GONCHA PLUS 🌍


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


We will inform you of new things as much as we can💯


Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


Forward from: ትምህርት ሚኒስቴር
#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ :-
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

Website:

https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444

ትምህርት ሚኒስቴር
@News_for_Student
@News_for_Student


Forbes የ ዓለማችን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች ናቸው ያላቸውን ከ 1-10 እንደሚከተለው ደረጃቸውን አስቀምጧል ከአስሩ ሰባቱ የአሜሪካ ካምፓኒ መሆናቸው ደግሞ የአሜሪካ ሀያልነት ቁልፍ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ይሄ መሆኑን ያሳየናል።በዓለማችን ከአንድ እስከ አስር ካሉት ቢልየነሮች ውስጥ ስምንቱ አሜሪካውያን መሆናቸው ትላንት ፖስት ተደርጎ ነበር። በዚህም ተባለ በዛ አሜሪካ የዓለማችን ገዢ ሀገር ናት።


🔴ውሸት ውሸት ውሸት😱🤭🤭

#እውነታው ኢቢሲ ከትናንት ጀምሮ "ኦፕን ማጋዚን የሚባል የህንድ መፅሄት በአፍሪካ የዲሞክራሲያዊ መሪዎችን ዝርዝር ይፋ አደረገ፣ ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድን በ1ኛ ደረጃ ላይ አስቀመጠ" የሚል ዘገባ ይዞ ሲወዘውዘው ነበር።

የእሱን መረጃ ይዘው ደግሞ የሀገሬ የሶሻል ሚድያ ገፆች እና የዩትዩብ ቻናሎች ሲቀባበሉት ነበር። ከኢቢሲ በተጨማሪ አዲስ ሚድያ ኔትዎርክ፣ የአዲስ አበባ ኮሚኒኬሽን ቢሮ፣ ኦቢኤን አማርኛ... ወዘተ መረጃውን ሲያጋሩ ነበር።

የመፅሄቱ ዋና ኤዲተር ኤስ ፕራሳናራጃን በዚህ ዙርያ መረጃ ለኢትዮጵያ ቼክ ማምሻውን ያደረሰ ሲሆን "እኛ እንዲህ አይነት መረጃ አላወጣንም፣ የእኛም ዘገባ አይደለም። ይህንን ልናረጋግጥላችሁ እንችላለን" የሚል ምላሽ ልኳል።

በዲጂታል መልኩ የታተሙ የመፅሄቱን የቅርብ ግዜ ህትመቶች የተመለከትኩ ሲሆን የተጠቀሰው አይነት መረጃ ይዘው እንዳልወጡ ማየት ይቻላል።

ከሁሉም የሚገርመው ግን የዚህ ሀሰተኛ መረጃ መነሻ በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አለሙ ስሜ ስም ተመሳስሎ በተከፈተ አንድ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት የተሰራጨ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን ማየት ይቻላል። ይህ አካውንት ደግሞ ሀሰተኛ እንደሆነ ኢትዮጵያ ቼክ በተከታታይ መረጃዎችን አቅርቦ ነበር።

ይቺን እንኳን ሳያጣሩ ለሚልዮን ተከታታዮች መረጃ ማቅረብ አይከብድም... ወይም እንደ ክበበው ገዳ አባባል "አይሰቀጥጥም"


ተጨማሪ ከፈለጉ የደወል ምልክቷን ይጫኑ

❯❯❯🔔🔔🔔❮❮❮
💔❤️‍🔥እውነተኛ ፍቅር💕 የሚገኘው ፍፁም የሆነን ሰው በማፈላለግ ሳይሆን ፍፁም ያልሆነውን ሰው ፍፁም አድርጎ በመመልከት ነው። የምትሰጠው ነገር ብዙም ይሁን ትንሽ ፈገግታ ጨምርበት "ለማንኛውም ሠው ጆሮህን ስጥ ፤ ድምፅህን ግን ቀንስ ፤ ሁሉንም ውደድ ፤ ጥቂቶቹን እመን ፤ ማንንም ግን አትበድል ፡፡💞" "የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ ።
ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው ።"መልካም ስም ለሰው ልጅ የመንፈስ ምግብ ነው ።" "ማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነው ።"
Share share Please 🙏🙏🙏

https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24


በጉጂ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ575ሺ በላይ ዜጎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል

