ራሱ ትህነግ አደናቅፎታል‼
ትህነግ ሲፎክርበትና ሲያምታታበት የከረመውን በ'ተፈናቃይ' ስም ታጣቂ የማስገባት ሂደት ራሱ አክሽፎታል።
በራያ ያደረገው ወረራ እየታወቀ ጠለምት ላይም ተፈናቃይ ልመልስ ሲል በጊዜው ተደናግረው የወጡ ወርቅ ቆፋሪዎችን ይሆናል በሚል የጠለምት አማራ በጊዜው ወደ ትግራይ የሄዱት እነማን እንደነበሩ ስለምናውቃቸው ከየቀበሌው ሰዎችን ወክለን እንለይ በሚል ሆደ ሰፊነት በርካታ የትግራይ ተወላጆችን ተቀብለው እያስተናገዱ ነበር።
ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ትክክለኛው የትህነግ ዓላማና ፍላጎት ተገልጧል። ከሁሉም ቀበሌዎች የተመረጡ ሽማግሌዎች እንዳረጋገጡት ትህነግ ሦስት አይነት ቡድኖችን ይዞ መጥቷል።
የመጀመሪያው በጠለምት ሽማግሌዎች ነዋሪ የነበሩ መሆናቸው የተመሰከረላቸው የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ እነዚህ ወደ ቀደመ ቀያቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። ከተመለሰት መካከል ትጥቅ መፍታት የነበረባቸው ያልፈቱ በርካታ ሚሊሻዎች ይገኙበታል። ሆኖም ትህነግ በሁለተኛ ዙር ጠለምትን ወርረው የነበሩ የትህነግ አመራሮችን ከማቅረቡም በላይ በሦስተኛ ዙር የሚገቡ በሚል ጠለምትን በጦርነቱ ወቅት ብቻ የረገጡት የታወቁ ዲሽቃና ሞርታር ተኳሾችን ሳይቀር የያዘ የወራሪው ወታደራዊ አባላትን ለማስገባት አስተዋውቋል።
የጠለምት ሕዝብም የሁለተኛና የሦስተኛ ዙር ተመላሽ የተባሉትን ቡድኖች ማንነት በግልጽ ያስረዳ በመሆኑ ትህነግ ደግሞ የወረራ አላማውን የሚያስፈፅምባቸው አካላት የማይገቡ ከሆነ አጠቃላይ ሂደቱ ይቋረጥ በሚል በሕዝብ ፊት ወስኗል።
በሌላ በኩል በአገር ሽማግሌ ተለይተው የገቡት የትግራይ ተወላጆች እየተቧደኑ የጠለምት አማራዎችን ማጥቃት የጀመሩ ሲሆን ለአብነትም የጠለምት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሜቴ አባላትንና ንፁሃንን ከትላንት ጀምሮ ለማካሄድ ሲሞክሩ የቆዩ ሲሆን በዛሬው ዕለት የኮሚቴው ፀኃፊ የሆነው መብራት አዲስ ላይ አካላዊ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል። ይህ አይነት ጥቃት ህዝብ በጥቃቱ ስጋት ተፈናቅሎ ትህነግ አካባቢውን ለመያዝ የሚጠቀመው ስልት ነው ተብሏል።