭ ሁነዋል።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13

2k 0 12 5 10

UFO👽 (ዩፎ) ወይም የማይታወቁ በራሪ ነገሮችን አይተው ያውቃሉ ?

ለመጀመሪያ ጊዜ ይፎችን አይቻለው በሚል ምስክርነት የተሰጠው በ1947 ነበር ከዛ በዋላ ግን ከ1000 በላይ ሰዎች ዩፎችን አይተናል በሚል ምስክርነት ሰተዋል።

ይሁን እንጂ ሳይንቲስቶች ሁሉኑም ምስክረነቶችን ውድቅ አድርገዋል ለምን ?

በዩቲውብ በስፍት ይመልከቱ👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1


ሳዑዲ አረቢያ ወደ 500 ሜትር የሚጠጋ ቁመት እና 120 ኪሎ ሜትር እርዝመት ያለው ሰማይ ጠቀስ ህንጻ በ1 ትሪሊዮን ዶላር ልትገነባ ነው ይህም ትልቅ ህንፃ 5 ሚሊዮን ህዝብን ይይዛል ተብሏል።

©ከአለም gallery

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


መኪናዎች አዘውትረው ከረቭ ላይ ይጋጫሉ አልያም ከቁጥጥር ውጭ ሁነው ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ይሄዳሉ ለምን?

ምንም ያክል አሪፍ የመኪና ነጂ ልትሆን ትችላለክ ይሄንን ካላወክ ግን አንድ ቀን ለአደጋ ተጋላጭ ትሆናለክ!!!

መንዳት ብቻ በቂ አደለም የአንተ ሹፌርነት በፊዚክስ እና በሳይንስ የታነፀ መሆነ አለበት ለምሳሌ ብዙዎቹ ሹፌሮች ከርቭ ላይ ሲዞሩ አዘውተረው የሚሸወዷት ነገረ አለች ሞት እና የንብረት ጉዳት እንዲከሰትም አድርጓል ሹፌር ከሆንክ ግን ከዚህ ፁሑፍ በዋላ የሆነ ነገረ ተረዳላለክ ብዬ አስባለው።

ሞተሪስት ሁንክ ከረቭ ስትዞር ልዩ የሆነ ስሜት ሊኖርው ይችላል በዛው ልክ ግን እራስክን ለአደጋ አጋልጠካል ሰለዚህ አንተም ተጠንቀቅ!!!

ማንኛውም በከረቭ ላይ የሚነቀሳቀሰ ነገር ከርቩን ጠብቆ እንዲዞር የሚያደርገው ሴንተርፔታል (centripetal) ሐይል (force) በመባል ይታወቃል ይሄም ሐይል አጠቃላይ ከመኪናው ክብደት እና እየሄዳቹበት ካለው ፍጥነት ጋር በቀጥታ ይገናኛል አስፍታቹ ስትዞሩ ደግሞ ይሄ ሐይል ይቀንሳል ይሄም በቀመር ሲፃፍ እንደሚከተለው ይሆናል።

F=MV*V/R

F = force
M = mass of the car
V = speed of the car
R = radius

ልብ በሉ የሆነን ከረቭ በምትዞሩበት ወቅት ይሄንን ሴንተርፒታል የተባለ ሐይል ትፈጥራላቹ ይሄም ሐይል የግድ በጎማቹ እና በመንገዱ መካከል ከሚፈጠረው ሰበቃ ወይም ፍርክሽን(friction) ጋር እኩል መሆነ አለበት ለምሳሌ ሲንተረፒታል ሐይሉ በጣም ትልቅ ይሆን እና የሰበቃ ሐይሉ የሚያንስ ወይም እኩል የማይሆን ከሆን መኪናው ወይም ሞተሩ ከቁጥጥር ውጭ በመሆን ከመንገዱ ይወጣ እና ትልቅ ጉዳትን ያስከትላል በተመሳሳይ ሰበቃው የሚበልጥ ከሆነ መኪናው የመውደቅ አደጋ ያጋጥመዋል።

ሰለዚህ መፍትሔው ምንድነው ?

