#ፈጠራና_ለዉጥ_በኢትዮጵያ_ከጥንት_ጀምሮ_እስከ_1930ዎቹ
በኢትዮጵያ ከጥንት እስከዛሬ የተለያዩ የፈጠራ ሥራ ሙከራዎችና የሥልጣኔ አሻራዎች ታይተዋል። ታዋቂው ልበ-ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት እኝህን የለውጥና የሥልጣኔ ጮራዎች፣ በተለይም ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ 1930ዎቹ የታዩትን በታሪክ መዝገብ ሰንደው አኑረውልናል። እኛም ለናንተ ለተወደዳችሁ አንባቢዎቻችን በሚመች መልኩ እንዲህ ወደ አማርኛ ቋንቋ መልሰን አሰናድተናል። መልካም ንባብ!
የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ መልክዓ-ምድር እና በተራሮች የተከበበች አገር መሆኗ አውሮፓዊያን አፍሪካን በተቀራመቱበት ዘመን (scramble for Africa) ነጻነቷን ጠብቃ ለረዥም ዘመናት እንድትኖር ረድቷታል። የዚህች አገር በቅኝ ያለመገዛት ታሪክ እንቆቅልሽ የሆነበት Daniel Thwaite የተባለ ጸሀፊ The Seething African Pot: A Study of Black Nationalism, 1882-1935 በተሰኘ መጽሀፉ ስለኢትዮጵያ ክብር እንዲህ ይላል፤
Ethiopia’s prestige in Africa consequent upon her triumphant success in repelling invasion, and in having remained unconquered throughout the centuries, is practically unfathomable. To the Africans in general, not only to those who invoked her as a liberator, she stands as a granite monument, a living exponent and testimony of the innate puissance of the black race, the shrine enclosing the last sacred spark of African political freedom, the impregnable rock of black resistance against white invasion, a living symbol, an incarnation of African independence.”
ይች የአፍሪካ ትንሳኤ ተምሳሌት ፣ የጥቁር ትግል አይበገሬነት ህያው ማሳያ ሲል ይህ ደራሲ የገለጻት አገራችን ኢትዮጵያ በብዙ መልኩ የሄደችበት የታሪክ መንገድ ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የተለየ ነው። ይህም መሆኑ አገሪቱ በታሪኳ ያለፈችበት የፈጠራና ለውጥ (innovation and change) ሂደት የራሱ የሆነ አሉታዊም አውንታዊም ገጽታ እንዲኖረው አድርጎታል።
#ጥንታዊ_አክሱም
ይህ ዘመን በኢትዮጵያ የፈጠራና ለውጥ ታሪክ ውስጥ ወርቃማው ዘመን ነበር ሊባል ይችላል። በስነ-ህንጻው ዘርፍ የአክሱም ሀውልት በዘመኑ ኢትዮጵያዊያን የነበሩበትን የስነ-ህንጻ ደረጃ ሲያመላክት፣ በዘመኑ የነበረው የጽሁፍና የቋንቋ እድገት፣ በገንዘብ የመገበያየት ሥልጣኔ፣ ወዘተ የዘመኑን የእድገት ደረጃ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያ ለውጭው ዓለም እውቀትና ጥበብ በሯን የዘጋች አልነበረችም። ለዚህ እንደማሳያ በክብረ ነገሥት ላይ የሰፈረውን የንግሥት ሳባንና የንጉሥ ሰለሞንን ታሪክ ማንሳት ይቻላል። በዚህ ታሪክ ውስጥ ንግሥተ ሳባ ስለ ሰለሞን ጥበብ ሰምታ ለጥበብ ካላት ታላቅ ፍላጎት የተነሳ እየሩሳሌም ድረስ ተጉዛ ከንጉሥ ሰለሞን መገናኘቷን እናያለን። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ዞስካለስ ዓይነቱ የአክሱም ነገሥታት የግሪክን ስነ-ጽሁፍ ጠንቅቀው ያውቁ እንደነበር በታሪክ ድርሳናት ተጽፎ እናገኛለን። ከዚህም በተጨማሪ የግሪክ ፊደላት በአክሱማዊያን ሳንቲሞች ላይ ታትመው ይታዩ ነበር። በአክሱማዊያን ኪነ-ህንጻ ላይም የግሪክ አማልክት የሆኑት ዜዉስ፣አሬስ እና ፖሴይዶን ተቀርጸው ይታያሉ።
በሀይማኖቱ ረገድ በአክሱም ዘመነ መንግሥት የታዩትን ለውጦች ስንመለከት፣ የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያዊያን በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በንጉሥ ኢዛና ዘመነ መንግሥት ክርስትናን መቀበላቸውን በኋላም ከአረቡ አለም ለተሰደዱ መስሊሞች አምባ መጠጊያ መሆናቸውን ታሪክ ይነግረናል። በዚህ ጊዜ የአክሱም ንጉሥ የነበረው ንጉሥ አርማህ፣ እሱን ተማምነው የመጡትን የነብዪ መሐመድ ተከታዮች ከሳሾቻቸው አሳልፎ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁት…..” የወርቅ ተራራ ብትሰጡኝ እንኳን እንኚህን ሰዎች አሳልፌ አልሰጣችሁም”። ነበር ያላቸው።
ንጉሥ አርማህ …..”የወርቅ ተራራ ብትሰጡኝ እንኳን እንኚህን ሰዎች አሳልፌ አልሰጣችሁም”።
#የአክሱማዊያን_የንግድ_ግንኙነት
የአክሱም ዘመን ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከነበሩ አገራት መካከል ግንባር ቀደም ነበረች። ለጊዜውም ቢሆን ደቡብ አረቢያን ተቆጣጥረው የነበሩት አክሱማዊያን በታላላቆቹ ኢምፓየሮች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነትን እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጥያቄዎችን ያስተናግዱ ነበር። በዚህም ምክንያት በንግዱ ዘርፍ ከግብጽ፣ኑቢያ፣አረቢያ፣ ፐርሺያና ህንድ ግንኙነት የነበራቸው አክሱማዊያን መርከቦቻቸው ቀይ ባህርን እና የህንድ ውቂያኖስን አቋርጠው ሩቅ ተጓዦች ነበሩ።
በቀጣይ ክፍል የመካከለኛውን ዘመን ኢትዮጵያ የፈጠራና የለውጥ ታሪክ እንቃኛለን።