بسم الله الرحمن الرحيم በስራ ለተጠመዱ ወላጆችበሕይወታቹ በጣም አስፈላጊው ነገር ምንድነው? የዚህን ጥያቄ መልስ ቀድማቹ በወረቀት ላይ በቅደም ተከተል አስፍሩት፤ በመሰረቱ ዋና የተፈጠረለትን አላህን በብቸኝነት የማምለክ ዓላማ ላልረሳ፣ምሉዕ የሆነውን ቁርዓን የሕይወቱ መመሪያ አድርጎ ለያዘ፣ለሚገጥሙት ሁኔታዎች የሚማርባቸው ለዓለማት እዝነት የተላኩት የነብዩﷺ ተከታይ የሆነ፣በሕይወቱ የሚከሰቱ ነገሮች ሁሉ ከአላህ ውሳኔ ፈቀቅ እንደማይሉ ለሚያምን...ይህ ጥያቄ ምንም ነው።ምክንያቱም በሕይወቱ ቅድሚያ የሚሰጠውን የሚያውቅና ለነገው ስንቁ በደንብ የሚዘጋጅ ሰው የሕይወቱን እርምጃ በቅደም ተከተል ማስቀመጥና መተግበር ይቸግረዋል ተብሎ አይታሰብም።
አብዛኞቻችን ወዳለንበት ተጨባጭ ስንመለስ ለሁላችንም እኩል በተሰጠን 24 ሰዓት ውስጥ የምንተገብረውንና በሕይወታችን ቅድሚያ የምንሰጠው ብለን የጻፍነውን እናነጻጽር፡ ሁለቱም የገጠመለት የታደለ ነው፤ ካልሆነ ቆም ብሎ ራስን መገምገም ሳያስፈልግ አይቀርም።በአሁኑ ሰዓት ያለንበት ተጨባጭ የኑሮ ሁኔታ ሚዛናችንን አዛብቶት ሁሉ ነገራችን ዱንያ ዱንያ ነው ሚለው፤ሰላት በወቅቱ የምንሰግድበት፣ኢስላማዊ እውቀትን የምንቀስምበት፣ቁርዓን የምንቀራበት፣ዱዓ እንኳን የምናደርግበት፣ከቤተሰቦቻችን ጋር መልካም ጊዜ የምናሳልፍበት፣ለሌሎች የምንደርስበት... ጊዜ ሁላ የማይሞላው ዱንያ ጠራርጎ ወስዶብናል።
ወደ ልጆቻችን እንመለስለልጆቻችን በተለይ በልጅነት ጊዜ ከምንሰጣቸው ውድ ስጦታ አንዱ ሙሉ ትኩረቱ ወደነሱ የሆነውን እኛን ነው፤ከራስ በላይ ምን ይሰጣል።በዕለተዕለት ተግባራችን ከልጆቻችን ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ስለተፈጠሩለት ዓላማ ከልጅነታቸው ጀምሮ እንዲረዱ አድርጎ ማውራት፣ልጆች ለአዕምሮ እድገታቸው ጨዋታ በጣም አስፈላጊ ነውና አብሮ መጫወት፣እነሱም የሚያወሩትን ማዳመጥ፣ጥያቄያቸውን ያለመሰልቸት መመለስ.. .ያስፈልጋል።አብዛኛው ወላጅ ስለልጁ ትክክለኛ ባህሪ እንኳን ጠንቅቆ አያውቅም፦ የሚመግበውና የሚንከባከበው ሞግዚት፣ የሚያጠናው በአስጠኚ፣የሚቀራው በኡስታዝ፣የሚመላለሰው በሹፌር፣አስተሳሰቡ የሚገነባው በካርቶን ፊልምና ለራሳቸው ባላወቁ ኢንተርኔቱን ባጥለቀለቁት ሰዎች ከሆነ ሰንባበተ።በዚህ ሁሉ መሃል ወላጆች ለልጆቻቸው ብሩህ ነገ ሲሉ ያለምንም እረፍት እየታተሩ ናቸው፤ ቤት እንኳን ቢሆኑ የስራ ስልክ ፋታ አይሰጣቸውም። አያቹ ክፍተቱን?
ችግሮቹ~ስለልጆቻችን እንዳናውቅና መካከላችን መራራቅን ይፈጥራል
~አሉታዊ ስነ-ምግባሮች እንዲከሰት ያደርጋል
~ስሜታቸውን በቀላሉ ለመረዳት ያዳግታል
~ከወላጅ ይልቅ ይበልጥ ወደ ጓደኛ ያደላሉ
~የወላጆቻቸው መወጠር በነሱ ምክንያት ስለሚመስላቸው የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል።
መፍትሔ~የጊዜ አጠቃቀማችንን ማስተካከል
~ አብረን የምንሆንባቸውን ጊዜያት እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀም(አብሮ መመገብ፣ት/ቤት ማድረስ. ..)
~ዕለታዊ ተግባሮችን አብሮ ማድረግ(ሰላት
አብሮ መስገድ ማለማመድ፣የቁርዓን ሃላቃ ቤት ውስጥ በማዘጋጀት
አብሮ መቅራት.. .)
~ከተቻለ የስራን ስልክን ውጪ አጠናቆ መግባት
~በቀን ውስጥ ትንሽም ደቂቃ ቢሆን ሀሳብን የሚሰርቁ ነገራቶችን በማስወገድ(ቲቪ፣ ስልክ...)ከልጆች ጋር ጊዜ ሚያሳልፉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፈልጋል።
እያንዳንዱ የምናሳልፈው ቀን ዋጋ አለው ለነገ እርግጠኛ አይደለንም እና አሁኑኑ ለውጡን እንጀምር አላህ ያግዘን!
رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَاماً
https://t.me/bezretulkheyrበሌሎች አማራጮችም ይከታተሉ👇👇👇
Facebook page https://www.facebook.com/profile.php?id=61563830304613&mibextid=ZbWKwL