1. የመኪና ጎማችን ልሙጥ መሆን የለበትም ምክንያቱም የሚፈለገውን የሰበቃ ሐይል መፍጠረ ይችላል በጣም እየፈጠንን ቢሆን እንኳን

2. ሲተርፒታል ሐይሉ እንዲያንስ ማድረግ ይሄንንም ማድረግ የሚቻለው ከረቭ በምንዞርበት ወቅት ፍጥነታችንን መቀንስ ወይም ከፍተኛ ክብደት ያለው እቃ አለመጫን ነው ምክንያቱም ሁለቱም ነገሮች ሲጨምሩ ሴንተረፒታል ሐይል በተመሳሳይ ይጨምራል ይሄም ሐይል የሚጨምር ከሆን በሰበቃ የምናገኘው ሐይልም የግድ ትልቅ መሆን አለበት አለዛ መኪናው ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል።

3. ከርቭ ስንዞር አስፍቶ መዞር ምክንያቱም አስፍተን የምንዞር ከሆነ ሴንተረፒታል ሐይሉን መቀነስ እንችላለን ይሄንን ሐይል የምንቀንስ ከሆን የሰበቃ ሐይሉ በጣም ትልቅ እንዲሆን አይጠበቅም ይሄም ማለት የመኪናቹ ጎሞ ልሙጥ እንኳን ቢሆን የሚፈለገውን የሰበቃ ሐይል ማምጣት ይችላል

4. በተጨማሪ ከረቭ የሆኑ አከባቢዎች ላይ መኪና ማቆም ወይም የተለየ እንቅሳቄሴ ማድርግ ለአደጋ ያጋልጣል።

በዩቱውብ አማራጭ ያግኙን👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13

በቴሌግራም አማራጭ ያግኙን 👇👇

https://t.me/Ethiotefer

በፌስቡክ አማራጭ ያግኙን 👇👇👇

https://www.facebook.com/108072828668584/posts/pfbid0Yt2hREhUkyBGaPGK3n83QmFKQ5FymHBg3nL7EapqLu12522cRAdxniHp5w9UAVLXl/?app=fbl


ኤልያኖች ሊሻፍዱ ይችላሉ በሚል የሰዎች የራቁት ምስል ወደ ጠፈር ሊላክ ነው።

ናሳ የሰዎችን ምስል ወደ ጠፈር ለመላክ የወሰነው እነዚህን ምስሎች ምናልባት ኤልያኖች ካዩት ሊሻፍዱ ይችላል በሚል ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የዩቲውብ ቻናላችንን ይጎብኙ👇👇👇👇👇👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=13


Forward from: ETHIO SCIENCE AND ASTRONOMY
ባለ ሶስት ፀሐዩ(ኮከብ) ፕላኔት
ወይም በሳንቲፊክ ስሙ "HD 188753" ይባላል

ይሄ ፕላኔት ሶስት ፀሐዮች ያሉት ሲሆን ሁለቱ አጠገብ ለአጠገ የሉት ፀሐዮች በአንድ በኩል ሲገኙ ሌላኝው ኮከብ ደግሞ በተቃራኒ በኩል ይገኛል ይሄ ፕላኔት ጨለማ የሚባል ነገረ አያቅም ወይም የኛ ፕላኔት ቢሆን 24 ሰሀተ ቀን ነበረ ምሽት የሚባል ነገረ አናቅም አስገራሚው ነገረ ደግሞ በዚህ ምድር ላይ ብንኖር ሁለተ ጥላ ይኖረን ነበረ ይሄም የሚሆነው በሁለቱ ኮከቦች ምክንያት ነው መሬት የኛን ፀሐይ ዙራ ለመጨረስ 365 ቀን ሲፈጅባት ይሄ ፕላኔት ግን የኛን ፀሐይ የሚያክለውን ኮከብን ዙሮ ለመጨረስ 3.36 ቀን ብቻ ነው የሚፈጅበት ይሄም የሚሆነው ለኮከቡ እጅግ የተቃረበ ሰለሆነ ነው

ፕላኔቱ ሁለተ የፊዚክስ ሕጓችን የሻረ ወይም የሚቃረን ነው የመጀመሪያው ትላልቅ ፕላኔቶች ከሚዞሩት ኮከብ እጅግ ይርቃሉ ልክ እንደ ጁፒተር እና ሳተርን የሚል ሲሆን ፕላኔቱ ግን ከሶስቱ አንዱ ከሆነው አና ትልቅ ከሆነው ፀሐይ 8 ሚልዬን ኪሎ ሜትር ብቻ ነው የሚርቀው ፕላኔቱ ግን እጅግ ትልቅ ነው ልክ እንደ ጁፒተረ ለምን እንዲ ተጠጋ የሚለውን መልስ መስጠተ የሚችል እሳቤ የለም በዚህም ቅርበተ የተነሳ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሙቀተ አለው ፕላኔቱ በቅፅል ስሙ "hot Jupiter" ይባላል ወይም የገሀነቡ ምድር ልንለው እንችላለነ።

ሁለተኛው ይሄ ፕላኔት የተቃረነው እሳቤ ደግሞ ፕላኔቶች ኮከቦችን እንደሚዞሩ ነበረ የሚታወቀው ነገረ ግን የዚህ ፕላኔት ኦርቢት ምን አይነተ እንደሆነ አይታወቅም ወይም ግልፅ አደለም ወይም ከዚህ በፊት ከሚታወቀው በተለየ መንገድ ነው ይሄ ፕላኔት የተገኘው በ2005 ሲሆን ይሄንን ፕላኔት ሳይንቲስቶች ደግመው ለማየት በ2007 የሞከሩ ሲሆን ፕላኔቱ ግን ጥፍቷል ወይም ይገኛል በተባለበት ቦታ አልተገኘም ይሄም የሆነው አውን ላይ ሌሎች ፕላኔቶችን ለማግኘተ የምንጠቀመው ቴክኖሎጂ ለዚህ ፕላኔት አይሰራም ወይም የተወሳሰበ ኦርቢት ስላለው በኮከቦቹ ዙሪያ የተ እንዳለ በርግጠኝነተ ማወቅ አይቻልም።

ይሄ ፕላኔት ከኛ ምድር 149 የብረሃን አመት ይርቃል
በምስሉ ላይ የሚታዩት ሁለቱ ኮከቦች ልክ እንደፕላኔቱ መሀል ላይ ያለውን ትልቁን ኮከብ የሚዞሩ ሲሆን በሁለቱ ኮከቦች ማሀል ያለው እርቀተ ሳተርን እና ዩራኑስ የሚባሉት በኛ ሶላርሲስተም ውስጥ የሚገኙትን ፕላኔት በማከላቸው ያለውን እርቀት ያክላል ሁለቱ ኮከቦች በክብደት ትልቁን ኮከብ ወይም መሀል ላይ ያለውን ፀሐይ በክብደት ይበልጣሉ።

ከምንትዬዎቹ ፀሐዮች ወይም ሁለቱ አጠገብ ለአጠገብ ያሉት ፀሐዮች ከትልቁ ፀሐይ የሚርቁት 18 እጥፍ ከፀሐይ እስከ መሬት ያለውን እርቀተ ነው ወይም ከፀሐይ እስከ ጁፒተረ , ዩራኑስ እስከሚባሉት ፕላኔቶች ያለውን እርቀት ይሸፍናል።

በነገራችን ላይ ይሄ ፕላኔት ብቻ አደለም ከአንድ በላይ ኮከብ ያለው በዙ የተገኙ አሉ በዚህ ጉዳይ በሌላ ቀን እንመለስበታለን።

share share🙏🙏🙏🙏👇👇

@ethiotefer @ethiotefer
@ethiotefer
@ethiotefer @ethiotefer


የአለም ፍፃሜ በሶስቱ በአንዱ ሊከሰት እንደሚችል ይገመታለ

1. በኒኩለር ቦንብ የታጀቡ ጦርነቶች
2. የአስትሮይድ ጥቃት
3. ሁሉም ሕይወት ያላቸው ፍጡሮች ከምድረገፅ የሚጠፉበት አይቀሬው ድርቅ

