አስ-ሱንና


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


አስ- ሱንና
ሱናሕ የኑሕ መርከብ ናት የተሳፈረባት ይድናል ወደ ኻላ የቀረው ይሰምጣል !!
🫵ቅድሚያ ለተውሂድ ተውሂድ የነብያት ሁሉ ጥሪ ናት ☝️

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter




🏷️የዛዱል መዓድ ፈታዋ 🌾
فتاوى زاد المعاد
          ቁ/268

🔊በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

        የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ
⏬  ⏬   ⏬   ⏬   ⏬  ⏬

🔎https://tinyurl.com/yy6u4xue
        🔹🔸🔹🔸🔹🔸

▪️1) የሀዲሰል ኩርስይና የነብያችን ሀዲስ ልዩነቱ ምንድነው ያብራሩልኝ።

▪️2)  አንዲት እህት በሃይዷ መዛባት ምክንያት ሰላት አትሰግድም። ሃይዷ በሚመጣበት ጊዜ በጣም ይቆይባታል። አንድ አንዴ በሰባት/በአስር ቀኑ ይቆምና በቆመ በ3ኛ ቀኑ ምናምን መልሶ ይመጣል። ከዛ 1 ወር 2 ወር ይቆይባታል። እዲም ቆይቶ ካቆመ በኋላ ሲመጣም ቆይቶነው ሚመጣው። ሃይድ ማየት ከጀመረች 3ት አመት ቢሆናት ነው። እስካሁን በትክክል መጥቶ አያውቅም ከጅምሩም እደተዛባ ነው ትላለች። ሰላት አትሰግድምና እንዴት ታድርግ?

▪️3) አንዳንድ ሰዎች ጠላት አሉብኝና በሲሕር ሊያጠቁኝ ይችላሉ በማለት አንድ አንድ የሚያጠራጥራቸውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ ያከሽፈዋል በሚል ውሃ ይደፉበታል። ይህ እንዴት ነው።እውነት ያከሽፋል?

▪️4) መንይ መዝይ እና ከሴት የሚወጣ ፈሳሽ በደምብ ሊገለጥልኝ አልቻለም
ከእንቅልፍ ስንነሳ ምናገኘዉ ፈሳሽ ቢብራራልን።

▪️5) ዝምድና መቀጠል ያለብን እስከ ምን ድረስ ነው። ምሳሌ እስከ አጎት ወይስ የወላጅ አጎት ወይስ እስከ ማን? ቢያብራሩልን።

▪️6) የአባቱ ስም የማይታወቅ ከማሳደጊያ ወስደው የሚያሳድጉትን ልጅ በራስ ስም ማስጠራት ይቻላል? ካልተቻለስ ምን ተብሎ ነው ልጁ መጠራት ያለበት?

▪️7) እኛ አካባቢ ያለው መስጅድ ሁሉ ጊዜ ሱብሂ ሰላት ላይ ቁኑት ያደርጋሉ እና ይሄ ደግሞ በሱና ያልተገኘ ነው ምን ባደርግ ይሻላል? አሚን ብል ወይስ ዝም ብዬ ብቆም?

▪️8) ድምፃችን አውጥትን በምንሰገድበት ጊዜ ቢስሚላህ በውስጥ ማለት አለብን? በማስረጃ ቢያብራሩት በጣም አስፈላጊ ሆኖብኝ ነው ሰዉ ለማስረዳት ነው።

▪️9)  በonline (zoom) የምማረው ትምርት ነበር። ትምርቱን የምንማር ልጆች የራሳችን ግሩፕ  አለን ለመተጋገዝ የከፈትነው።እኔ ከነሱ የተሻልኩ እንደሆንኩኝ በማሰብ ደሞ አንዳንድ የግሩፓችን ተማሪዎች ያልገባቸውን ነገር በonline እንዳግዛቸው ይጠይቁኛል። ወንዶቹን የቻልኩትን zoom አፕ ላይ በግል እየተገናኘንና በድምጽ እያወራን አስረዳቸዋለው ።እንዳስረዳቸውና እንዳግዛቸው ለሚጽፉልኝና ለሚደውሉልኝ ሴቶችስ ኡስታዝ? በዚሁ መንገድ በግል ማገዝ ይፈቀድልኛል?