👉6ሺ በላይ የሚሆኑ ህጻናት የከፋ ችግር ላይ ናቸው

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በአጠቃላይ 18 ወረዳች የሚገኙ ሲሆን በ9 ወረዳዎች ከ575 ሺ 675 በላይ ዜጎች ለረሀብ ተጋልተጠዋል ሲሉ የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አቶ ዮሀንስ ወርቁ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከ77ሺ በላይ ህጻናት ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 6ሺ 400 ህጻናት ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ ናቸው። በመሆኑም በአፋጣኝ የተመጣጠነ ምግብ እና ህክምና ካላገኙ ከዚህ የከፋ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ኃላፊው ለጣቢያችን ተናግረዋል።


በወረዳዎቹ 819ሺ 192 በላይ እንስሳቶች ግጦሽ እና ውሃ ባለማግኘታቸው ለድርቅ አደጋ እንደታገለጡ እና በየእለቱ ለሞት እየተዳረጉ መሆኑን ተገልጿል።

በመሆኑም በተከሰተው ድርቅ የምግብ፣ የመድሀኒት ፥ የውሃ እና የግጦሽ ችግር በሰፊው እየተስተዋለ በመሆኑ መንግስታዊ ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በአፋጣን ድጋፍ ካላደረጉ የሰዎች ህይወት አደጋ ላይ ናቸው ሲሉ   አቶ ዮሀንስ ወርቁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡


በዞን ባሳለፍነው 2014 ዓመት በተከሰተዉ ረሃብ እና ድርቅ የተነሳ ከ700 ሺ በላይ የሚሆኑ እንስሳት ለሞት መዳረጋቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡


#MoE

106 ሺህ ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ የትምህርት ፕሮግራም ተካተዋል፡፡

በ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በታች ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለአራት ወራት ያህል በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሚሰጠው የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፡፡

የ Remedial ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ባለሙያዎች እና ፕሮፌሰሮች ኮሚቴ በማዋቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት የትምህርት አይነት ይዘቶችን መለየቱን በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

በአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዘኛ፣ የተፈጥሮ ሳይንስና ሂሳብ የትምህርት አይነቶችን የሚወስዱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ እንግሊዘኛ፣ ማህበራዊ ሳይንስና ሂሳብ ትምህርት አይነቶችን እንደሚወስዱ መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ይዘቶቹን መሰረት አድርጎ በተቋማት የሚዘጋጅ (ከ30 በመቶ) እና በማዕከል የሚዘጋጅ (ከ70 በመቶ) የሚያዝ ፈተና በመፈተን በድምሩ 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ የሚያገኙ ተማሪዎች መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመንግስት እና በግል ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል ይችላሉ ብለዋል፡፡
https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24


ብር ሳይኖርህ😒💃ሴትን ልጅ መመኘት ካርድ ሳይሞሉ ዳታ እንደማብራት ነው😂
ተጨማሪ ከፈለጉ👇👇👇

https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24


❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ፍቅረኛ ይዘው ወይም ወደው ያውቃሉ ታዲያ የወደዷት ልጅ ያልተገባ መልስ ተሰጦወት አዝነው ያውቃሉ ነገሩ እንዲህ ነው ሴት ልጅ እንዳልወደደቺህ እና እንደወደደቺህ ማወቅ ከፈለክ
ይህንን አድርግ መጀመርያ ሴት ልጅ ነገሮቺን የመደበቅ ችሎታ በተፈጥሮ የተቸረቺው ነው ማለት እየወደደቺህ አልወድህም የሚል ምላሽ መስጠት እየፈለገቺህ አልፈልግህም የማለት የማስመሰል ችሎታ አላት ስለዚህ
ማረግ ያሉብህ ነገሮች😌
1, አይኗን ተመልከት አይኗን በተመለከትክ ሰአት የአይኗ ብሌን በ 45% በስፋት ከጨመረ አትጠራጠር እየዋሸቺህ ነው
2, ስታወራህ በጭራሽ አንተን አትመለከትክም ማለት አጠገብህ ሁና ለምሳሌ መሬት መሬቱን ዛፉን
ቤቱን ታዲያ ደፉረህ አይኔን እያየሽ አውሪኝ በላትና ደፉራ አታይህም ነገር ግን በኮንፊደንስ ካየቺህ አትወድህም ማለት ነው
እነዚህን ነገሮች በማስተዋል ማወቅ ትቺላለህ
ፕሊስ ቻናሉን share በማረግ
አግዙን

https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24


#ማስታወቂያ
♻️ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ  ት/ት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ፈተና 600 እና በላይ  ውጤት ላመጣችሁ ተማሪዎች

ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ፕሮግራሙ የካቲት 21 አዲስ አበባ 4ኪሎ ሙዝየም የሚካሄድ ስለሆነ
1.  ተሸላሚ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ለሚያደርጉት ጉዞ የአየር ትራንስፖርት መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ቦርዲንግ ፓስና ደረሰኝ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
2.  ተማሪዎች ሰኞ በ20/06/15  ከሰዓት ጀምሮ ወደተዘጋጀላቸው ማረፊያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4ኪሎ ግቢ  እንድትገቡ በማለት እናሳውቃለን


🌍በአለማችን ላይ እየተበራከተ የመጣው
የራስን ማጥፋት ሙከራ በጣም እየጨመረ ሲሆን
ምክኝያቶቹም
🔴ድብርት
🔴ከቴክኖሎጂ ጋር ያለመጠን ቅርርብ
🔴 ከሰው ጋር የመገናኝት ፍላጎታችን

መቀነስ ከብዙወቹ ጥቂቶቹ ሲሆኑ
በአለማቺን ከፍተኛ የራስ ማጥፋት ሙከራ የሚደረግባት ጃፓን ስትሆን
ምክንያቱም ጃፓኖች ሲበዛ ወግ አጥባቂ ናቸው
ይህ እንዳለ ሆኖ ግን 30 በመቶ የሚሆኑት ራሳቸውን የሚያጠፍት
ፈተና በመውደቅ እንደሆነስ ያውቃሉ
https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24
https://t.me/Goncha24


የዋቻሞ ዩኒቨርስቲ የመደበኛ የተማሪወች አቀባበል


♻️ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል።

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በ15 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸው ይታወቃል።

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበውለታል።
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new


🏅 ውሾቹ ይጮሀሉ ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል

> በነገራችን ላይ "ውሾቹም ይጮኻሉ ግመሎቹም ይሄዳሉ" የሚለው አባባል የአረብ ነጋዴዎች አባባል እንደሆነ "የኔ ጀግና" የሚለው የሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት መጽሐፍ ላይም ሰፍሮ እናገኛለን።

አረቦች በግመሎቻቸው የንግድ እቃዎቻቸውን ጭነው በሚሄዱበት ሰዓት የበረሃ ውሾት በጣም ቢጮሁባቸውም እነሱ ላይ ድንጋይ በመወርወር ጊዜን አያባክኑም፤ ምክንያቱም የውሾቹ መጮህ ግመሉን ከጉዞው አያቆመውምና።

በአንድ ወቅት የእንግሊዝ መሪ የነበረው ዊንስተን ቸርችልም ይህንን ብሎ ነበር...
"ባንተ ላይ ለሚጮህ ውሻ ሁሉ እየቆምክ ድንጋይ የምትወረውር ከሆነ ከአላማህ በቶሎ አትደርስም" ንግግሩ እውነታን ያዘለም ነው።
መልስ ለሚገባው እንጂ ለተናገረ ሁሉ መልስ መስጠት አግባብ አይደለም የጊዜ ብክነትም ነው። ምክንያቱም አንዳንዶች የሚጮሁት ትክክለኛ ጥያቄን እና መልእክትን ይዘው ሳይሆን እኛን ከመስመራችን አስወጥተው ከራሳቸው ጎራ ለመመደብ ነውና።

https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new


🦋ሴቶች አውሬ ወንድ ይወዳሉ

ሴቶች ውስብስብ ናቸው፣ ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ከተረጋጋ ህይወት ይልቅ ውጥንቅጡ የወጣ (chaotic) ህይወትን የሚመርጡት። ሰላማዊ እና የተረጋጋ ህይወትን በቶሎ ይሰለቻሉ።