የአለም ፍፃሜ መቼ እና እንዴት ይከሰታል ? በስፍት በዩቲውብ ይመልከቱ👇👇👇👇👇👇

https://youtu.be/KBMo2vv7ftM


ከሰው ልጆች የተላከውን መልክት ኤልያኖቹ ያገኙት ይሆን ?

ሳይንቲስቶች እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠረ በ 2008 ለኤልያኖች መልክት ላኩ መልክቱ ደግሞ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠረ በ2029 ይደርሳቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ነገሩ እንዲ ነው ሳይንቲስቶች ከ15 ዓመታት በፊት ያገኙት አንድ ፕላኔት ሕይወት ላላቸው ፍጡሮች አመቺ ሁኖ አገኙት አስገራሚው ነገረ ደግሞ ፕላኔቱ ከኛ አለም 20 የብርሃን ዓመት እርቆ ይገኛል ወደዚህ ፕላኔት በብርሃን ፍጥነት እንኳን ብንጓዝ እዚህ ዓለም ላይ ለመድረስ 20 ዓመት ይፈጅብናል እንደማለት ነው።

በአካል ወደዚህ ፕላኔት መሄዱ አዋጪ ሁኖ ያለገኙት ሳይንቲስች ዝንብለን ከምንቀመጥ የራዲዮ መልክት እንላክ በማለት መልክት ልከዋል የራዲዮ መልክቱ በብርሃን ፍጥነት የሚንቀሳቀስ በመሆኑ ምክንያት መልክቱ የኤልያኖቹ ዓለም ላይ የሚደርሰው ከ20 ዓመት በዋላ ነው መልክቱ የተላከው እንድ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2009 ሲሆን እስካሁን ድረስ 13 ዓመት ተጉዟል ከ7 ዓመታት በዋላ ደግሞ እዚህ አለም ላይ ይደረሳል። በዚህ አለም ላይ የሰለጠኑ ፍጡሮች ኑረው ከሰው ልጆች የተላከላቸውን መልክት ይመለከቱት ይሆን ?የብዙዎች ጥያቄ ነው

በነገራችን ላይ በተመሳሳይ ኤልያኖቹ ምልክቱን አይተውት ለሰው ልጆች መልሰው መልክት ከላኩ መልክቱ እኛ ዓለም ላይ የሚደርሰው እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር በ2049 ይሆናል።

ልብ በሉ ይሄ መልክት የኤልያኖቹ ዓለም ላይ ለመድረስ ይሄ ሁሉ ዓመት የሚፈጅበት በሰከንድ 300,000km እየተጓዘ ነው ወይም በአንድ ሰከንድ ውስጥ የኛን ዓለም 10 ጊዜ መዞር በሚያስችለው ፍጥነት ነው።

top 10 አስደናቂ እና አስገራሚ ፕላኔቶች ተጨማሪ በዩቲውብ ይመልከቱ👇👇

https://youtu.be/pwzFlG4E4GU


UFO👽

ለመጀመሪያ ጊዜ ይፎችን አይቻለው በሚል ምስክርነት የተሰጠው በ1947 ነበር ከዛ በዋላ ግን ከ1000 በላይ ሰዎች ዩፎችን አይተናል በሚል ምስክርነት ሰተዋል።

ይሁን እንጂ ሳይንቲስቶች ሁሉኑም ምስክረነቶችን ውድቅ አድርገዋል ለምን ?

በዩቲውብ በስፍት ይመልከቱ👇👇

https://youtube.com/channel/UCgmzpzIOElQB2v1JZtkjKQg?sub_confirmation=1

20 last posts shown.