▪️10) አንዲት የጓደኛዬ እህት ዉጭ ሀገር ትኖር ነበር እና ገንዘብ ስታስቀምጥ ከወለድ ጋር ነበር ወደ ሀገር ስትመለስ ወንድሟ ስራ አብረዉ ለመስራት ብሩን እከነወለዱ አዉጥተዉ ሥራ ጀመሩ ሥለ ወለዱ እሷም እሡም አያዉቁም በመሀል ከእኔ ጋር ተጋባን ከ2አመት በህዋላ ከእኔ ጋር ከተጋበን ከ100000 ብር 85000ብር ተሠጠት እኔ ከቆየ ቡሃላ ሳጣራ ብሩ ከወለዱ ጋር እንደወጣ አወኩኝ ብሩ ጠፍቶ አልቆዋል ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ ወንጀለኛስ እሆናላሁን?

▪️11) ከዚህ በፊት በምስራበት መስሪያ ቤት የህክምና በግል ሆስፒታል ታክመን ወጪ  ይሸፈንልን ነበር አሁን ግን ጤና መድን ተመዝግባቹህ በዛ በኩል ታከሙ አሉን በዛ በኩል ከሆነ ብቻ ነው ወጪው ሚሸፈነው ለጤና መድን መመዝገብ ይቻላል?

▪️12) ሴት ልጅ ኸይድ ላይ ሆና ከባለቤቷ ጋር በስሜት ስትነካካ የሷም የዘር ፈሳሽ የወጣ ከመሰላት መታጠብ ያለባት ወዲያው ነው ወይስ ከኸይድ ስትጠራ ነው?

▪️13) በኢትዮጲያ univeristy ገብቶ ህግ መማር እና ጠበቃ ወይም የህግ አማካሪ ሆኖ መስራት ይቻላል?

▪️14) በማታ ጥፍር መቁረጥ እንዴት ይታያል? ሰዎች በማታ ጥፍር መቁረጥ ድህነት ያመጣል ሲሉ ሰምቼ ነው።






መርካቶ ዛሬም ቃጠሎ ደረሰ እየተባለ ነው። ግራ የገባ ነገር። ለማንኛውም ነጋዴዎች አደጋውን በመከላከልም ይሁን ጉዳትን በመቀነስ ላይ ማድረግ የምትችሉት ጥንቃቄ ካለ አስቡበት። እቃ መቀናነስ፣ በተለየ ትኩረት የሚፈልጉ በጣም ውድ እቃዎችን ወይም ዶክመንቶችን ማራቅ ሊሆን ይችላል። ብቻ የሚቻላችሁ ካለ አስቡበት። መርካቶ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አካባቢዎች ያላችሁ ትኩረት አድርጉ።
የተጎዳችሁን አላህ ይተካችሁ። ሌሎቻችሁን አላህ ይጠብቅላችሁ።
=
©


የጉዞ ማስታወሻ
~
በቅርቡ ለሳምንት ያክል በአንድ የአፍሪካ ሃገር ውስጥ ቆይታ አድርጌ ነበር። ጉብኝቱ ላይ የተገኘሁት በአንድ በሙስሊሞች ዙሪያ ሰፋፊ ኸይር ስራዎችን በመስራት ላይ በተሰማራ ወዳጅ ያላሰብኩት ግብዣ ተደርጎልኝ ነው። በቆይታዬ ላይ እንዲሁ ትኩረቴን የሳቡኝን ነገሮች ማንሳት ወደድኩኝ።

1- ኢስላምን ለማስፋፋት፣ ሙስሊሞችን ለማገዝ ሃብታቸውን በማፍሰስ፣ ከሃገርና ከቤተሰብ ርቀው ደፋ ቀና የሚሉ 0ረቦችን ተመልክቻለሁ። ከኛ ጋር የማይቀራረብ ምቾት የለመዱ ከመሆናቸው ጋር ሁለ ነገራቸውን ጥለው ለዲን መስዋእትነት ሲከፍሉ ሳይ የኛ ስንፍና ፍንትው ብሎ ነው የታየኝ። እኛኮ በገዛ ሃገራችን ውስጥ በየገጠሩ እየወጣን የረባ እንቅስቃሴ አናደርግም። ባለንበት ከተማ ውስጥ እንኳ የረባ ትጋት የለንም። እኛኮ አላህ ከሰጠን ሃብት ለደዕዋ የምንዘረጋው እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። እኛኮ ከስራችን እንቅፋታችን ይበዛል።

