TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
GOSPEL TV ETHIOPIA

13 May, 16:10

Open in Telegram Share Report

✝️ መስቀልን መሸከም ✝️

“ከዚያም ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ “በኋላዬ ሊመጣ የሚፈልግ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም በየዕለቱ ተሸክሞ ይከተለኝ፤”
— ሉቃስ 9፥23 (አዲሱ መ.ት)

✍ ብዙ ሰዎች መስቀሌን ተሸከሙ እንጂ መስቀሉን ይሸከም እንደሚል አያስተውሉም። ቃሉ የሚነግረን እያንዳንዳችን ስለምንሸከመው ወይንም ስለ ክርስቶስ ስለምንቀበለው መከራ ነው።

መስቀልን መሸከም ውስጥ የሚፈፀሙ ነገሮች ምንድን ናቸው?

1) በፈተና መፅናት
“በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ምክንያቱም ፈተናን ሲቋቋም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሰጠውን ተስፋ፣ የሕይወትን አክሊል ያገኛል።”
— ያዕቆብ 1፥12 (አዲሱ መ.ት)

2) በክህደት መፅናት
“በመብላት ላይ ሳሉም፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አላቸው።”
— ማቴዎስ 26፥21 (አዲሱ መ.ት)

3) ማንም በማይረዳችሁ ሰዓት መፅናት
“እርሱም እየማለና እየተገዘተ፣ “እኔ ሰውየውን አላውቀውም!” አላቸው። ወዲያውም ዶሮ ጮኸ።”
— ማቴዎስ 26፥74 (አዲሱ መ.ት)

4) እንቅልፍን በማጣት መፅናት
“በመገረፍ፣ በመታሰር፣ በሁከት፣ በሥራ ብዛት፣ እንቅልፍ በማጣት፣ በመራብ፣”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 6፥5 (አዲሱ መ.ት)

5) በተፅዕኖዎች ውስጥ መፅናት
“ነገር ግን የምጠመቀው ጥምቀት አለኝ፤ እስኪፈጸምም ድረስ እንዴት ተጨንቄአለሁ?”
— ሉቃስ 12፥50 (አዲሱ መ.ት)

6) በፀሎት መፅናት
“በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።”
— ሮሜ 12፥12 (አዲሱ መ.ት)

7) በሀዘን መፅናት
“ከዚያም፣ “ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝናለች፤ ከእኔ ጋር በመትጋት እዚሁ ቈዩ” አላቸው።”
— ማቴዎስ 26፥38 (አዲሱ መ.ት)

8) ከኃጢአተኞች ከሚመጣ ተፅዕኖ መፅናት
“ደማስቆ ሳለሁ ከንጉሥ አርስጦስዮስ በታች የሆነው ገዥ ሊያሲዘኝ ፈልጎ፣ የደማስቆ ሰዎችን ከተማ ያስጠብቅ ነበር። ነገር ግን በግንቡ መስኮት በኩል በቅርጫት አውርደውኝ ከእጁ አመለጥሁ።”
— 2 ቆሮንቶስ 11:32-33 (አዲሱ መ.ት)

💎 ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

Share 👉🏼 @GospelTvEthiopia

2.2k 0 32 26
Catalog
Channels and groups catalog Search for channels Add a channel/group
Researches
Telegram Research 2019 Telegram Research 2021
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
Contacts
Support Email
API
API statistics Search API of posts API Callback
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot