እውን መረጃ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Music


📌#ቀዳሚ_ምርጫዎ ➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ ➠ወቅታዊ መረጃዎች ➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች የምታገኙበት ቻናል
📌ጥቆማ ለመስጠት እና Cross
👉 @Ewenmereja_bot
#እውነተኛ እና #ትኩስ #መረጃዎች
#እውንነት

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Music
Statistics
Posts filter


ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ ታሪፍ ጣሉ፤ ኢትዮጵያም 10 በመቶ ታሪፍ ተጥሎባታል

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አዲስ የታሪፍ እርምጃ ወሰዱ። ረቡዕ ዕለት በዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ፣ አሜሪካ ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ላይ አዲስ የታሪፍ መጠኖችን መጣላቸውን አስታውቀዋል።

ትራምፕ እንደገለጹት፣ ይህ እርምጃ አሜሪካን ቀዳሚ ለማድረግ እና የንግድ ጉድለትን ለመቀነስ ያለመ ነው። በአብዛኛዎቹ ሀገራት ላይ የተጣለው ታሪፍ ከ10% እስከ 49% የሚደርስ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም 10% ታሪፍ ተጥሎባታል።

አሜሪካ የንግድ ጉድለቷን ለመቀነስ እና የአሜሪካን ኢኮኖሚ ለመጠበቅ ይህን እርምጃ እንደወሰደች የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ከ20 በላይ ሀገራት ላይ የታሪፍ ጭማሪ የተደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያም ከነዚህ ሀገራት አንዷ መሆኗ ተዘግቧል ።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት  እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው‼️

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።

ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ  ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።

ላለፉት ዓመታት(እሳቸው  በኃላፊነት ከተሾሙ ጀምሮ)፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት በከፍተኛ ደረጃ ዝቅተኛ  እንዲሆን ካደረጉ መንስዔዎች መካከል፣ የመምህራን ብቃትና የተነሳሽነት ማነስ ተጠቃሽ መሆናቸው ጠቁመዋል።

ችግሩን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲቻል የተለያዩ ተግበራት እየተሰሩ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ "በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል"ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።

ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።

ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።

በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።

ወደ መምህርነት ሙያ የሚገቡ ሰዎችን ክፍተት ለማስተካከል ከተያዙ ዘርፈ ብዙ የማትጊያ ሥርዓቶች አንዱ፣ መምህራን በአገሪቱ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ የራሳቸው ድርሻ እንዲኖራቸውና የኑሮ ውድነቱን እንዲቋቋሙ ለማድረግ፣ "የመምህራን ባንክ" ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑን አንስተዋል።

ባንኩ "በአንድ ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባዋል ብለን እንጠብቃለን" ያሉት ሚኒስትሩ፣ በ2019 ዓ.ም ደግም በእርግጠኝነት ወደ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ አሰራር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

Via : ሪፖርተር

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


በአማራ ክልል ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ተናገሩ

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎችና የህክምና ባለሙያዎች ተናገሩ።

ራስን ለማጥፋት የአዕመሮ ህመምና ቅፅበታዊ አጋጣሚዎች ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጧል። በባሕር ዳር ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ 156 ከራስ ማጥፋት ጋር በተያያዘ ወደ ህክና የመጡ ሰዎች መኖራቸውን አንድ የህክምና ባለሙያ ለዶይቸቨለ ተናግረዋል።

በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ጓዴ ተዋበ ከአዲሱ ዓመት መግቢያ ጀምሮ ራስን ከማጥፋት ጋር በተያያዘ ጉዳተኞች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውን ገልጸውልናል። ከታካሚዎቹ መካክልም ብዙዎቹ ከተጎዱ በኋላ ወደ ተቋሙ በመድረሳቸው ሕይወታቸው ያለፈ መኖሩን አመልክተዋል።

በወራቤ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአዕምሮ ህክምና ስፔሽያሊስት ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው በበኩላቸው ራስን ለማጥፋት የሚያስችሉ መነሻ ምክንያቶች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ዋነኞቹ ድብርትና ቅፅበታዊ ሁኔታዎች የሚፈጥሩት ሁኔታ እንደሆኑ ተናግረዋል።

Via DW Amharic

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


ኢትዮጵያ ወደ ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመላክ የሙከራ ስርጭት መደረጉ ተነገረ

ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ወደ ታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል መላክ የሚያስችላትን ስምምነት መፈራረሟ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህንንም ሂደት ለማስጀመር የሙከራ ስርጭት መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

"የሙከራ ስርጭት ሂደቱ ምንም አይነት ችግር ሳይገጥመው ተከናውኗል" ያሉት የተቋሙ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን፤ "የሚቀረው ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግ ብቻ ይሆናል" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

እስካሁን ስምምነቱ ተግባራዊ መሆን ያልቻለውም ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመግዛት የኬንያን መሠረተ ልማት መጠቀም ስለሚኖርባት፤ ሀገራቱ ስምምነት ላይ እስከሚደርሱ እንደነበርም ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ኤሌክትሪክ ሽያጭ ከጀመረች ጊዜ ጀምሮ ወጥ በሆነ መንገድ ኤክስፖርት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የሚላከው የኤሌክትሪክ ሃይል በሰዓት እስከ 200 ሜጋ ዋት ድረስ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ "ይህም ስምምነት ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የመጀመሪያቹ ሦስት ዓመታትን ያጠቃልላል" ብለዋል።

ከዚያ በመቀጠል በሚኖሩበት ሦስት ዓመታት ደግሞ ወደ 400 ሜጋ ዋት በሰዓት ከፍ እንደሚል አመላክተዋል።

በኬኒያ በኩል በሚወጡ መረጃዎች መሠረት፤ አሁን ላይ 10 በመቶ የሚሆነው የኤሌክትሪክ ሃይል የሚያገኙት ከኢትዮጵያ በሚወስዱት መሆኑን አመላካች ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በ2028 የኤሌክትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅሟን ወደ 13 ሺሕ ሜጋ ዋት ለማሳደግ በእቅድ የያዘች ሲሆን፤ በዚህም 14 ሀገራትን በኤሌክትሪክ ሃይል የማስተሳሰር እቅድ ይዛ በትብብር እየሰራች መሆኑ መገለጹ ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት ለጅቡቲ፣ ኬንያና ሱዳን የኤሌክትሪክ ሃይል እያቀረበች የሚትገኘው ኢትዮጵያ፤ በቀጣይ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊ ላንድና ሱማሊያ ጋር  ትስስር ለመፍጠር ማቀዷን ሀገራቱም የኃይል ግዢ ፍላጎት ማሳየታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ አቶ ነሲቡን አዲስ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሾመ

ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ አቶ ነሲቡ ተመስገንን አዲስ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ከመጋቢት 23 ቀን 2017 ጀምሮ እንዲያገለግሉ መሾሙን አስታወቀ። 18 ዓመታትን ያስቆጠረ የሥራ ልምድ ያላቸው አቶ ነሲቡ፣ ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉን በዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል።

ነሲቡ በዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የድርጅቱን ሽያጭ እና የገበያ አቋም በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ቁልፍ ሚና መጫወታቸውን ኩባንያው ገልጿል ።

"ምርታማነትን ያማከለ እድገት፣ የሰው ኃይል ማብቃት እና የላቀ አፈጻጸም ቅድሚያ ትኩረቴ ናቸው" ያሉት አቶ ነሲቡ፣ "የዩኒሊቨርን እሴቶች እና ባህሪያት በመጠበቅ ተገቢውን የቁጥጥር እና የአስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ይህን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ" ብለዋል።

ከኩባንያዉ ለካፒታል በተላከዉ መግለጫ አቶ ነሲቡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተማሩ ሲሆን፣ በዩኒሊቨር የሚሰጠውን የአፍሪካ ሊደርሽፕ አክስሌረተር ፕሮግራምንም አጠናቀዋል።

መቀመጫው በእንግሊዝ ሀገር የሆነው የአለም አቀፉ ዩኒሊቨር በኢትዮጵያም ላለፉት ስምንት ዓመታት እንደ ላይፍቦይ፤ ኦሞ እና ክኖር የመሳሰሉ የግልና የጋራ ንጽህና መጠበቁያዎች እንዲሁም ምግብ ነክ ምርቶችን እያቀረበ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ አምራች ድርጅት መሆኑ ይህ ።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


