#የኢጋድ_የትምህርት_ብቃት_ማረጋገጫ_ማዕቀፍ
የኢጋድ አባል አገራት የተጣጣመ የትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ መተግበር ሊጀምሩ ነው።
ይህም የአባል አገራቱ ተማሪዎች በየትኛውም የድርጅቱ አባል አገር ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉበትን ሁኔታ ይፈጥራል።
የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን (ኢጋድ) የተጣጣመ የትምህርት ብቃት ማዕቀፍ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በኬንያ ተካሂዷል።
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አንዱዓለም አድማሴ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በመወከል በመድረኩ ተሳትፈዋል።
ሁሉም የኢጋድ አባል አገራት የራሳቸውን የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ የሚያዘጋጁ ሲሆን ድርጅቱ ከሚያዘጋጀው ማዕቀፍ ጋር እንዲጣጣም ይደረጋል።
አባል አገራቱ የየራሳቸው የትምህርት ስርዓት ያላቸው መሆኑ ችግር እንደማይፈጥር ተነስቷል።
የማዕቀፉ መዘጋጀት ከፍተኛ የህዝብ እንቅስቃሴ በሚታይበት የኢጋድ አካባቢ ዜጎች ያለምንም ችግር ለመስራት እና ለመማር ያስችላቸዋል ተብሏል።
ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ በማዕቀፉ የሚካተቱ የኢጋድ አባል አገራት ናቸው። #TheStandard
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!