2- ሌላው የገረመኝ ነገር በሃገሪቱ ውስጥ በረጅም ዘመናት ኢስላምን ረስተው ከነጭራሹ ሃይማኖት አልባ የሆኑ ህዝቦች መኖራቸውን መስማቴ ነው። ይሄ አስደንጋጭ ነገር ነው። ወደኛ ተመልሼ ሳስብ ተቀራራቢ እውነታዎች እንዳሉ ነው የገባኝ። ሰሜን ሸዋ ላይ በርካታ ዐረብኛ ፅሁፍ የተተከለባቸው መቃብሮች አሉ። የጥንት አርጎባዎች መቃብር ናቸው። ዛሬ አካባቢው ኦርቶዶክስ ነው። ሃዲያዎች በአብዛኛው ወደ ጴን .ጤነት ተቀይረዋል። ደቡብ ጎንደር ላይ እምነት አልባ የሆኑት አውራ አምባዎች የእስልምና ታሪካቸው የሩቅ አይደለም። እነዚህ የለየላቸው ክስተቶች ናቸው። በደርግ የሶሻሊዝም ፋሽን ከኢስላም የራቁት ቀላል አይደሉም። ዛሬም በየ ገጠሩ እጅግ ብዙ ወገናችን ሙስሊም ነው ለማለት በሚከብድ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። አጥብቀን ካልሰራን ብዙ የባሱ ነገሮች ይከሰታሉ።

3- የኛ ሃገር ሙስሊም ተጨባጭ ከብዙ ሃገራት አንፃር ሲታይ ከነ እንከኑ የተሻለ እንደሆነ ያለኝን ግምት አሁንም ከፍ አድርጌያለሁ። በጀማዐ ሶላት ታዳሚ ብዛት፣ በሴቶች አለባበስ፣ በወጣቱ ዲናዊ ንቅናቄ፣ ... ሌላው ቀርቶ ከብዙ የዐረብ ሃገራት ሳይቀር የተሻለ ነው። ይሄ አላህን ልናመሰግንበት የሚገባ ነው። ቀጥሎም ለዚህ ለውጥ አሻራቸውን ያሳረፉ መሻይኾች፣ ዱዓቶች ለኢትዮጵያ ሙስሊም ባለ ውለታ ናቸው።

4- በሄድኩበት ሃገር ሌላው ያስተዋልኩት የደዕዋውን እንቅስቃሴ የሚመሩት እንዳለ የመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ምሩቆች ናቸው። ይሄ የዚህን ትልቅ ተቋም ትልቅ አበርክቶ የሚያሳይ ነው። በኛ ሃገር ደዕዋ ላይም የመዲና ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲ ጥሩ አስተዋጽኦ አለው። ይሁን እንጂ ደዕዋው ላይ ካሉት ይልቅ ለአመታት ሲማሩ ቆይተው ባክነው የሚቀሩት ይበዛሉ።

5- ሌላው የጃሚ0 ትምህርት በቂ የዒልም ትጥቅ እንደማያስታጥቅ ነው ከብዙዎች አቅም የተረዳሁት። ከሃገር ውጭ ትምህርት ላይ ያላችሁ ወገኖች በግል እየጣራችሁ ራሳችሁን በሚገባ እንድታበቁ አደራ እላለሁ። ካልሆነ ግን የማይጠቅም ስምና ጉራ ነው የሚተርፋችሁ።

