ከጭማቂ ይልቅ ሳይጨመቅ ሙሉ ፍራፍሬዎችን መብላት
የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት በጤና እና የደም ስኳር ላይ የሚያመጣው ተጽእኖ ሙሉ ፍሬውን ከመብላት በተቃራኒ ነው። የፍራፍሬ ጭማቂ መጠጣት ሙሉ ፍሬውን ከመብላት በበለጠ ፍጥነት በደም ውስጥ ያለው የግሉኮስ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል።
ጠቃሚ የፍራፍሬው ክፍል ተራግፈው ስለሚቀሩ ንጹህ የፍራፍሬ ጭማቂ የፍራፍሬውን ስኳርና ውሃ ብቻ የያዘ ነው። ጭማቂ ውስጥ የሚቀረው የፋይበር መጠን በጣም ትንሽ ነው። በተጨማሪም ጣዕምን ለማሻሻል ሲባል የፍራፍሬ ጭማቂ ውስጥ ስኳር የመጨመር እድላችን ሰፊ ነው። መጠኑም ቢሆን አንድ ብርጭቆ ጭማቂ ብዙ ፍራፍሬ ሊይዝ ይችላል። ጭማቂ ፈሳሽ ስለሆነ ከአንጀት በፍጥነት ሰርጎ ወደ ደም ይገባል።
ሙሉ ፍራፍሬ ፋይበር፣ ቫይታሚንና ማዕድኖችን ይዟል ይህም ለአጠቃላይ ጤና ጠቃሚ ነው። ፋይበሩ የፍራፍሬው ተፈጥሯዊ ስኳር ወደ ደም ውስጥ የሚገባበትን ፍጥነት እንዲቀንስ እና ረዘም ላለ ጊዜ የጥጋብ ስሜት እንዲኖር ያደርጋል። በተቃራኒው ጭማቂ ወይም የታሸገ ጁስ ከሆነ ግን አብዛኛው ፋይበር በጭማቂ ማዘጋጀት ሂደት ይወገድና ስኳር ብቻ ይቀራል። ጭማቂ ስንጠጣም ፍራፍሬ እንደማኘክ ጊዜ ስለማይወስድ ሳናስተውለው በአንድ ትንፋሽ ብዙ ስኳር ለመጠጣት ይዳርጋል።
ለዚህም ነው በጁስ (ፍሬሽ ጭማቂም ይሁን የታሸገ) መልክ ካለው ፍራፍሬ ይልቅ ሙሉ ፍራፍሬን መብላት የሚበጀው።
ምንም እንኳን የፍራፍሬ ጭማቂ ከመጠጣት ሙሉ ፍራፍሬን መብላት የተሻለ ቢሆንም የተወሰነ ጭማቂ መውሰድ ከፈለጉ በቀን ከአንድ ትንሽ ብርጭቆ (150 ሚሊ ሊትር) የማይበልጥ ሆኖ በውሃ በደንብ በማቅጥን መጠቀም ይችላሉ።
Telegram: https://t.me/HealthifyEthiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@HealthifyEthiopia
@HealthifyEthiopia