Feta Daily News


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter






#ታሪክን_የኋሊት

ህዳር ሲታጠን

በሽታው ከኅዳር 7 እስከ 20 በቆየበት ጊዜ 40,000 የሚያህሉ ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል

ብዙዎቹ የሚያውቁት የኅዳር በሽታ (የኅዳር መቅሰፍት) በሚባለው ስሙ ነው።በእርግጥ በሽታው ከውጪ ሀገራት በአየር(ንፋስ) ምክንያት በ1911 ዓ/ም ሀገራችን የገባ ሲሆን ሳይንሳዊ ስሙ "ግሪፕ" ሲባል ኢትዮጵያውያን ደግሞ ኢንፍሎኤንዛ መቅሰፍት ይሉት ነበር። በ3ቀንና በ4ቀን የሚገድል በሽታ ነበር፡፡ በጊዜውም በአዲስ አበባ ብቻ 9000 ሰዎችን ገድሏል።

የሚገርመው የበሽታው አስከፊነት ስለጨመረ በበሽታው የሞተውን ሰው የሚቀብር ሰው አይገኝም ነበር። ሬሳውን ቤተክርስቲያን ሄዶ ለመቅበር አቅም ያጣ ቤተሰብ ደግሞ እዛው ግቢው ውስጥ ይቀብሩ ነበር አንድ ቤተሰብ ሙሉ የሚያስታምማቸው በማጣት ቤተሰቡ በሙሉ ያልቅ ነበር።

አንድ ሰው የሞተበትን ዘመዱን ለመቅበር ጉድጎድ ቆፍሮ ሬሳውን ለማምጣት ቤቱ ሄዶ ሲመጣ በቆፈረው ጉድጎድ ሌላ ሰው ተቀብሮበት ያገኛል አንዳንዶች ደግሞ የሚቀብሩበት ጉድጎድ ጥልቅ ስላልነበር ሬሳውን አውሬ ይተናኮለው ነበር።

በኅዳር 12 ቀን ደግሞ ከበፊቱ ቀናት የሚበልጥ ሰዎች ሞተዋል። በአጠቃላይ በሽታው ከኅዳር 7 እስከ 20 በቆየበት ጊዜ 40,000 የሚያህሉ ሰዎች እንደሞቱ ይነገራል።

በዚህ በሽታ ብዙ ሹማምንትና የዘመኑ ታላላቅ ሰዎች ሞተዋል በበሽታው አልሞቱም እንጂ አልጋ ወራሽ ተፈሪ መኰንን (ኃይለ ሥላሴ)፣ እቴጌ መነን ፣ ንግሥት ዘውዲቱ ተይዘው እንደነበር ይነገራል።

ከዛም ሕዝቡ ይህን መቅሰፍት ለመዳን ቆሻሻዎችን ያቃጥሉ ጀመር። ይኸው ይሄ ዘመን አልፎ እንደ ታሪክ እናወራዋለን። እኛም ቆሻሻዎችን በማቃጠል ይህን አሰቃቂ ዘመን ስናስብ በዛውም አካባቢን ማጽዳት ነው፡፡


እስራኤል በሐማስ ለታገቱባት እያንዳንዱ ዜጎች አምስት ሚሊዮን ዶላር እከፍላለሁ ማለቷ ተሰማ

እስራኤል በሐማስ ለታገቱባት እያንዳንዱ ዜጎች አምስት ሚሊዮን ዶላር እከፍላለሁ ማለቷ ተሰምቷል። የፍልስጤሙ ሐማስ ከአንድ ዓመት በፊት 250 እስራኤላዊንን አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።

ከታገቱ 250 እስራኤላዊን መካከል 97ቱ አሁንም በሐማስ እጅ ስር ይገኛሉ።


ሙዚቀኛዋ ቤተ-እምነት ውስጥ ቪድዮ እንድትቀርፅ የፈቀዱት አሜሪካዊ ቄስ ከሥራቸው ተባረሩ

ሳብሪና ካርፔንተር የተባለች አሜሪካዊት ሙዚቀኛ ቤተ-ክርስትያን ውስጥ ተገላልጣ የሙዚቃ ቪድዮ እንድትቀረፅ የፈቀዱት የኒው ዮርክ ቄስ ሹመታቸው ተገፎ ከሥራቸው ተባረሩ።

ሞንሲኞር ጄሚ ጂጋንቲየሎ ከሥራቸው መታገዳቸውን ያስታወቀው የብሩክሊን ከተማ የሮማን ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ነው።

የዘፋኟ ቪድዮ የተቀረፀው አወር ሌዲ ኦፍ ማውንት ካርሜል ቸርች ውስጥ ሲሆን ይህን ተከትሎ ባለፈው ዓመት ጥቅምት ነው ቤተ-ክርስትያኗ ምርመራ የጀመረችው።

ቄሱ ሞንሲኞር ጄሚ ቤተ-ክርስትያኗን መምራት ተስኗቸዋል አሊያም ሥልጣናቸውን በዝብዘዋል ተብለው ከመከሰሳቸውም ባለፈ ያልተፈቀደ የገንዘብ ዝውውር አድርገዋል የሚል ወቀሳ ቀርቦባቸዋል።