ሩስያ ሆን ብላ የራሷን ግድብ አወደመች

ሩስያ በዩክሬይን ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የራሷን ግድብ ማውደሟ ተሰማ።

ሩስያ ግድቡን ያወደመችው የዩክሬይን ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ለማገድ ነው ተብሏል።

የጀርመን ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ሩስያ ግድቡን የደረመሰችው ሦስት ቶን ይመዝናል በተባለ የጦር አውሮፕላን ቦምብ ነው።

ግድቡ ከዩክሬይን ድንበር በጥቂት መቶ ኪሎ ሜትሮች በምትገኘው ፖፖቭካ በተባለች መንደር አቅራቢያ ነው።

ዩክሬይን በቤልጎሮድ ዞን የማጥቃት እርምጃዋን እያጠናከረች እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ።

የዩክሬይን ጦር ግን በጉዳዩ ላይ እስከ አሁን ያለው ነገር እንደሌለ ዜናው አመልክቷል።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


በቤተክርስቲያን ዉስጥ ለምዕመናን ላብ የተጠረገበት ሶፍት በሚያበሉ አካላት ላይ እርምጃ ተወስዷል ተባለ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል በስሩ አባል ለሆኑ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉጪ የሆኑ አጃሄዶች እና ልምምዶችን በሚመለከት ከድርጊቶቹ እንዲቆጠቡ መክሯል።

የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት ለካዉንስሉ የላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ፤ አባላት በቤተክርስቲያን ዉስጥ ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ከሆኑ ተግባራት እንዲቆጠቡ የሚያሳስብ ነዉ።

ለአብነትም ዘይት ፣ ዉሃ ፣ ጨርቃጨርቅ የሚሸጡ እንዲሁም ላባቸዉን የጠረጉበትን ሶፍት ለምዕመናን የሚሰጡ መኖራቸዉን አመላክቷል። ካዉንስሉ አባላት ቤተክርስቲያኖች ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ በጥብቅ አስጠንቅቋል መባሉንም ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የርኆቦት አብያተክርስቲያናት ህብረት ካዉንስሉ ያወጣዉን መመሪያ እንደምትተገብር አሳዉቃ መሰል ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምዶችን እንደምትጸየፍ ገልጻለች።

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከነብይ እዩ ጩፋ ጋር ዉጥረት ዉስጥ መግባታቸዉ የሚታወስ ሲሆን  ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምዶችን በሚተግብሩ አካላት ላይም እርምጃ እየወሰደ ነዉ።

ነብይ እዩ ጩፋ በጸጥታ አካላት ሀዋሳ ከተማ ላይ እጀባ የተደረገላቸዉ መሆኑ ፤ ካዉንስሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉጪ ነዉ ብሎ የነበረ ቢሆንም ነብይ እዩ ጩፋ ግን የካዉንስሉን መግለጫ አጣጥለዉ ነበር። በዚህም የተነሳ በነብዩ የሚመራዉ የክራይስት አርሚ ቸርች በካዉንስሉ እገዳ ተጥሎበታል።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


አሜሪካዊው ተዋናይ ቫል ኪልመር ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ባትማንን ጨምሮ በአይረሴ ፊልሞች ባሳየው የትወና አቅም የሚታወሰው አሜሪካዊው የፊልም ሠው ቫልኪልመር ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።

የ65 ዓመቱ አዛውንት ከቀደምት ስራዎቹ ‘ቶፕ ገን’ እና ‘ባትማን ፎሬቨር’ የተሰኙት ይጠቀሱለታል።

የተዋናዩ የሞት መንስኤ በሳምባ ምች እንደሆነ ሴት ልጁ የገለፀች ሲሆን ከ11ዓመታት በፊት 2014 በጉሮሮ ካንሰር ህመም ተጠቅቶ እንዳገገመ በተጨማሪነት ገልፃለች።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ቻይና የሚበሩ ታክሲዎችን ሥራ አስጀመረች

ታክሲው በሰዓት እስከ 130 ኪሎ ሜትር
ፍጥነት እና 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ይሄዳል።

