ሃፍ ታይም ፉትቦል - Half Time Football


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Sport


እግርኳስ ቅመም እንጂ ወጣወጥ አይደለምና በሚገባው ልኬቱ ለማቅረብ ቆርጠን ተነስተናል !!!
ይቀላቀሉን
since everybody is focusing on writing and blogging about the few elite football professionals & clubs, we focus mainly on interesting current affairs & in depth analysis of the most import

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Sport
Statistics
Posts filter


🚨 በነገራችን ላይ አርሰናል " በጉዳት ከመታመሱ " በፊት ከሊቨርፑል ጋር የነበረው የነጥብ ልዩነት ይህን ይመስል ነበር

📌 አንድ ቡድን ተጫዋቾቹ በተደጋጋሚ የማይጎዱበት ከሆነ የእድል ጉዳይ ሳይሆን የplayer management ነው

- የተጠና የልምምድ ቆይታ (training sessions)
- ከጨዋታ ቡሃላ ያለ ማገገም (post match recovery)
- ከተጫዋቾች ፊትነስ ጋር የሚሄድ የአጨዋወት ስታይል (physical intensity)
- የጨዋታ አመራር (in game management) ከብዙ በጥቂቱ ተጫዋቾች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀንስ የሚጠቅሙ ስልቶች ናቸው

ይህን በማድረጉ ረገድ ደግሞ አርኒ ስሎትና ረዳቶቻቸው ከየርገን ክሎፕ ጊዜ በተለየ ተጠበው መስራታቸው ልጆቻቸው በሊጉ ማራቶን ዘላቂ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል

Anyways ሰንጠረዡን አይታችሁ ስትጨርሱ የሊቬን ቀዩ ማልያ መግዛት ከፈለጋችሁ ከታች ያለውን ሊንክ ተጠቀሙ
👇👇👇👇👇👇
https://www.delina.app/mobitemdetails.php?itemId=165&ref=InjuryTg


🚨🇧🇷 ቪቶር ሮኬ ባርሴሎናን ለቆ ፓልሜራስን በቋሚ ተቀላቅሏል::

የብራዚሉ ክለብ 25.5 ሚሊዮን ዩሮ በቅድሚያ እንዲሁም 5 ሚሊዮን ዩሮ እንደሁኔታው ይከፍላል

የ20 አመቱ አጥቂ 4 የላሊጋ ጎሎች ካስቆጠረበት ሪያል ቤቲስ ጋር የነበረውን የውሰት ውሉ አቋርጦ ወደሃገሩ ያመራል::


👚ሊዮኔል ሜሲ ከ Apple Music ጋር ባደረገው ቆይታ ካነሳቸው ነጥቦች መካከል

- በክለቡ ውስጥ ያለን ሰዎች በሙሉ ኢንተር ሚያሚን ማሳደግ , ውጤታማና ባለድል ማድረግ እንፈልጋለን

- ቡድኑን ከተቀላቀሉት አዳዲስ ተጫዋቾች ጋር ቆንጆ የሆነ ኬሚስትሪ እየፈጠርን ስለሆነ ብቃታችንን እናሳያለን

- ሜጀር ሊግ ሶከር (MLS) በአሜሪካዊያን ዘንድ ተቀባይነቱ እየጨመረ ቢሆንም ሌሎች ክለቦች የኢንተር ሚያሚን ሞዴል ቢከተሉ የበለጠ ጥራቱን ማሳደግ ይቻላል

- በሊጉ ውስጥ ያሉ ቡድኖች በፍጥነት ማጥቃትን ስለሚመርጡ ጨዋታዎቹ የበለጠ ለፉክክር ምቹ ናቸው


🚨ሩበን አሞሪም ስለ አንድሬ ኦናና

- ኦናና አደገኛ ሙከራዎች እያዳነ ቡድናችንን በተደጋጋሚ ታድጓል::

- አልፎ አልፎ ስህተቶችን ቢሰራም ኖርማል መሆኑን አውቀን እሱን ማገዝ ይገባናል


🚨🔙 ካርሎ አንቸሎቲ: “ኪሊያን እምባፔ የጥርስ ህመሙ ስለተሻለው ከሪያል ቤቲስ ጋር ለሚደረገው ጨዋታ ዝግጁ ነው:: እሱ ማድሪድን ለመገዝ ሁሌም ደስተኛና ዝግጁ ነው::”


