ትግሉ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ!
1) ግምገማ አድርጉ። ከታችኛው ርከን ጀምሮ ጥያቄውን ያቅርብ፣ ተወካዩ በየደረጃው፣ ከዛም ከፍተኛ አመራሩ ከወራት በፊት ከነበረው የተለዩ ነገሮችን በደንብ ይገምግም። በድፍረት። ከዛም ማስተካከያ እርምጃዎች በይፋ መግለጫ ይነገሩ።
2) በፋኖ ስም ዘረፋ እየፈፀመ ያለ፣ ብልፅግና ሆን ብሎ ያሰማራው ወዘተ ኃይልን በይፋ ማውገዝና ድንበር መለየት ያስፈልጋል። ህዝብ ተማርሯል። የፋኖን ስም የሚያጠፋ፣ ህዝብን የሚያማርር አጋች ቡድንን ጠላቴ ነው ብሎ ማሳየት ያስፈልጋል። በተመሳሳይ በነፍስ ግድያ፣ በስርቆት ወዘተ ሲፈለግ ፋኖን ለመጠጋት የመጣ ወዘተ ካለ በሙሉ ገምግሞ ማሰናበት ያስፈልጋል። መሳሪያ ይዞ ስለመጣ ብቻ አላማውን ይከተላል ማለት አይደለም።
3) አመራሮች አሁን ባለው ወቅት ሁሉንም ነገር መናገር አይጠበቅባቸውም። አንዳንዴ ደግሞ ከአማራ መሰረታዊ ጥያቄ ጋር የሚያጋጩ ጉዳዮች ላይ ያልተገቡ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው። የወልቃይትና ራያን ጉዳይ ጨምሮ ከአማራ መሰረታዊ ጥያቄ ጋር የሚያጋጩ ጉዳዮችን አትነካኩ። የራያና የወልቃይት ጉዳይን ለብአዴን አሳልፋችሁ አትስጡ። የአማራን ጉዳይ እይዛለሁ የሚል ሁሉ የመጀመሪያ አጀንዳ መሆን ያለበት ነው። ሌሎች በህዝብ የሚያስተቹ፣ አከራካሪ ጉዳዮች ካሉ የግድ ዛሬ መነገር አለባቸው ማለት አይደለም። የፋኖ አመራሮች የሴራ ትንተና የመጀመሪያ የሚዲያ ትኩረታቸው መሆኑ ግዴታ አይደለም።
4) ከሚሊሻ፣ ከኃይማኖት አባት፣ ከሽማግሌ ጋር ያለውን አካሄድ ማስተካከል ያስፈልጋል። ካልሆነ አንድ፣ ሁለት፣ ሶስት እየተባለ በየጊዜው እየጨመረ ከማህበረሰብ ጋር ግጭት ያመጣል። ከህዝብ እሴት፣ ከፋኖ አላማ ጋር የማይሄዱ ጥፋቶች ከተፈፀሙ ተገቢ እርምጃ መውሰድና ማሳወቅ ይገባል።
5) እንደግፋችኋለን የሚሏችሁን የቲክቶክ፣ የፌስቡክ፣ የዩቱዩብ ወገኖች በተናጠል መረጃ አትስጧቸው። በእናንተ ስም ሌሎችን እንዲሰድቡ አትፍቀዱ። እናንተም ጋር ነገ ይመጣሉ። ከሰሟችሁ "ተውልን" በሏቸው። እንደ ትግል መጠላለፉ እንቅፋት ሆኖብናል በሏቸው።
6) አንድነት እንዲሁ ላይመጣ ይችላል። በአንዳንድ ጉዳዮች ጀምሩት። ለምሳሌ በጋራ ጉዳይ ላይ በየሳምቱ የጋራ መረጃ ስጡ። እንደ መግለጫም ሊሆን ይችላል። ይህ ተቀራራቢ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል። ለልዩነት መሰረቱ ሚዲያ ጭምር እንደመሆኑ ተቀራራሚ መረጃ፣ ተቀራራቢ ግንዛቤ እንዲኖር ያደርጋል።
7) የተለያየ አጀንዳ ለምሳሌ የጎጥ፣ የስልጣን፣ የዝና ወዘተ ፍላጎት ይዘው የተጠጓችሁን አጥሩ።
ካልሆነ በርካታ ኃይሎች እንደ ቅርጫ ሊከፋፈሏችሁ ተነስተዋል። እንደ አማራ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካው በአገር ደረጃ ውዥንብር ውስጥ ነው። የተለየ ፈተና ውስጥ አይደላችሁም። ሁሉም ኃይል ከእምነት ተቋሞ እስከ ማህበራት ከፖለቲካ እስከ ሲቪክ ተቋም ፈተና ውስጥ ነው። እናንተ አንዱ ተፈታኝ ናችሁ። ራሳችሁን፣ የህዝብን ሁኔታ፣ የቱ አከሰረን፣ የቱ አተረፈን ብላችሁ ገምግሙና ፈተናውን እለፉ። በተለይ በተለይ መጓተቱ ለአማራ ህዝብ ሌላ እዳ እንዳያመጣ መጠንቀቁ ተገቢ ነው።