ሁለት መንገደኞችን ያሳፍራል ።

ቪዲዮ: ማህበራዊ ሚዲያ

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


በአማራ ክልል ውጊያ የመቀጠል አሳሳቢነት

ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ በአማራ ክልል ከባድ ጦርነት መቀስቀሱ የተነገረ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ መቀጠሉ በሰፊው ይሰማል፡፡ የፋኖ ኃይሎች ‹‹ዘመቻ አንድነት›› ያሉትን ጥቃት በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ላይ መክፈታቸው እየተነገረ ሲሆን፣ መንግሥትም በአፀፋው በታጣቂዎቹ ላይ ዘመቻ መጀመሩ ይነገራል፡፡ በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የተለያዩ አካባቢዎች የጥይት ጩኸት መሰማቱ እንደቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ምንጮችም ያረጋግጣሉ፡፡

መከላከያ ሠራዊት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ይፋ ባደረገው መግለጫም፣ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ምግበይ ኃይለ በተባሉት በትግራይ ሠራዊት ጄኔራል ሥልጠናና ዕገዛ ጥቃት ከፍተውብናል ሲል መግለጹ፣ የአማራ ክልል ቀውስ ወደ ትግራይም ተሻገረ እንዴ የሚል ጥያቄን ያጫረ ነበር፡፡ በአማራ ክልል የተጠናከረውን ውጊያ በማቀነባበር የተወነጀሉት ብርጋዴር ጄኔራል ምግበይ ኃይለ ግን፣ በወቅቱ በሰጡት መግለጫ ከፕሪቶሪያ ውል ውጪ የሚደረግ እንቅስቃሴ በትግራይ በኩል የለም ብለዋል።

Via፡ ሪፖርተር

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


የEBS አዲስ ምእራፍ ፕሮግራም ታገደ ደብዳቤው ከላይ አያይዘነዋል።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


ቻይና በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላት ገለፀች

ቻይና ይሄን ፍላጎቷን የገለፀችው የቻይና-አፍሪካ ልማት ፈንድ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩ ዡሮይ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ጋር ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው።

በውይይቱ አምባሳደሩ የሀገራቱን ትብብር ማጠናከርና ኢንቨስትመንትን ማሳደግ እንደሚገባ መግለጻቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አአስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የሚገነባውን አዲስ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጨምሮ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና ኢትዮ-ቴሌኮምን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

ዩ ዡሮይ በበኩላቸው ውይይቱ የሀገራቱን የልማት ትብብር ለማሳደግና አዳዲስ የትብብር መስኮችን ለመፍጠር እንደሚያስችል አስረድተዋል፡፡

የቻይና ልማት ፈንድ በኢትዮጵያ አዲስ በሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት ላይ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


በ ትግራይ ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት የ120 አምቡላንሶች ድጋፍ ተደረገ

በትግራይ ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት 120 አምቡላንሶችን ጨምሮ የመድኃኒትና የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉን በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገለጸ።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ብርሀኑ መኮንን እንደገለፁት፤ በክልሉ ያለውን መሰረታዊ የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ለመፍታት እና የአምቡላንስ ተደራሽነትን ለማስፋት ማህበሩ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ድጋፍ ተደርጓል።

የ120 አምቡላንሶች ድጋፍ መደረጉ በተለይ ከወሊድ ጋር በተያያዘና በድንገተኛ አደጋ በእናቶችና ህጻናት ላይ የሚከሰት ሞትን ለመቀነስ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።

የክልሉን የጤና አገልግሎትና ስርዓት ለማሻሻልም ተጨማሪ ስራዎች እንደሚጠይቅ ገልጸው፤ በገጠር አካባቢ በሚኖረው ማህበረሰብ ዘንድ ያለውን የመድኃኒትና የአምቡላንስ አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።

በተመሳሳይ የዓይደር ስፔሻላይዝድ ሪፈራል እና የመቀሌ አጠቃላይ ሆስፒታሎች 18 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁስን በድጋፍ መልክ አግኝተዋል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የጤና ቢሮ ተወካይ አቶ ሚኪኤለ ሃጎስ፣ ለድጋፉ አመስግነው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እያደረጉት ያለውን መሰል ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


መገናኛ ብዙሀን የሚያጫውቷቸውን ሙዚቃዎች የሚመዘግብ ዌብሳይት ይፋ ሆነ።

ሙዚቀኞች ስራዎቻቸውን ገብተው በዚህ ዌብሳት ላይ ማስመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