🚨🇧🇪 ቲቦ ኮርትዋ ማድሪድ ሲቲን በገጠመበት የሻምፕዮንስ ሊግ ጨዋታ የቤልጂየም ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ የሆነው ሩዲ ጋርሺያ ጋር መመካከሩን ተከትሎ ከሁለት አመታት ቆይታ ቡሃላ ሃገሩን ለማገልገል ተስማምቷል::


🚨🇺🇾 ዳርዊን ኑኔዝ በክረምቱ ሊቨርፑልን ለቆ አል-ናስርን ሊቀላቀል እንደሚችል ፋብሪዚዮ ሮማኖ ሹክ ያለ ሲሆን እንደዘገባው ከሆነ ጃንዋሪ ላይ የተጀመረው ጥረት መስኮቱ ሲከፈት እንደሚጠናከር ይጠበቃል


🚨🔵 ቶድ ቦሊ ስለቼልሲ አስተዳደሩ

- የብሪቲሽ ሚዲያዎች ያገኙትን ማራገብና ጎዶሎ መረጃ ማቅረብን ተክነውበታል

- እንደክለብ ተስማምተን ያስቀመጥነውን መንገድ ነው እየተከተልን የምንገኘው

- ወደሁዋላ እያየዩ ስራን መስራት አልወድም


🥺ሲቲን ስለቅ ፔፕ የተናገረኝን መቼም አልረሳውም

- በሁለት አመታት ውስጥ ላደረክልንና ለሰጠከን ነገር በሙሉ ከልብ አመሰግንሃለው::

- በርካታ ዋንጫዎችን ሰጥተከናል የነበረህ ስብእና ልዩ ነበር:: አንድም ቀን ችግር ሳትፈጥርና ድምፅህን ሳታሰማ ነው ያለህን በሙሉ ሜዳ ላይ ያበረከትከው

ጁሊያን አልቫሬዝ በሲቲ ቤት
103 ጨዋታዎች አድርጎ
36 ጎሎችን አስቆጥሯል
17 አሲስቶች አበርክቷል

1 ሻምፕዮንስ ሊግ
2 ፕሪሚየር ሊግ
1 ኤፍ ኤ ካፕ
1 ሱፐር ካፕ
1 የአለም ክለቦች ዋንጫን አንስቷል


⚠️ ፊፋ ማርች 1 በሚያደርገው ቀጣይ ጉባኤው ስራ ላይ የሚያቀርባቸው አራት ማሻሻያዎች


▶️የቬንገር ኦፍሳይድ :- አንድ ተጫዋች ሙሉበሙሉ ኦፍሳይድ ካልሆነ በቀር አውራ ጣቱ ገባ ተብሎ አይሻርም

▶️የመሃል ዳኛው የቫር ውሳኔዎችን በድምፅ ማጉያ ያብራራሉ - ጭቅጭቁ ይቀንሳል

▶️አሰልጣኞች በቫር ይታይል የማለት መብት ይሰጣቸዋል - የተገደበ ቢሆንም "ተበደልን " የሚለውን ለቅሶ ይቀንሳል

▶️ ዳኞች ጉዳት ሲያጋጥምና አንዳንድ ጉዳዮች ሲከሰቱ ሰኣት የማቆም አማራጭ ይኖራቸዋል

እነዚህ ህጎች የሚፀድቁ ከሆነ ከጁላይ 1 2025 አንስቶ ተግባራዊ ይሆናሉ


🚨 ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዚህ የፕሪሚየር ሊግ ሲዝን ለማንችስተር ዩናይትድ

🌟 13 የግብ አስተዋጽዖ በማበርከት አንደኛ ነው

🌟 ከየትኛውም የማንቸስተር ዩናይትድ ተጫዋች በላይ 59 የግብ እድሎችን ፈጥሯል ( ከአማድ በ20 ይበልጣል)

🌟 ትላልቅ የግብ እድሎችን በመፍጠር ቀዳሚ ነው (12 Big Chances Created)

🌟 7 ግብ የሆኑ ኳሶችን በማቀበል ቀዳሚ ነው

🌟 1995 ተቾችን በማስመዝገብ, 31 ፋውሎችን በማሸነፍ , 140 ጊዜ ኳስን ከተጋጣሚ በመንጠቅ ቀዳሚው ነው

🥈 126 የአየር ላይ ሽሚያዎችን በማሸነፍ ከቡድኑ 2ኛ ነው

ያለፉት 6 የማንችስተር ዩናይትድ ጎሎች በሙሉ የተገኙት ከእርሱ ነው

በሁሉም ውድድሮች ካስቆጠራቸው ያለፉት 8 ጎሎች መካከል 7ቱ ዩናይትድን አቻ / አሸናፊ ያደረጉ ናቸዉ

⚽️ 🆚 ኤቨርተን - አቻ 🤝
⚽️ 🆚 ሬንጀርስ - ድል 💪
⚽️ 🆚 ብራይተን - አቻ 🤝
⚽️ 🆚 አርሰናል - አቻ 🤝
⚽️ 🆚 ሲቲ - አቻ 🤝
⚽️ 🆚 ፎረስት - ❌
⚽️ 🆚 ሌስተር - ድል 💪
⚽️ 🆚 ቼልሲ - አቻ 🤝