ምሳሌ የሚሆነን ... ጸባየ ሸጋና አንገቱን ደፍቶ ከሚኖር ወንድ ይልቅ ልባቸው የሚርደው ለአውሬው ወንድ ነው።

በአንድ ወቅት የጉግል ኢንጂነሮች "ሴቶች ምን አይነት ወንድን ይፈልጋሉ?" የሚል ጥናት አካሂደው ነበር።

ጥናቱም እንደሚያመላክተው በአብዛኛው ሴቶች የሚነበቡ መጽሐፍቶች ተመሳሳይ የታሪክ ይዘት አላቸው -  አንዲት ምንም የማታውቅ ውብ ሴት ከአንድ የአውሬነት ወይም የአፈንጋጭነት ጠባይ ካለው ወንድ ጋር በፍቅር ትወድቃለች። ሴቷም ይህን ቁጡ የሆነ ፍጥረት አማላ፣ በራሷ መንገድ ገርታ ታቀዘቅዘዋለች።

ሴቶች የሚወድቁላቸው አውሬ ወንዶች እነማን ናቸው?

ሴት፣ ልክ እንደ ኮኮናት ፍሬ ውጪው ጠንካራ እና የማይሰበር፣ ውስጡ ግን ጣፋጭና ለስላሳ ወንድን ትፈልጋለች - በሌሎች ፊት የገዘፈ፣ ከእሷ ውጪ ለማንም የማይንበረከክን ወንድ!

...  ለእሷ ጣፍጦና ለስልሶ ለሌሎች የማይረታ፤ እሷ ብቻ በውስጡ ያለውን ልስላሴና ጣፋጭነት ታገኘዋለች።

የገጹ አንባቢዎች ተሳተፉበት... ሴቶችም፣ ወንዶችም እስቲ ሀሳብ ስጡበት...
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new


የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ዲያቆን ጌታቸው ላይ የ1 ዓመት ከ8 ወር የእስራት ቅጣት ተወሰነበት‼️

በምስራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ወጣት ላይ የ1ዓመት ከ8ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን ፋስት መረጃ ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተከሳሽ ዲያቆን ጌታቸው አለልኝ አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው ውጭ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በማሰብ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 11፡0ዐ ሲሆን በግ / ወይን ከተማ አስተዳደር ዐ1ቀበሌ ልዩ ቦታው አርሴማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ተበዳይ የ12 ዓመት ህፃንን በተክሊል ጋብቻ ወይም በሀማኖት ስርዓት ያገባት በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ማግባት ወንጀል ዓ/ህግ የሰውና ጋብቻው ሲፈፀም የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማያያዝ ክስ መስርቶ ተከሳሽም የዓ/ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት የዓ /ህግ ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ነገር ግን ህፃናትን ማግባት በቤተክርስቲያ ህግ የተፈቀደ ነው ወንጀል አይደለም በማለት ተከራክሮ ፍ/ቤቱም የህግ ምስክሮችን ሰምቶ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁ113/2 / መሠረት ፍ/ቤቱ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 648 /ሀ/በመቀየር እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ ግን የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለት በማመልከቱ በቀን 13/6/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ተብሎ የታሰበውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል ፡፡
https://t.me/ethio24new
https://t.me/ethio24new


#የጥሪ ማስታወቂያ

📌በ2015 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ቀን ከታች በተገለጸው መሰረት:
👉 የካቲት 27 እና 28 መሆኑን እናሳውቃለን
ለተጨማሪ 👇👇👇👇
https://t.me/ethio24new


#ማስታወቂያ የአቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 15/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንድትችሉ ቀኑ የተራዘመ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ:- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።
ለተጨማሪ
watch ⤵️ehio24new


🌍በሞያሌ 11 ህጻናትን በአንድ ሚሊዮን ብር ተደራድሮ ሊሸጥ የነበረዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ  ኮሙኒኬሽን እንደገለጸው  ተከሳሽ መሃመድ ኢጀታ  የተባው ግለሰብ በምዕራብ ባሌ ዞን ባሉ ወረዳዎች በመዘዋወር አስራ አንድ ሴት ህጻናቶችን በተለያየ መልኩ በማታለል  እና ቤተሰቦቻቸውን በማሳመን በህገወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