በሙዚቀኛው ኤሊያስ መልካ ስም የተሰየመው ይህ ዌብ ሳይት(EMCCMO.COM)ባለቤትነታቸው የተረጋገጡ የድምጻውያን ስራዎችን ይመዘግባል ተብሏል።

ዌብሳይቱ የሙዚቀኞችን ስራዎች መመዝገብ ብቻም ሳይሆን በየሚዲያው በ24 ሰዓት ውስጥ ምን ያህል ሙዚቃ እንደተላለፈ የሚመዘግብበትን ወይንም የሚቆጥርበትን ሲስተም አካቷል ተብሏል።

ይህም መገናኛ ብዙሀን በሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች ለሚከፍሉት የሮያሊቲ ክፍያ መረጃን የሚሰጥ ይሆናል።

የኢትዮጲያ አእምሮአዊ ንብረት ባለስልጣን መገናኛ ብዙሀን በሚያጫውቷቸው ሙዚቃዎች የሮያሊቲ ክፍያ አሰባሰብ ላይ ውሳኔ ለመወሰን በዛሬው እለት እየመከረ ይገኛል።

የኢትዮጵያ የቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር እና የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቅጅና ተዛማጅ መብቶች የጋራ አስተዳደር በጋራ ባዘጋጁት ሰነድ ዙሪያም ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

የሙዚቃ፡ የከዋኞች የድምጽ ሪክርዲንግ እና የኦዲዮቪዢዋል ሥራዎች የሮያልቲ አሰባሰብ እና አከፋፈል ቀመር ላይ መገናኛ ብዙሀን መክፈል ስለሚኖርባቸው ክፍያ ለመወሰን ነው ይህ ውይይት እየተካሄደ ያለው።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


የአዲስ አበባን የትራንስፖርት እጥረት ይቀንሳሉ የተባሉ መቶ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ወደ ስምሪት ገቡ

"አውቶቡሶቹ ከአየር ብክለት ነፃ፣ ምቹ፣ በአንድ ጊዜ በርካታ ሠው ማጓጓዝ የሚችሉ፣ ዘመናዊና ተደራሽ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ አስተማማኝ፣ ለአውቶቡስ ብቻ በተፈቀደ መስመር ስለሚጓዙ ፈጣን አገልግሎት የሚሰጡ እንዲሁም ለነዳጅ ይወጣ የነበረውን ወጪ የሚቀንሱ ናቸው" ሲሉ የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

አውቶቡሶች ዛሬ በሁሉም የከተማ አቅጣጫዎች ለነዋሪዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጡም ተገልጿል።

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን  አዋጅ ያፀድቃል

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም 22ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የፌደራል መንግስት በክልሎች ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ የወጣ ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል የሚውል የ96 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላር ወይም የ12 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት ተፈራርመዋል

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና በዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ማሪያም ሳሊም ተፈራርመዋል፡፡

ከተፈረመው ስምምነት ውስጥ 50 ሚሊየን ዶላሩ ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር በብድር መልክ የተሰጠ ሲሆን÷ 46 ነጥብ 367 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ከዓለም አቀፉ የትምህርት አጋርነት ፈንድ በድጋፍ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ድጋፉ የቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ የሚውል ነው መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


🔹አዋጅ  አዋጅ‼️

ለሃቅና ፍትህ ከሚሞተው ህዝብ የፈለቀ እውነተኛ የህዝብ ድምጽን የሚወክል፤  የታፈነውን እውነት ገሀድ የሚያወጣ ሚዲያ እነሆ ብለናል!

እውነትን ፈላጊ፣  ከሆንክ ዝም ብለህ join በል

👇👇👇👇

https://t.me/+_hm4FWfJ63hhNDg0
https://t.me/+_hm4FWfJ63hhNDg0


ትራምፕ ለሦስተኛ ጊዜ ስልጣን ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ተናገሩ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ሕገ መንግሥት የፕሬዚዳንትነት ስልጣን የሁለት ጊዜ ገደብ ቢኖርም፤ ለሦስተኛ የሥልጣን ዘመን ሊወዳደሩ እንደሚችሉ በድጋሚ ተናገሩ።  