6- ሌላኛው በሄድኩበት ሃገር ያየሁት ሙስሊሞች ሰፊ ነፃነት ያላቸው መሆኑ ነው። ከመንግስት በኩል ጫና የለባቸውም። ዐረቦች በነፃነት ሙስሊሞችን ያገለግላሉ። በሙስሊሞች ለሙስሊሞች የተገነቡ የወንዶች ትምህርት ቤቶች፣ የሴቶች ትምህርት ቤቶች፣ የአይታም ማዕከላት፣ ሌሎችም ተቋማት ውስጥ መስጂዶች አሉ። የመንግስት ኃላፊዎች ባሉበት ምረቃ ላይ ቁርኣን ሲቀራ፣ አዛን ሲደረግ የጎሪጥ የተመለከተው አካል የለም። እኛ ጋር ያለውን ክፋት ርቀቱን አሰብኩኝ።

7- የሃገሪቱ ሙስሊሞች በቁጥራቸውም፣ በዲንም ይሁን በአካደሚ በተማረ የሰው ሃይላቸውም፣ በኢኮኖሚያቸውም፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባላቸው ተሳትፎም በጣም ከኛ ያነሱ ናቸው። ከእኛ ባነሰ አቅም ላይ ሆነው ተፍ ተፍ ሲሉ ሳያቸው ግን እኛ አቅማችንን እንደሚገባ እንዳልተጠቀምን ነው የተሰማኝ።

8- ሌላው የደነቀኝ ነገር ሌሎች ህዝቦችን ወደ ኢስላም መጣራት በጣም ቀላል መሆኑ ነው። አንድ ሰው ጎዳና ላይ ደዕዋ ቢያደርግ ብዙ ሰው ሊሰልም ይችላል። ቋሚ ክትትል ካልተደረገ ግን በሌላ ጊዜ ቢመለስ እነዚያን ሰዎች ኢስላም ውስጥ አናገኛቸውም። በቀላል እንደገቡ በቀላል ይወጣሉ፡፡ ሰፊ ስራ ለመስራት ደግሞ የአቅምም፣ የሰው ሃይልም ውስንነት አለ። በኛም ሃገር ተጨባጭ ተግቶ የሚሰራ ጠፍቶ እንጂ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰዎችን ማስለም ከባድ ነገር አይመስለኝም።

9- በሄድኩበት ሃገር ፈርጣማ የኢኮኖሚ አቅም ያላቸው ነገር ግን በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሺ0ዎች አሉ። ደግነቱ ሌሎች ሃገራት ላይ እንደሚታየው ወደ ቡድናቸው የመጣራት ተነሳሽነት የላቸውም። መስጂዳቸው ጭር ያለ ነው። ከህዝቡ እጅግ ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታና ሰፊ መሀይምነት አንፃር ሲታይ ጠንከር ያለ ስብከት ቢኖራቸው አደጋቸው ከባድ ነበር። በነገራችን ላይ ቁጥራቸው እዚህ ግባ የሚባል ባይሆንም ሃገራችን ውስጥ በኢራን ኤምባሲ ድጋፍ በህቡእ የሚንቀሳቀሱ ሺዐዎች አሉ።

10- ሌላው የድርጅቶችን አስፈላጊነት በሚገባ አይቻለሁ። ለሙስሊሙ ህዝብ ድጋፍ እያደረጉ ያሉት ዐረቦች በድርጅት የሚንቀሳቀሱ ናቸው። ያለ ህጋዊ ተቋም (ጀምዒያህ) ምንም አይነት የበጎ አድራጎት ስራዎችን መስራት እንደማይችሉ ሲናገሩ ሰምቻለሁ። በህቡእ ለሚንቀሳቀሱ አካላት የሚሄዱ ገንዘቦችን ለመቆጣጠር ሲሉ መንግስታት የፋይናንስ ፍሰቶችን በጥብቅ ይቆጣጠራሉ። እነዚህ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በርከት ያሉ ትምህርት ቤቶችን፣ መስጂዶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ የህክምናና የሙያ ማሰልጠኛዎችን፣ የአይታም ማዕከሎችን በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ፣ በኤሺያ፣ በአሜሪካ አቋቁመዋል። የመጠጥ ውሃ ጉድጓዶችን ይቆፍራሉ። ሰፋፊ እርዳታዎችን ያከፋፍላሉ። እነዚህን ስራዎች የሚሰሩት በሚሄዱበት ሃገር ከተከፈቱ ህጋዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ነው።
=