Captain fantastic. ©️
🔴የማንችስተር ዩናይትድ ቀዩን ማልያ ለመግዛት ከፈለጉ
👇👇👇👇👇
https://www.delina.app/mobitemdetails.php?itemId=186&ref=BrunoTg


ሳላህ በአንፊልድ

142 G/A
140 ጨዋታዎች

King of Anfield 👑


📌ሞሃመድ ሳላህ የሲዝኑ 17 የሊግ አሲስቱን አስመዝግቧል

⏳የኦንሪና ዴብሩያንን ሪከርድ ለመጋራት 3 ለመስበር ደግሞ 4 አሲስቶች ብቻ ይቀረዋል (10 ጨዋታዎች አሉት)

🔥በሁሉም ውድድሮች 39 ጨዋታዎችን አድርጎ 52 የግብ አስተዋጽዖ አበርክቷል

በወርሃ ፌብሩዋሪ 13 G/A
🕹 7 ጨዋታዎች አድርጎ
⚽️ 8 ጎሎች አስቆጥሯል
🅰️ 5 አሲስቶች አበርክቷል

የሊቬን ቀዩ ማልያ ለመግዛት ከፈለጉ
👇👇👇👇👇
https://www.delina.app/mobitemdetails.php?itemId=165&ref=SalahTG


😱 አስገራሚው የሃሪ ማጎየር ሪከርድ
የ32 አመቱ ሴንተርባክ ከ23/24 የውድድር ዘመን ጅማሮ አንስቶ
7️⃣ ከማርከስ ራሽፎርድ እኩል ጎሎችን አስቆጥሯል
6️⃣ አንቶኒ(4) እና ሳንቾ(2) በድምሩ ካስቆጠሩት በላይ 7 ጎሎችን አስቆጥሯል


📌ምስጋና ለሃሪ ማጎየር ይገባና ማንችስተር ዩናይትድ በ27ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሃግብር ኢፕስዊች ታውንን በኦልትራፎርድ አስተናግዶ 3-2 በማሸነፍ ከሶስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች በኋላ ወደድል አድራጊነቱ ተመልሷል።

ማንችስተር ዩናይትድ በመጀመሪያው አጋማሽ
- በዶርጉና በኦናና መካከል በተፈጠረ ያለመናበብ ግብ ተቆጠረበት
- አቻነት የሆነው በown goal ነበር
- ፓትሪክ ዶርጉ በ43ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወገደ
-ለእረፍት ለመውጣት ሽራፊ ሰከንዶች ሲቀሩ ግብ አስተናገደ

ሆኖም ከመልበሻ ክፍል መልስ ሃሪ ማጎየር በዚህ ሲዝን ለ3ኛ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን የታደገበት ጎልን በማስቆጠር ቀያይ ሰይጣናቱን የ3 ነጥቦች ባለቤት አድርጓል።

⚽️ የአቻነት ግብ vs ፖርቶ
⚽️ የማሸነፊያ ግብ vs ሌስተርን
⚽️ የማሸነፊያ ግብ vs ኢፕስዊች


የሃሪን ጎል ይመልከቱ
👇👇👇👇👇
https://t.me/HTFvids/15619


ሃሪ ማጎየር ከእረፍት መልስ ዩናይትድን ወደ መሪነቱ ያመጣች ጎልን አስቆጥሯል

3-2


ፓትሪክ ዶርጉ በቀይ ወጣ
ኢፕስውች ደገመ

2-2


ማንችስተር ዩናይትድ በ4 ደቂቃዎች ውስጥ ባስቆጠራቸው ጎሎች ኢፕስዊች ታውንን 2-1 እየመራ ይገኛል

ሳም ሞርሲ (og) ጎል
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/HTFvids/15613

ማቲያስ ዴሊንግት ጎል
👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/HTFvids/15614


Goaaaaaaaal
ማን ሲቲ 1-0 ስፐርስ
ሃላንድ

20 last posts shown.