ትራምፕ ከአሜሪካዉ «ኤንቢሲ» ዜና ወኪል ጋር በደረጉት ቆይታ "እየቀለድኩ አይደለም" ብለዋል።

ትራምፕ ይህን ህልማቸዉን ለማሳካት ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ዘዴዎችንም ጠቁሟል።

እንደ ትራምፕ በሕገ መንግሥቱ 22ኛው  አንቀጽ፤ ሕገ መንግሥታዊ ለውጥ ሳይደረግ ለሦስተኛ ጊዜ ለስልጣን መወዳደር በሕግ የማይቻል እንዲሆን ያደርጋል ብለዋል።

ትራምፕ ሁለተኛ የስልጣን ዘመናቸዉን ከያዙ በኋላ፣  የመንግስት ዘርፎች ላይ ለዉጥ ለማድረግ ከኤሎን ሙስክ ጋር ተባብሮ መስራትን ጨምሮ ታይቶ የማይታወቅ አስፈፃሚ እርምጃዎችን በመተግበር ላይ መሆናቸዉ ይታወቃል።

የትራምፕ ደጋጋፊዎች በበኩላቸዉ፤ በርታ ከዚህ በበለጠ  ማድረግ አለብህ እያሉ አበጀህ ሲሉ ጥሪ እያሰሙ ነዉ። 

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1


ከ6 ዓመት በኋላ በቁጥጥር ስር ዋለ!

“ካንተ ጋር በፍቅር ግንኙነት መቀጠል አልፈልግም” ብላኛለች የግድያ ወንጀል የፈፀመና በሌለበት የዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት የተላለፈበት ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
***
ተከሳሹ ጌታቸው አለምፀሃይ  ይባላል፡፡ የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ጥር 2 ቀን 2011 ዓ/ም ከቀኑ 5 ሰአት  ገደማ  በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2  ልዩ ቦታው ሳባ ህንፃ ላይ ነው፡፡

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ተከሳሹ በህንፃው 6ኛ ፎቅ ወደሚገኘው የክፍለ ከተማው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ቢሮ ውስጥ በመግባት የፍቅር ጓደኛዬ ናት በሚላት መአዛ ካሳ  በተባለች ግለሰብ ላይ የግድያ ወንጀሉን ፈፅሟል፡፡

“አልፈልግህም ብላኛለች” በሚል ምክንያት በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ግለሰቧን በቢሮዋ ውስጥ እያሯሯጠ የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በስለት በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሹ፤ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ የምርመራ መዝገብ ተደራጅቶበታል፡፡

ጌታቸው አለምፀሃይ በፖሊስ የተጠርጣሪዎች ማረፊያ ቤት በነበረበት ወቅት በህመም ምክንያት ወደ ህክምና ተቋም ለመሄድ የካቲት 19 ቀን 2011 ዓ/ም ጥያቄ አቅርቦ ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኋላ ከህክምና ቦታ እንደተሰወረ እና በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በሌለበት በፍርድ ቤት ሲታይ እንደቆየ የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

በሰውና በሰነድ ማስረጃ ተደራጅቶ የቀረበለትን የክስ መዝገብ ሲመለከት የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት በነሀሴ 3 ቀን 2014 ዓ/ም  ውሎው ጌታቸው አለምፀሀይ በሌለበት በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እና ከህዝባዊ መብቶቹ ለዘወትር እንዲሻር ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡     

የፍርድ ቤቱን የቅጣት ውሳኔ ተፈፃሚ ለማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ የክትትልና ኦፕሬሽን ክፍል ፍርደኛውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቀንና ለሊት ያልተቋረጠ ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓ/ም  ሆለታ ከተማ ውስጥ ከተደበቀበት ስፍራ ወንጀሉ ከተፈፀመ ከ6 ዓመት በኋላ በድጋሚ ሊያዝ ችሏል፡፡

ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ለጊዜው ቢሰወርም ከህግ ተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችል ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ ሌሎችም የወንጀል ጉዳዮች መኖራቸውን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ከህግ ለማምለጥ የሚደረጉ ሙከራዎች ከፖሊስ ክትትል ውጪ እንደማይሆኑ በመገንዘብ ህብረተሰቡ ለፖሊስ እያደረገ የሚገኘውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል እና ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችም ከመሰል ድርጊት እንዲታቀቡ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@Ewun_Mereja1
@Ewun_Mereja1

20 last posts shown.