የሰባት ዓመት ታዳጊን በማገት በሚሊየን ገንዘብ የጠየቁ ተፈረደባቸው❗️

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ወልመራ ወረዳ ሆለታ ከተማ የሰባት ዓመት ታዳጊን በማገት በሚሊየን ገንዘብ የጠየቁ ተፈረደባቸው፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን ጠቅላይ ፍርድ ቤት እያንዳንዱ የ11 ዓመት ጽኑ እስራት የተፈረደባቸው ሶስት ወጣቶች እራሳቸውን በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በማስመሰል ወንጀሉን መፈጸማቸው ነው የተገለጸው፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት የዞኑ አቃቤ ህግ ባለስልጣን በሽምቅ መንግስትን በሚፋለሙት ታጣቂዎች ስም ሰዎችን በማገት ገንዝብ የመጠየቅ ወንጀል አሁን አሁን እየተበራከተ መጥቷል፤ ብለዋል፡፡


ዩክሬን አሜሪካ ሰራሽ የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩሲያ ተኮሰች❗️

የባይደን አስተዳደር ለዩክሬን የሰጠውን ፍቃድ ተከትሎ ዩክሬን የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩሲያ ግዛት መተኮሷን የሩሲያ መንግስት ገልጿል።

የአሜሪካ ባለስልጣናት ዩክሬን የአርሚ ታክቲካል ሚሳኤል ሲስተም (Atacms) መጠቀሟን አረጋግጠዋል ነገር ግን ዩክሬን እስካሁን ያለችው ነገር የለም።

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱ ማክሰኞ ጧት በሰሜን ዩክሬን በሚያዋስነው ብራያንስክ ክልል ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አስታውቋል።

አምስቱ ሚሳኤሎች ተመትተው አየር ላይ ሲከሽፉ አንደኛው ግን ጉዳት ማድረሱ ተሰምቷል።




ፑቲን ፊርማቸውን አስቀመጡ❗️

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተሻሻለው የሞስኮ የኑክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ድንጋጌ ላይ ፊርማቸውን አስቀመጡ፡፡

የኑክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ድንጋጌውን ፑቲን ያጸደቁት አሜሪካ ዩክሬን ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳዔሎችን(አርሚ ታክቲካል ባሊስቲክ ሚሳዔል ፤አታከምስ) ተጠቅማ ወደ ጥልቅ የሩሲያ ግዛት ጥቃት እንድትሰነዝር ፈቃዳለች በተባለ በማግስቱ ነው፡፡

ሰነዱ ማንኛውም ኑክሌር ያልታጠቀ አገር በኑክሌር ታጣቂ አገር ድጋፍ ሩሲያን እና አጋሮቿን ካጠቃ በትብብር እንደተመታን እንቆጥረዋለን የሚል ነው ፡፡




''ወታደራዊ ኃይሉን እጠቀማለሁ'' ትራምፕ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህጋዊነት ውጪ ያሉ ስደተኞችን ለማባረር አስቸኳይ አዋጅ በማወጅ ወታደራዊ ሃይሉን እንደሚጠቀሙ ዛሬ አረጋግጠዋል::




በትግራይ ክልል በየሳምንቱ 17 ሺህ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው

በትግራይ ክልል ባለፉት 3 ወራት በወባ በሽታ ምክንያት 13 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የትግራይ ጤና ቢሮ በተለይም ወባን ለመካለከል እና ለመቆጣጠር ከፌደራል መንግስቱ የአቅርቦቶች ድጋፍ እንደሚሻ የሚገልፅ ሲሆን እስካሁን ግን የሚጠበቀው እንዳልተገኘ የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋይ ገብረመድህን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል።


አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " የሶማሌላድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን አሸነፉ

የዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንዲሁም ፋይሰል አሊ ዋርቤ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

የኢሮ ፓርቲ ምርጫውን 63.92 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው። የተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ ፤ ኩልሚዬ ፓርቲ 34.81% ነው ያገኘው።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ሽልማትና ዕውቅና አገኘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው አፔክስ የመንገደኞች ምርጫ 2025 የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ሽልማትና ዕውቅና ማግኘቱን አስታውቋል።

የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች ከበረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጠ ድምፅ መሰረት የተበረከተና በአቪዬሽን ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው አለም አቀፍ ዕውቅና መሆኑ ተመላክቷል።


ከአክሱም ከተማ ጠፍተው የነበሩትን የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ መቀጠሉ ተገለጸ


በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት እና አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ማሳወቁ አይዘነጋም።

የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን የተዘረፉት እና የጠፉትን 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ብለዋል።

የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ኃላፊው እነዚህን ቅርሶች የማስመለስ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።






በባህርዳር ሄሊኮፕተር ተከስክሷል የሚለው መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ - መከላከያ ሚኒስቴር

ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ የተራገበዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ካሉት "ቤዞች" አንደኛው ምድብ የሆነው ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ አየር ምድባችን ነው። ከትናንት በስተያ ቅዳሜ በነበረው የአየር ኃይል የምድብ ልምምድ ምክንያት መደበኛ የአየር መንገድ በረራ ለጥቂት ጊዜያት ተቋርጦ የነበር መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ማኒስቴር አስታውቋል።

ይሁን እንጅ የአየር መንገድ ተሳፍሪዎች የተወሰነ መጉላላትን አጋጣሚ በመጥቀስ ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል የማደናገሪያ ሃሳብ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ እየተራገበ ይገኛል ያለዉ ሚኒስቴሩ

መደበኛ በረራ ለውስን ጊዜያት ተቋርጦ የነበረው በተገቢው መንገድ ስራ የጀመረ ሲሆን የምዕራብ አየር ምድብም ልምምዱን ስኬታማ በሆነ መንገድ አጠናቋል ብሏል።

20 last posts shown.