እድሜያቸው ከዘጠኝ እስከ  አስራ ሁለት ዓመት ውስጥ የሚገኙ  አስራ አንድ ህጻናትን  በአንድ ሽፍን ተሸከርካሪ ጭኖ በሞያሌ ጠረፍ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡የባሌ ዞን ፖሊስ ከአካባቢው ማህበረሰብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ከቦረና ዞን ፖሊስ  ጋር ክትትል በማድረግ  ግለሰቡ ለአስራ አንዱ  ህጻናት  በአጠቃላይ አንድ ሚሊዮን ብር ተቀብሎ ሊደራደር ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን  ተገልጿል፡፡

ተከሻሹን ከቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በማስመጣት  የምርመራ መዝገቡን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በማቅረብ  የዓቃቢ ህግን የምርመራ መዝገብ  ሲከታተል የቆየቀው  የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ  ቤት በዋለው ችሎት ተከሳሽ መሃመድ ኢጀታ ላይ በአስር ዓመት እስራት እና በአምስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን  የባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ  ለብስራት ሬዲዮ የላከው ሪፖርት ያመላክታል፡፡
ለተጨማሪ https://t.me/ethio24new


የእጩ ፍሬሽማን ተማሪዎች ወይም የአቅም ማሻሻያ(Remedial) ፕሮግራም ትምህርት የተማሪዎች ምደባ በዚህ ሳምንት ምናልባት ነገ  ወይም ከነገ ወዲያ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

፨ትክክለኛውን ቀን አላሳወቁም‼️


🌍የባቡር ሀዲዶችን ሲዘርፍ የነበረ ወንጀለኛ በቁጥጥር ስር ዋለ

"የመሰረተ ልማት ንብረቶችን የሰረቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።"

በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር በምንጃር ወረዳ አሞራ ቤት ቀበሌ አቋርጦ የሚሄደዉን የባቡር ሀዲድ ብረት የሰረቀዉን ግለሰብ ከነኢግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የምንጃር ወረዳ የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ሲሳይ ፈጠነ ገልፁ።

መነሻቸዉን ከአሞራ ቤት ቀበሌ መልካጅሎ በማድረግ 1ኛ ኮድ 3A 50830አ.አ 2ኛ ኮድ 3A 39544አአ በሆኑ ሁለት አይሱዙ መኪና ንብረቱን ጭነዉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አንድ ተጠርጣሪ በፀጥታ ኃይሎች ብርቱ ክትትል ከነኢግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ሲዉል ለጊዜዉ ባልተያዙ ተጠርጣሪዎች ላይ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

ኃላፊው አክለለውም በቁጥጥር ስር የዋለዉ ተጠርጣሪ እና ኢግዚቢት ምርመራዉ ተጣርቶ ለሚመለከተዉ የፍትህ አካል መዝገቡ ተልኳል ብለዋል።

ተጠርጣሪዉ በቁጥጥር ስር እንዲዉል ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ የፀጥታ ኃይሎችን እና ማህበረሰቡን ያመሰገኑት ምክትል ኮማንደር ሲሳይ ፈጠነ በቀጣይም ማህበረሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

20 last posts shown.

190

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

➠ማሳሰቢያ➠ የመደበኛ የተመደቡ ተማሪወች እስከ 15 እንዲገቡ የተባለ ሲሆን የሬሜድያል ደግሞ እስከ 22 ድረስ እንዲገቡ ተብሏል ለተጨማሪ GONCHAPLUS
ከምደባ ጋር ተያይዞ የተማሪዎች ጥያቄና ቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜ ዛሬ ያበቃል 👉30,004 ተማሪዎች በ15 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል ማክሰኞ የካቲ...
" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል " - ቅዱስ ሲኖዶስ ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጥ የተወሰደ ፦ " ... በዛ...
የአቅም ማሻሻያ  (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫ እስከ የካቲት 10 ድረስ ማስተካከል ይቻላል ተባለ በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክ...
Forbes የ ዓለማችን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች ናቸው ያላቸውን ከ 1-10 እንደሚከተለው ደረጃቸውን አስቀምጧል ከአስሩ ሰባቱ የአሜሪካ ካምፓኒ መሆናቸ...