© IbnuMunewor




ድመት ድመት መሆኗን ዘንግተህ እንደ በግ treat ልታደርጋት ብትሞክር ፊትህ ላይ ዳማ ትሰራልሃለች፡፡ በጉንም እንደ ድመት ልታጫውተው ከሞከርክ በቴስታ ብሎ ሰማይ ምድሩን ያዞርብሃል፡፡ ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት ጥሩ እንዲሆን የምትፈልግ ከሆነ ሰዎችን ዕወቃቸው ባህሪያቸውንና አመለካከታቸውንም አጥና ፡፡

ህይወት ሰፊ ነች አጋጣሚዎቿም ብዙ ናቸውና የተለያየ ዐይነት ባህሪ ካላቸው ሰዎች ጋር ልታገናኝህ ፣ ልታዛምድህና ልታቆራኝህ ትችላለ ፡፡ አንዳንዱ በባህሪው ግትር ፣ ቁጡ ፣ ነጭናጫ ፣ ጭምት ፣  አዝግ ፣ ተንኮለኛ ፣ አልማጭ ፣ ራስ ወዳድ ፣  ጉረኛ ፣ ትዕቢተኛ ፣ ገለልተኛ ፣ ስግብግብ ፣ ሴሰኛ ፣ ፣ ጨካኝ ፣  ሴረኛ ፣ እኔ ብቻ ልደመጥ ባይ ፣ እኔ ብቻ ቆንጆ ነኝ ባይ ሊሆን ይችላል ፡፡ ሌላው ደግሞ በተቃራኒው አዛኝ ፣ ተጫዋች ፣ ትሁት ፣ ለሰው ሟች ፣ ቁጥብ ፣ ተናናሽ ፣ ፣ ለስላሳ ፣  ተግባቢ  ሊሆን ይችላል ፡፡ ለሁሉም በሽተኛ ተመሳሳይ መድሃኒት እንደማይሰጠው ሁሉ የተለያየ ባህሪ ላላቸው ሰዎችም ተመሳሳይ approachን ማንፀባረቅ ተገቢ አይሆንም ፡፡

ምን አልባት ሁሌም ትሁት እና ለስላሳ መሆን ላያዋጣ ይችላል ፡፡ አንዴ ምን ሆነ መሰላችሁ , የሆነ ጓደኛዬ ወደ መስጂድ ለመሄድ ከቤቱ ወጥቶ መንገድ ጀመረ ፡፡ ውስጥ ለውስጥ እየተጓዘ ሳለም የሆነ ዕብድ ቋጥኝ የሚያህል ድንጋይ ይዞ በሚያስፈራ አካኋን ወደሱ አቅጣጫ እየተግተለተለ  ሲመጣ ተመለከተ ፡፡ ፈርቶ ወደኋላ ቢሮጥ ዕብዱ የያዘውን ድንጋይ ሊወረውርበት ይችላል ፡፡ ብልጡ ጓጀኛዬ ፈጠን ብሎ እሱም ዕብዱ የያዘውን የሚያስንቅ ኪሊማንጃሮ የሚያህል ዐለት ተሸከመና ወደ ዕብዱ አቅጣጫ በፍጥነት መራመድ ጀመረ ፡፡ ወዲያውም ዕብዱ ፊቱን አዙሮ በመጣበት ነካው ፡፡ 💪😎
አንዳንዴ እንዲህም ይሰራል ( ሞክራችሁት ብትፈነከቱ እኔ የለሁበትም 😁 )

ያ ማለት ግን አፀያፊ ስድቦችን የሰደባችሁን ስደቡ
ያዋረዳችሁንም አዋርዱ ማለት አይደለም ፡፡ ለአንዳንዶች ከመልስ ይልቅ ዝምታ ከመብረቅ የበለጠ የሚጮህ አስደንጋጭ መልስ ይሆናል ፡፡

