⛓💥⛓💥ታማኝ እስረኛ⛓💥⛓💥
🕯ሁለት አይነት እስረኛ በእስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ አንደኛዎቹ ከእስር ቤት የማይወጡ🔒 ሁልግዜ በእስር ቤት የሚኖሩ 🤦♂️🤦♀️🤦♂️ ውጩን ማየት የማይችሉ በእስር ቤት የተሰራውን የሚበሉ🧆 በተዘጋጀላቸው ስፍራ የሚተኙ ናቸው።
#ሁለተኞቹ ደግሞ ከመጀመሪያዎች የተለዩ ናቸው ታሳሪ🔗🔗 ናቸው ነገር ግን ታማኝ ታሳሪ(ታማኝ እስረኛ) በመባል ይታወቃሉ እነዚህ እስረኞች በእስር ቤት ብቻ የተገደቡ አይደሉም🙅♂ ወጭ ይወጣሉ🚶➡️ ከውጭ ይመገባሉ ቤተሰብ አይተው👭👫🧍♀ ይመለሳሉ ነፃ🕺💃 የሆኑ ቢመስሉም እንኳን ከፍርድ በታች ናቸው እስረኛ 🔗🔗 ናቸው። ታዲያ እነዚህ እስረኞች 📌አንድ ነገር ያስተውሱኛል በዚህ ምድር የሚኖሩ አብዛኛውን ሰዎች ያስታውሱኛል ማለትም ብዙ ሰው ባያውቅም ባያስተውልም ነፃ👐 የሆነ ከፍርድ ያመለጠ ቢመስለውም ነገር ግን በፍርድ ውስጥ ነው። የሕይወት መጽሐፍ የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ📖 ስለሁለት ሰዎች ሲያወራ እንደዚህ ይላል
🔖" በእርሱ በሚያምን #አይፈረድበትም፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ አሁን #ተፈርዶበታል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:18)
በልጁ ያመነ ከፍርድ ነፃ ነው ያላመነ ግን #በፍርድ ውስጥ ይኖራል በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እስኪያምን ድረስ በፍርድ ስር ይኖራል ይበላ ይጠጣ ይለብስ ይሰራ ይሆናል ነገር ግን እስረኛ ነው።
ታዲያ አንተስ❓ አንቺስ ❓ከፍርድ ነፃ ናቹ ወይስ በፍርድ ውስጥ ናቹ ❓
በኢየሱስ ክርስቶስ ያመነ ከኃጢአት ህግ ከኃጢአት ፍርድ ነፃ ይወጣል ምክንያቱም የሕይወት መጽሐፍ እንዲህ ይላል ............."
በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 5:1)
#ታዲያ እንዴት ነው ከፍርድ ነፃ የምወጣው ❓ እንዴት ነው የማመልጠው❓
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
" ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤" " ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 10:9-10)
ይድናል ከፍርድ ነፃ ይሆናል የዘላለም ሕይወትን ያገኛል።