#ፈጠራና_ለዉጥ_በኢትዮጵያ_ከጥንት_ጀምሮ_እስከ_1930ዎቹ
ክፍል 2
በመካከለኛው ዘመን በንጽጽር ኢትዮጵያ ለሌሎች ዓለማት ሥልጣኔ እና እውቀት በሯን መዝጋቷ የአገሪቱን የፈጠራና የለውጥ ጉዞ ተንፏቃቂ አድርጎት ነበር። በዘመኑ ምቹ የነበረው የዓየር ጠባይ የሚሰጠው ምርት ከበቂ በላይ በመሆኑ ጊዜው የደስታና የፈንጠዚያ ነበር ማለት ይቻላል። አንዳንዴ የዓየር ሁኔታው ሲዛባና ህዝቡ ለድርቅ ብሎም ለረሃብ ሲጋለጥ ሁኔታው ከፈጣሪ እንደተላከ ቁጣ ነበር የሚታየው። ይህም ችግሩ የፈጠራና የለውጥ አስተሳሰብ አብዮት እንዳይነሳ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል። ከዚህም በተጨማሪ እንደ ዘርዓያዕቆብ ዓይነት የኦርቶዶክስ ክርስትና ጥብቅ አማኝ ነገሥታት ከፈጠራና ለውጥ እንቅስቃሴ ይልቅ ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች ያደሉ ነበሩ።
በዘመኑ ከውጭ ዓለማት ጋር ግንኙነት ለማድረግ ከሞከሩት ነገሥታት መካከል አጼ ይስሐቅ ተጠቃሽ ነው። የአጼ ይስሐቅ የውጭ ግንኙነትም ቢሆን በዋነኝነት ትኩረቱን ያደረገው በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ነበር። ይህ ንጉሥ የቱርኪሽ ማምሉኮችን በመቅጠር ለወታደሮቹ ሥልጠና እንዲሰጡለት፣የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች እንዲሰሩለትና የግብር ስርዓቱን እንዲያደራጁለት አድርጎ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በ1428 ዓ.ም. በዛሬዋ ስፔን አከባቢ ለምትገኘው የአራጎን ንጉሥ አፎንሶ የእጅ ሥራ ጥበበኞችን(artisan) እንዲልክለት የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ ነበር።
አጼ ልብነ ድንግል ለፖርቱጋሉ ንጉሥ ማኑኤል ቀዳማዊ በጻፈው ደብዳቤ የወርቅና የብር እንዲሁም የነሃስ ማንጠር ችሎታ ያላቸውን እና በነዚህ ማዕድናት ቤተክርስቲያንን ማስዋብ የሚችሉ ባለሞያዎችን እንዲልክለት ጠይቋል። አክሎም እኝህን ባለሞያዎች ቢልክለት ተንከባክቦ እንደሚይዛቸው እና ወደ አገራቸው መመለስ በፈቀዱ ጊዜም ያለምንም ችግር መመለስ እንደሚችሉ በእግዜብሔር ስም ቃል ገብቶለታል።
-Send masters who can make figures of gold and silver, copper, iron, tin, and lead, and send me lead for the churches; and masters of gilding with gold leaf, and of making gold leaf; and this soon, and let them come to remain with me here and in my favor. And when they may wish to return at their desire, I will not detain them and this I swear by Jesus Christ, Son of the Living God.”
ከዚህም በተጨማሪ አጼ ልብነ ድንግል ለንጉሥ ማኑኤል ቀዳማዊ ልጅ Joao III ተመሳሳይ ደብዳቤ ጽፎ ነበር።
የኋላ ኋላ በአህመድ ግራኝ ወረራ ጊዜ በ1541 ዓ.ም Christovao da Gama የተመራ 400 ወታደሮችንና 130 ባሮችን ያቀፈ ቡድን ከፖርቱጋል መጥቶ በጦርነቱ ላይ ድጋፉን ሰጥቷል። ከጦርነቱም በኋላ አጼ ገላውዲዎስ እነኝህን የውጭ ዜጎች አገር ውስጥ ለማስቀረት ትልቅ ጥረት ማድረጉን ታሪክ ይነግረናል። በዚሁ ጊዜ አጼ ገላውዲዎስ የቀጠራቸው የአርመን፣የግብጽ እና የሶሪያ ዜጎች በቤተመንግሥት ግንባታ ሥራ ላይ ተሳትፈው ነበር።
ዘመነ ሰርጸ-ድንግል
ሌላው በመካከለኛው ዘመን ከነበሩ የኢትዮጵያ ነገሥታት መካከል የተለያዩ ባለሞያዎችን ከውጭ አገር ለማስመጣት ሙከራ ያደረገው አጼ ሰርጸ-ድንግል ነው። አጼ ሰርጸ-ድንግል በ1589 ዓ.ም. ለፖርቱጋሉ ንጉሥ ፍሊፔ ዳግማዊ በጻፈው ደብዳቤ ፣ የተለያዩ የጦር መሳሪያ ሥራ እውቀት ያላቸውን ባለሞያዎች እንዲልክለት ጠይቆ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ሰርጸ-ድንግል በጉዛራ ቤተመንግሥት እንዲገነቡለት Garneau እና Arnaud የተባሉ ፈረንሳዊያን ባለሞያዎችን ቀጥሮ እንደነበር ይነገራል። የሰርጸ-ድንግል ወንድም ዘ-ድንግልም እንዲሁ ለንጉሥ ፍሊፔ ሶስተኛ የብረት ሥራ ባለሞያዎችን እንዲልክለት በደብዳቤ መጠየቁን ታሪክ ያወሳል።
ምጽአተ ኢየሱሳዊያን (jesuits)
የ16ኛው እና የ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያና የአውሮፓዊያን ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረው የኢየሱሳዊያንን በ1557ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ ነው። የኢየሱሳዊያንን መምጣት ተከትሎ የአውሮፓን ድጋፍ እጅጉን ይሹ የነበሩት ዘ-ድንግል እና ሱስኒዮስ የሮማን ካቶሊክ እምነት ተቀበሉ። ነገር ግን ኢየሱሳዊያኑ ተስፋ እንዳደረጉት ሰፊው ህዝብ የሮም ካቶሊክ እምነትን ለመቀበል ፍቃደኛ አልነበረም። በዚህም የተነሳ ብዙ ደም አፋሳሽ አመጾች ተከስተው ነበር።
ከ1541-1633 ዓ.ም. በነበረው ዘመን ከፖርቱጋሎች ጥቂት እንቅስቃሴዎች በተቀር ኢትዮጵያ ከውጭ አገራት ጋር የነበራት ግንኙነት በአገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሁም በፈጠራና ለውጥ ላይ ያስከተለው ለውጥ እምብዛም ነው። በዘመኑ የነበሩ የአገሪቱ ነገሥታትም ከጦር መሳሪያ በቀር በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ላይ ትኩረት ሲያደርጉ አይታይም። በሌላም በኩል ከውጪ የመጡትን ባለሞያዎች እውቀት ወደ አገር ልጅ የሚያሸጋግር ተቋም አልነበረም። የሰውም ሞያውን የመልመድ ፍላጎት ነበር ለማለት የሚያስደፍር አልነበረም።
ይቀጥላል