©


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ጥላቻቸውን በሴኩላሪዝም ስም ያቀርቡታል
~
በሴኩላሪዝም ስም የሙስሊሞችን መብት እየተጋፉ ከትምህርት ገበታ ያርቃሉ። በሴኩላሪዝም በሚታወቁት የምእራቡ ዓለም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ግን ሙስሊም ሴቶች ከነ ኒቃባቸው ተምረው ሲመረቁ እያየን ነው። እኛጋ ሴኩላሪዝም ሽፋን እንጂ መንስኤው ጥላቻና ክፋት ብቻ ነው። ምስሉ ላይ እንደሚታየው መንግስታዊ አካላት ፍጥጥ ባለ መልኩ ከነ ዩኒፎርማቸው ሃይማኖታዊ አጀብ ይፈፅማሉ። በየ ቢሮው ስትገቡ መዝሙር ተከፍቶ ታገኛላችሁ። ሃይማኖታዊ ስእሎችንም ይለጥፋሉ። ሙስሊሙ ጋር ሲደርስ ግን በሲኩላሪዝም እያመሀኙ የመማር መብታቸውን ይነፍጋሉ። ማስመሰል በቃ! ጥላቻችሁን በስሙ ጥሩት! በአፄው ዘመን የነበረው ሙስሊሞችን ከትምህርት የማራቅ ሴራ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
=
#ሼር #Share


ሙዘኒይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ አሉ፦

ሻፊዒይ ዘንድ ገባሁ። በሞቱበት ህመማቸው ላይ ሳሉ ነው። "እንዴት አደርክ የ0ብደላህ አባት?" አልኩኝ።
እራሳቸውን ቀና አደረጉ። ከዚያም:
"ዱንያን እየለቀቅኩ፣ ወንድሞቼን እየተለየሁ፣ ክፉ ስራዬን ለመገናኘት፣ ወደ አላህ ለመጓዝ የቀረብኩ ሆኜ አድሬያለሁ። ሩሔ ወደ ጀነት ሆና የምስራች የምላት ትሁን፣ ወደ እሳት ሆና የማረዳት ትሁን አላውቅም" አሉና አለቀሱ።

📚 [አሲየር : 10/75]


#Share
#ሼር
#Share




ብዙ ሰው ትኩረት ነፍጎታል። በተቃራኒው በማይረባ ነገር ተጠምዷል። መረጃው ያለው ሰው ትንሽ ስለሆነ ይመስለኛል።

አመናችሁም አላመናችሁም ሰሞኑን በበርካታ ትምህርት ቤቶች ኒቃብ ተከልክሏል። የሚደርስላቸው ተቋምም ሆነ ድምፅ የሚሆናቸው ግለሰብ አጥተው በርካታ ኒቃቢስቶች ትምህርት ካቆሙ ሳምንት አልፏቸዋል።

ለማን ቢነገር ይሻላል? መጅሊስ ይህን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ በቋሚነት ለምን አይፈታም? ምን እየተካሄደ ነው? ዛሬስ በምን እናመካኝ?

እህቶቻችንን ስልታዊ በሆነ መልኩ ከትምህርት ገበታ ማገድ እስከ መቼ?

ትኩረት ለኒቃቢስት ተማሪዎች!

ኒቃቧንም ትለብሳለች፣ ትምህርቷንም ትማራለች።


(ይህን መልዕክት በማሰራጨት ቢያንስ ሰዎች ዘንድ እየሆነ ስላለው ነገር መረጃው እንዲኖር እናድርግ። በዱዓችንም እናግዛቸው።

©


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ክፍል 3
📕 المحاضرة الثالثة
#ሼር


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ክፍል 2
📕 المحاضرة الثانية
#ሼር


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ክፍል 1
📕 المحاضرة الأولى:
مصادر المعرفة
#ሼር


‏•••═══ ༻✿༺═══ •••
مصادر التلقي ومنهج الاستدلال عند أهل السنة
‏•••═══ ༻✿༺═══ •••
መሰራታዊ ዕውቀትን ሚያስጨብጥ አሪፍ ና ወሳኝ ኮርስ ነበር አዳምጡት 3 ክፍል ነው ሳትሰለቹ አዳምጡት 👌

ቪድዮ ከታች አለላቹህ👇👇

🎙 الملقي:  د.  سعيد بن حسين القحطاني

#ሼር #Share


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
كلمة نافعة:-

عن معرفة الله سبحانه وتعالى بأسمائه وصفاته.


٦ربيع الآخر ١٤٤٦ هجري .





20 last posts shown.